የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 5/15 ገጽ 3
  • እውነተኛ ደህንነት ሊጨበጥ አልቻለም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውነተኛ ደህንነት ሊጨበጥ አልቻለም
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሳይቤሪያ ነብር ከመጥፋት ይተርፍ ይሆን?
    ንቁ!—2008
  • እውነተኛ ደህንነት አሁንም ሆነ ለዘላለም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • “ዓይናችሁን ግለጡና እዩ”
    ንቁ!—1997
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 5/15 ገጽ 3

እውነተኛ ደህንነት ሊጨበጥ አልቻለም

ሕፃኑ አርኖልድ የአሻንጉሊት ነብሩን በጣም ይወደዋል። ሲጫወት፣ ሲመገብም ሆነ ሲተኛ በሄደበት ቦታ ሁሉ አሻንጉሊቱ አይለየውም ነበር። አሻንጉሊቱ አጠገቡ መኖሩ እንዲረጋጋና ደህንነት እንዲሰማው ያደርገው ነበር። አንድ ቀን ችግር ተፈጠረ። አሻንጉሊቱ ጠፋ!

አርኖልድ ማልቀስ ሲጀምር እናቱ፣ አባቱና ሦስት ታላላቅ ወንድሞቹ አሻንጉሊቱን ለማግኘት ትልቁ ቤታቸውን ያስሱ ጀመር። በመጨረሻ ከመካከላቸው አንዱ አሻንጉሊቱን አንድ መሳቢያ ውስጥ አገኘው። አርኖልድ አሻንጉሊቱን መሳቢያው ውስጥ ከከተተው በኋላ የት እንዳስቀመጠው ጠፍቶት ነበር። የነብር አሻንጉሊቱን ሲያገኝ እንባውን አደራረቀ። ደስ ከመሰኘቱም በተጨማሪ እንደገና ደህንነት ተሰማው።

ሁሉም ችግሮች አሻንጉሊት ከመሳቢያ ውስጥ የማግኘት ያክል በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ቢሆኑ ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር! ሆኖም ብዙ ሰዎች የሚያጋጥሟቸው ደህንነታቸውን የሚፈታተኑ ነገሮች ከዚህ በጣም የከፉና ውስብስብ ናቸው። በማንኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ‘ወንጀል ወይም ዓመፅ ይፈጸምብኝ ይሆን? ከሥራ እባረር ይሆን? ቤተሰቤ በቂ ምግብ ያገኝ ይሆን? ሰዎች በሃይማኖቴ ወይም በትውልድ ጎሳዬ የተነሳ ያገልሉኝ ይሆን?’ በማለት ራሳቸውን ይጠይቃሉ።

ብዙ ሰዎች ደህንነት አይሰማቸውም። በተባበሩት መንግሥታት ዘገባ መሠረት ወደ ሦስት ቢልዮን የሚጠጉ ሰዎች ቀላል በሽታዎችን መታከምም ሆነ በጣም አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን ማግኘት አይችሉም። ከአንድ ቢልዮን የሚበልጡ ሰዎች በከባድ ረሃብ ይማቅቃሉ። ወደ አንድ ቢልዮን የሚጠጉ ሰዎች ምንም እንኳ መሥራት ቢችሉም ችሎታቸውን የሚመጥን ወይም በቂ የሆነ ሥራ የላቸውም። የስደተኞች ቁጥር እያሻቀበ ነው። በ1994 ማብቂያ ላይ በግምት ከ115 ሰዎች አንዱ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ተገዷል። ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ወንጀሎችና ዓመፆች መንስኤ የሆነውና በየዓመቱ 500 ቢልዮን ዶላር የሚያስገኘው የዕፅ ንግድ በሚልዮን የሚቆጠር ሕይወት አጥፍቷል። ጦርነት በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጨርሷል። በ1993 ብቻ በ42 አገሮች ውስጥ ከፍተኛ ግጭቶች ሲፈጠሩ በሌሎች 37 አገሮች ውስጥ ደግሞ ፖለቲካዊ ዓመፅ ተካሂዷል።

ጦርነት፣ ድህነት፣ ወንጀልና ሌሎች የሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ነገሮች እርስ በርሳቸው የተቆራኙ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ነው። እነዚህ ችግሮች የጠፋ አሻንጉሊት ከመሳቢያ ውስጥ የማግኘትን ያህል በቀላሉ መፍትሄ የሚገኝላቸው አይደሉም። እንዲያውም ሰዎች ጭራሹኑ እነዚህን ችግሮች አይፈቷቸውም።

የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ “ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ” በማለት ያስጠነቅቃል። ታዲያ በማን መታመን አንችላለን? ይህ ጥቅስ በመቀጠል “የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው፤ እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፣ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ” ነው ይላል።—መዝሙር 146:3-6

ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ ደህንነት እንዲሰፍን ያደርጋል ብለን ማመን የምንችለው ለምንድን ነው? በአሁኑ ጊዜ ደህንነትና ደስታ የሰፈነበት ሕይወት ማግኘት ይቻላልን? ሰዎች ደህንነት እንዳያገኙ እንቅፋት የሆኑባቸውን ነገሮች አምላክ የሚያስወግደው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ