የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 4/15 ገጽ 32
  • ዓለም አቀፍ ሰላም ምንጩ ከየት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓለም አቀፍ ሰላም ምንጩ ከየት ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 4/15 ገጽ 32

ዓለም አቀፍ ሰላም ምንጩ ከየት ነው?

ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ትምህርትና ሃይማኖት ለዓለም ሰላም ሊያስገኝ ይችላል? የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ጸሐፊና ዩኔስኮ ያዘጋጀውን የ1989 የሰላም ትምህርት ሽልማት ተሸላሚ የሆኑት ዶክተር ሮበርት ሙለር ይህ ምኞት አላቸው። ዘ ቫንኮቨር ሰን የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ዶክተር ሙለር “በዓለማችን ላይ የሚገኙ ተማሪዎች በሙሉ ፕላኔታችንን፣ ሰብዓዊነትንና ተቻችሎ መኖርን የሚመለከቱ መሠረታዊ ጭብጦችንና የሥነ ምግባር ደንቦችን ያካተተ ትምህርት መማር አለባቸው የሚል ጽኑ እምነት” አላቸው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት በሙሉ የተባበሩት መንግሥታት ከሁሉ የተሻለ የሰላም ተስፋ መሆኑን ለተማሪዎች የሚያስተምሩበት ጊዜ ይመጣል የሚል አመለካከት አላቸው። “የዓለም ሃይማኖቶች በሙሉ የተባበሩት ሃይማኖቶች በሚል ስያሜ የተባበሩት መንግሥታትን የሚመስል የአንድ አዲስ ድርጅት አባላት መሆን አለባቸው” የሚል እምነትም እንዳላቸው ሰን ሪፖርት አድርጓል። በዓለም ዙሪያ ስለ ሰላም ትምህርት ሲሰጥ “ሁሉም ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ተቻችሎ መኖርን ያራምዳሉ።”

ዓለም አቀፍ ሰላም ዕውን የሚሆንበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ምንም ጥርጥር የለውም! ሆኖም የትኛውም ሰብዓዊ ድርጅት ይህን ማድረግ አይችልም። ከ2,700 ዓመታት በፊት በመንፈስ አነሳሽነት የሚመራ አንድ ጸሐፊ ቅን ልቦና ያላቸው ሰዎች ‘ከእግዚአብሔር የተማሩ እንደሚሆኑና’ ሰላማቸውም “ብዙ” እንደሚሆን በትንቢት ሲናገር ከሁሉ የላቀው የሰላም ትምህርት ምንጭ ማን መሆኑን አሳውቋል።​—⁠ኢሳይያስ 54:​13

መጽሐፍ ቅዱስ ‘የሰላም ምንጭ’ አምላክ መሆኑን ይናገራል። (ሮሜ 16:​20) ይሖዋ ሕዝቦቹ ‘ጦርነትን ከመማር ይልቅ’ ‘ሰላምን እንዲሹና እንዲከተሉ’ እንዲሁም ‘ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ እንዲቀጠቅጡ’ በማስተማር ላይ ስለሆነ በአሁኑ ጊዜም እንኳ አስደናቂ የሆነ ዓለም አቀፋዊ የትምህርት መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።​—⁠1 ጴጥሮስ 3:​11፤ ኢሳይያስ 2:​2-4

ግብዝነትና ማጭበርበር የማይታይበት በእውነት ላይ የተመሠረተ አምልኮ የአምላክን ሞገስና በረከት ያገኛል። (ማቴዎስ 15:​7-9፤ ዮሐንስ 4:​23, 24) በሰላምና በኅብረት የሚኖሩ እንዲሁም እርስ በርስ እውነተኛ ፍቅር ያላቸው ሕዝቦች ሊያስገኝ የሚችለው ሙሉ በሙሉ ከአምላክ ቃል ጋር የሚስማማ እውነተኛ አምልኮ ብቻ ነው።​—⁠ዮሐንስ 13:​35

የአምላክ ቃል ስለ ዓለም ሰላም የሚሰጠውን ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት ከዚህ መጽሔት አሳታሚዎች ጋር እንዲገናኙ እንጋብዝዎታለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ