የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 1/1 ገጽ 30-31
  • ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስለ አምላክ ምሕረት የምናገኘው ትምህርት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 1/1 ገጽ 30-31

ለታዳጊ ወጣቶች

ትሑትና ደፋር የነበረ ሰው

ዮናስ—ክፍል 1

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዮናስ 1:1-17 እንዲሁም ከ2:10 እስከ 3:5 ድረስ አንብብ።

ማዕበሉ ምን ዓይነት ድምፅ የነበረው ይመስልሃል? ማዕበሉ ሲታይ ምን ይመስል ነበር?

․․․․․

ዮናስና በመርከቧ ላይ የነበሩት ሰዎች ድምፅ ምን ዓይነት ስሜት እንደነበራቸው የሚንጸባረቅበት ይመስልሃል?

․․․․․

ዮናስ በባሕሩ ውስጥ በሰመጠበት ጊዜ እንዲሁም ትልቁ ዓሣ ከዋጠው በኋላ ምን አስቦ ሊሆን እንደሚችል ግለጽ። (ዮናስ 2:1-9⁠ን አንብብ።)

․․․․․

2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።

በነነዌ ምን ዓይነት ሰዎች ይኖሩ ነበር? ዮናስ መጀመሪያ ላይ ወደ እነሱ ለመሄድ የፈራው ለምን ሊሆን ይችላል? (ናሆም 3:1)

․․․․․

ነነዌ በአምላክ ዘንድ “ታላቅ ከተማ” ነበረች ሲባል ምን ማለት ነው? (ዮናስ 3:3፤ 2 ጴጥሮስ 3:9)

․․․․․

ዮናስ ስለ ሠራው ስህተትም ሆነ ስለ አምላኩ ሲናገር ግልጽ መሆኑ ስለ እሱ ምን ይጠቁማል? (ዮናስ 1:9, 10⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ዮናስ ወደ ባሕሩ ከተጣለ በኋላ በመርከቧ ላይ የነበሩት ሰዎች ስላደረጉት ነገር ያወቀው እንዴት ሊሆን ይችላል? (ዮናስ 1:15, 16⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ስለ ፍርሃት።

․․․․․

ስለ ትሕትና።

․․․․․

ስለ ድፍረት።

․․․․․

ይሖዋ ስለ ሰዎች ሌላው ቀርቶ እኛ ክፉዎች እንደሆኑ አድርገን ስለምናስባቸው ሰዎች ጭምር ስላለው አመለካከት ምን ተምረሃል?

․․․․․

4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?

․․․․․

ተጨማሪ ምርምር ለማድረግ የጥር 1, 2009 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 25-28 ተመልከት።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት www.watchtower.org ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ