ለታዳጊ ወጣቶች
ስለ አምላክ ምሕረት የምናገኘው ትምህርት
ዮናስ—ክፍል 2
መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።
1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ከዮናስ 3:1 እስከ 4:11 ድረስ አንብብ።
ዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ ሲገባ ምን ተሰምቶት የነበረ ይመስልሃል?
․․․․․
ዮናስ የይሖዋን የፍርድ መልእክት ሲያውጅ ሊኖረው ስለሚችለው የድምፅ ቃና አስብ፤ ከድምፁ ቃና ምን ዓይነት ስሜት እንደነበረው ተገነዘብክ?
․․․․․
ዮናስ ከከተማዋ ውጭ ተቀምጦ ሳለ ምን ተሰምቶት ነበር? (ዮናስ 4:5-8ን አንብብ።)
․․․․․
2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ዮናስ ይሖዋ በነነዌ ላይ አስቀድሞ የተናገረውን ጥፋት እንዲያመጣ የፈለገው ለምን ሊሆን ይችላል?
․․․․․
ምርምር ማድረግ የምትችልባቸው መሣሪያዎችን በመጠቀም (1) የቅል ተክል ምን እንደሚመስልና ያሉትን ባሕርያት (2) የነነዌ ንጉሥ ማቅ መልበሱና አመድ ላይ መቀመጡ ምን ትርጉም እንዳለው ለማወቅ ሞክር።
․․․․․
ዮናስ መጀመሪያ ላይ ወደ ነነዌ ሄዶ ትንቢት ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ እያለ ታማኝና ደፋር ነቢይ ተብሎ ሊጠራ የሚችለው ለምንድን ነው? (ማቴዎስ 21:28-31ን አንብብ።)
․․․․․
3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦
ሰዎች ከመጥፎ አኗኗራቸው መለወጥ ስለመቻላቸው።
․․․․․
ስለ ይሖዋ መሐሪነት።
․․․․․
መሐሪ መሆን ስላለው አስፈላጊነት።
․․․․․
4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?
․․․․․
ተጨማሪ ምርምር ለማድረግ የሚያዝያ 1, 2009 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 14-18 ተመልከት።
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት www.watchtower.org ተመልከት።