የርዕስ ማውጫ
ጥቅምት 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከኅዳር 28, 2011–ታኅሣሥ 4, 2011
ገጽ 8
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 42, 14
ከታኅሣሥ 5-11, 2011
ነጠላነትንና ትዳርን አስመልክቶ የተሰጠ ጥበብ ያዘለ ምክር
ገጽ 13
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 26, 36
ከታኅሣሥ 12-18, 2011
“የመጽናናት ሁሉ አምላክ” በሆነው በይሖዋ ታመኑ
ገጽ 23
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 28, 48
ከታኅሣሥ 19-25, 2011
ገጽ 27
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 38, 42
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 8-12
የምንኖረው የትም ይሁን የት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ ጠቃሚ የሆኑ መዝናኛዎችን ለመምረጥ ይረዳናል። ይህ ርዕስ የመዝናኛ ምርጫችን ጠቃሚ መሆኑን መመዘን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 13-17
አንድ ሰው ነጠላ ሆኖ ከመኖር ወይም ከማግባት ጋር በተያያዘ የሚያደርገው ውሳኔ መላ ሕይወቱን ብቻ ሳይሆን ከአምላክ ጋር ያለውን ዝምድናም ይነካበታል። ይህ ርዕስ ያገቡም ሆነ ነጠላ የሆኑ የአምላክ አገልጋዮች በ1 ቆሮንቶስ ምዕራፍ 7 ላይ የሚገኘውን ምክር ተግባራዊ ማድረጋቸው በሕይወታቸው ውስጥ ወሳኝ በሆነው በዚህ ጉዳይ ረገድ የሚጠቅማቸው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 23-31
በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የይሖዋ አገልጋዮችም ሆኑ ሌሎች ሰዎች በርካታ የሚያስጨንቁ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል። ከእነዚህ ሁኔታዎች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? አስጨናቂ ሁኔታ ሲያጋጥም የሚያስፈልገውን ማጽናኛ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? እነዚህ ሁለት የጥናት ርዕሶች ይሖዋና የእሱ ምሥክሮች በችግር በተሞላው በዚህ ዘመን ሰዎችን የሚያጽናኑት እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
3 ‘ምንጊዜም ነቅቶ መጠበቅ’—በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
18 ይሖዋን ማገልገል ታላቅ ደስታ አስገኝቶልኛል
[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል መግለጫ]
Globe: Courtesy of Replogle Globes