የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 5/1 ገጽ 3-4
  • ለኢየሱስ የቀረበ ጥያቄ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለኢየሱስ የቀረበ ጥያቄ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሌሎች ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራሉ
  • “የዓለም ክፍል አይደሉም”
  • ጨው—ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው ሸቀጥ
    ንቁ!—2002
  • የክርስቲያኖች ትምህርት ማኅበረሰቡን የሚጠቅመው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ሃይማኖት ፖለቲካ ውስጥ መግባቱ ተገቢ ነው?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 5/1 ገጽ 3-4

ለኢየሱስ የቀረበ ጥያቄ

ሃይማኖተኛ የሆኑ ብዙ ሰዎች ሃይማኖት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንዳለበት ይሰማቸዋል። እነዚህ ሰዎች፣ የሰው ልጆችን ችግሮች በመቅረፍ ረገድ ሃይማኖት ትልቅ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ያምናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው በርካታ ሰዎች ሃይማኖትና ፖለቲካ መለያየት እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። አንተስ ሃይማኖት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ስለሚጫወተው ሚና ምን ትላለህ? ኃያል የሆኑት እነዚህ ድርጅቶች እጅና ጓንት ሆነው ሊሠሩ እንደሚገባ ይሰማሃል?

ኢየሱስ ክርስቶስ “በሰው ልጆች ሃይማኖታዊ ታሪክ ውስጥ . . . ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ሰው” እንደሆነ አንድ ጸሐፊ ገልጸዋል። ታዲያ ኢየሱስ ‘ሃይማኖት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት ይኖርበታል?’ የሚል ጥያቄ ቢቀርብለት ምን ብሎ የሚመልስ ይመስልሃል? ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ያስተማረው ትምህርትም ሆነ ያከናወናቸው ነገሮች ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሆናሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ተከታዮቹ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባው ተሳትፎ ለማወቅ የሚረዷቸውን ሐሳቦች ታዋቂ በሆነው የተራራ ስብከቱ ላይ አስተምሯል። በዚህ ስብከቱ ላይ ከጠቀሳቸው ነጥቦች መካከል አንዳንዶቹን እስቲ እንመልከት።

በሌሎች ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራሉ

ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ለዓለም ሊኖራቸው ስለሚገባው አመለካከት ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ሆኖም ጨው የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን እንዴት መልሶ ሊያገኝ ይችላል? ከዚህ በኋላ ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ለምንም ነገር አያገለግልም። እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። . . . ሰዎች መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።” (ማቴዎስ 5:13-16) ኢየሱስ ተከታዮቹን ከጨውና ከብርሃን ጋር ያመሳሰላቸው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ በእነዚህ ዘይቤያዊ አገላለጾች የተጠቀመው ተከታዮቹ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊያሳድሩ የሚችሉትን በጎ ተጽዕኖ ለማጉላት ነበር። ጨው፣ ምግብ እንዳይበላሽ የሚከላከለው ከምግቡ ጋር ከተቀላቀለ ብቻ ነው። በተመሳሳይም መብራት ለአንድ ቤት ብርሃን ሊሰጥ የሚችለው በቤቱ ውስጥ ከበራ ብቻ ነው። ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ እንደሚጠቁመው ተከታዮቹ እንደ ጨው የሚሆኑት ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር ነው፤ በተመሳሳይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ሳይሆን አጥርተው ማየት ለሚፈልጉ ሁሉ እንደ ብርሃን ይሆናሉ። ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ በምድር ላይ ከሌሎች ርቀው የራሳቸውን ማኅበረሰብ እንዲያቋቁሙ አላዘዘም። ተከታዮቹ ከቀረው ዓለም ተገልለው በሃይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ እንዲኖሩም አላበረታታም። ከዚህ በተቃራኒ፣ ጨው ምግብ እንዳይበላሽ መከላከል ብርሃን ደግሞ ጨለማውን መግፈፍ እንዳለበት ሁሉ ክርስቲያኖችም በሌሎች ሕይወት ላይ በጎ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደሚገባ አስተምሯል።

“የዓለም ክፍል አይደሉም”

ይሁንና ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ከማኅበረሰቡ መገለል እንደሌለባቸው የሰጠው መመሪያ አንድ ክርስቲያን ለፖለቲካ ሊኖረው በሚገባው አመለካከት ረገድ ጥያቄ ያስነሳል። ለምን? ኢየሱስ ከመሞቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት ተከታዮቹን አስመልክቶ ወደ አምላክ ሲጸልይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “የምለምንህ ከዓለም እንድታወጣቸው ሳይሆን ከክፉው የተነሳ እንድትጠብቃቸው ነው። እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል አይደሉም።” (ዮሐንስ 17:15, 16) ታዲያ ክርስቲያኖች የዓለም ክፍል ሳይሆኑ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መኖር የሚችሉት እንዴት ነው? የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት እስቲ ሦስት ተጨማሪ ጥያቄዎችን እንመርምር፦

• ኢየሱስ ለፖለቲካ ምን አመለካከት ነበረው?

• ዛሬ ያሉ ክርስቲያኖች በፖለቲካ ውስጥ መግባት አለባቸው?

• የክርስቲያኖች ትምህርት ማኅበረሰቡን የሚጠቅመው እንዴት ነው?

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ራሳቸውን ከኅብረተሰቡ እንዲያገልሉ እንደማይፈልግ ተናግሯል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ