የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 6/1 ገጽ 9
  • “የዘላለም ሕይወት ማግኘት”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የዘላለም ሕይወት ማግኘት”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አሁንና ለዘላለም እውቀት ማካበት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ዮሐንስ 17:3 ላይ የተመዘገቡት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ከአምላክ የሚገኘው እውቀት ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ሌሎች ወደ ሕይወት የሚመራውን እውቀት እንዲያገኙ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 6/1 ገጽ 9

“የዘላለም ሕይወት ማግኘት”

“የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ስለሆንከው ስለ አንተና ስለላክኸው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት መቅሰማቸውን መቀጠል አለባቸው።”​—ዮሐንስ 17:3

እውቀት ሕይወታችንን ሊያተርፍልን ይችላል። በኒጀር የሚኖረው የአሥር ወር ሕፃን የሆነው ኑሁ በታመመ ጊዜ የጤና ረዳት የሆነችው እናቱ ምን ማድረግ እንዳለባት በሚገባ ታውቅ ነበር። ስኳር፣ ጨውና ንጹሕ ውኃ በመቀላቀል ከሰውነቱ የሚወጣውን ፈሳሽ ለመተካት የሚያስችል ውህድ አዘጋጀች። የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እንደገለጸው ይህች እናት “ፈጣን እርምጃ በመውሰዷና በአካባቢው ጤና ጣቢያ በመኖሩ ልጇ ቶሎ ሊድን ችሏል።”

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው እውቀትም ሕይወታችንን ሊያድንልን ይችላል። የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ሙሴ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃሎች አይደሉም፤ በእነርሱ . . . ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።” (ዘዳግም 32:47) በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ረጅም ዘመን እንድንኖር ያስችለናል? መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወታችን ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

ቀደም ባሉት አምስት ተከታታይ ርዕሶች ላይ እንደተብራራው መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው ትንቢት እምነት የሚጣልበት ከመሆኑም ሌላ ከታሪክና ከሳይንስ አንጻር ትክክለኛ መረጃ በማስፈሩ እንዲሁም እርስ በርሱ የሚስማማና ጠቃሚ ምክር የሚሰጥ በመሆኑ ወደርየለሽ መጽሐፍ ነው። ይህም መጽሐፍ ቅዱስን ልዩ እንዲሆን ያደርገዋል። ታዲያ ይህ መጽሐፍ ረጅም ዕድሜ ይኸውም የዘላለም ሕይወት ማግኘት ስለሚቻልበት መንገድ የሚገልጸው ሐሳብ ትኩረት ሊሰጠው አይገባም?

የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛ እውቀት መቅሰም በአሁኑ ጊዜ የአእምሮ ሰላም ወደፊት ደግሞ ደስታ የሚያስገኘው እንዴት እንደሆነ እንድትመረምር እናበረታታሃለን። የይሖዋ ምሥክሮች፣ ይህን እውቀት እንዴት መቅሰም እንደምትችል ሊያሳዩህ ይችላሉ።

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሣጥን/​ሥዕል]

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ለምናነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሊሰጠን የሚችለው ብቸኛ መጽሐፍ መሆኑም የተለየ ያደርገዋል፤ ለምሳሌ፦

• የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው?

• መከራ ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው?

• በሞት ያጣኋቸውን ሰዎች ማግኘት እችላለሁ?

ለሚሉት ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ በይሖዋ ምሥክሮች በተዘጋጀው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? በተባለው መጽሐፍ ላይ ማግኘት ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ