የርዕስ ማውጫ
የካቲት 15, 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. All rights reserved.
የጥናት እትም
ሚያዝያ 1-7, 2013
ገጽ 3 • መዝሙሮች፦ 11, 28
ሚያዝያ 8-14, 2013
ገጽ 8 • መዝሙሮች፦ 22, 28
ሚያዝያ 15-21, 2013
ገጽ 17 • መዝሙሮች፦ 49, 16
ሚያዝያ 22-28, 2013
የአምላክን ክብር እንዳታገኙ ምንም ነገር እንቅፋት አይሁንባችሁ
ገጽ 25 • መዝሙሮች፦ 15, 29
የጥናት ርዕሶች
▪ ይህ መንፈሳዊ ውርሻችን ነው
▪ ለመንፈሳዊ ውርሻችን አድናቆት አላችሁ?
በእነዚህ ርዕሶች ላይ የይሖዋ ሕዝቦች ያላቸውን መንፈሳዊ ውርሻ የተለያዩ ገጽታዎች እንመረምራለን። አምላክ ቃሉ ተጠብቆ እንዲቆይና ስሙን እንድናውቅ ያደረገው እንዲሁም በሐሰት ሃይማኖታዊ ትምህርቶች እንዳንታለል መንፈሳዊውን እውነት ጠብቆ ያቆየልን እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።
▪ ጥበቃ ከምታገኙበት ከይሖዋ ሸለቆ አትውጡ
ይህ የጥናት ርዕስ በዘካርያስ 14:4 ላይ የተገለጸው ጥበቃ የሚገኝበት ሸለቆ ምን እንደሆነ የሚያብራራ ከመሆኑም ሌላ ከዚህ ሸለቆ አለመውጣታችን አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ይጠቁማል። ከዚህም በተጨማሪ በዘካርያስ 14:8 ላይ የተጠቀሰው የሕይወት ውሃ ምን እንደሚያመለክት እንዲሁም ከዚህ ውሃ መጠጣት ምን ጥቅም እንደሚያስገኝልን ያብራራል።
▪ የአምላክን ክብር እንዳታገኙ ምንም ነገር እንቅፋት አይሁንባችሁ
ይህ ርዕስ ይሖዋ ለሰው ልጆች የሚሰጠውን ክብር ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይጠቁማል። ከዚህም በተጨማሪ ይህን ክብር እንዳናገኝ እንቅፋት ሊሆኑብን የሚችሉ ነገሮች ምን እንደሆኑና ይህን ክብር መፈለጋችንን መቀጠላችን ሌሎችን የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
13 የንጉሠ ነገሥቱ የክብር ዘብ አባላት ምሥራቹን ሰሙ
31 ከታሪክ ማኅደራችን
ሽፋኑ፦ በሰሜናዊ ምዕራብ ናሚቢያ የምትገኝ አንዲት አስፋፊ፣ ሂምባ የተባለ የአርብቶ አደር ጎሣ አባል ለሆነች ሴት ምሥራቹን ስትናገር። የሂምባ ሴቶች፣ ከተፈጨ ድንጋይ የሚገኝ ቀይ አፈር ከሌሎች ነገሮች ጋር ደባልቀው ፀጉራቸውንና ገላቸውን ይቀባሉ
ናሚቢያ
የሕዝብ ብዛት
2,373,000
አስፋፊዎች
2,040
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
4,192