የርዕስ ማውጫ
ሰኔ 15, 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. All rights reserved.
የጥናት እትም
ነሐሴ 5-11, 2013
ገጽ 7 • መዝሙሮች፦ 11, 1
ነሐሴ 12-18, 2013
ስለ ይሖዋ ልግስና እና ምክንያታዊነት ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ
ገጽ 12 • መዝሙሮች፦ 22, 15
ነሐሴ 19-25, 2013
ስለ ይሖዋ ታማኝነት እና ይቅር ባይነት ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ
ገጽ 17 • መዝሙሮች፦ 18, 35
ነሐሴ 26, 2013-መስከረም 1, 2013
ገጽ 24 • መዝሙሮች፦ 6, 34
የጥናት ርዕሶች
▪ ስለ ይሖዋ ባሕርያት የተሟላ ግንዛቤ ይኑራችሁ
▪ ስለ ይሖዋ ልግስና እና ምክንያታዊነት ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ
▪ ስለ ይሖዋ ታማኝነት እና ይቅር ባይነት ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ
ብዙ ክርስቲያኖች ስለ ይሖዋ ባሕርያት ሲያስቡ ወደ አእምሯቸው የሚመጡት አራቱ ዋና ዋና ባሕርያቱ ናቸው። ሦስቱ የጥናት ርዕሶች እንደ ዋና ዋናዎቹ የይሖዋ ባሕርያት ትኩረት ስለማናደርግባቸው ሌሎች ባሕርያቱ ያለንን ግንዛቤ ያሳድጉልናል። ስለ እያንዳንዱ ባሕርይ ስናነሳ የሚከተሉት ጥያቄዎች ይብራራሉ፦ ይህ ባሕርይ ምን ማለት ነው? ይሖዋ ይህን ባሕርይ ያሳየው እንዴት ነው? እኛስ ይህን ባሕርይ በማሳየት ረገድ ይሖዋን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?
▪ የይሖዋ ተግሣጽ እንዲቀርጻችሁ ፍቀዱ
ቅዱሳን መጻሕፍት፣ ይሖዋ በሰው ልጆች ላይ ያለውን ሥልጣን በምሳሌያዊ ሁኔታ ሲገልጹ እሱ “ሸክላ ሠሪ” እንደሆነ ይናገራሉ። (ኢሳ. 64:8) ይህ የጥናት ርዕስ፣ ታላቁ ሸክላ ሠሪ በጥንት ዘመናት ግለሰቦችንና ብሔራትን ከቀረጸበት መንገድ ምን ትምህርት እንደምናገኝ ያብራራል። በተጨማሪም በዛሬው ጊዜ አምላክ ሲቀርጸን ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
29 ሽማግሌዎች “የዛለችውን ነፍስ” ታጽናናላችሁ?
32 ታስታውሳለህ?
ሽፋኑ፦ በፍራንክፈርት፣ ጀርመን በሚገኝ አደባባይ ላይ የይሖዋ ምሥክሮች ሲሰብኩ
ጀርመን
የሕዝብ ብዛት
81,751,600
የይሖዋ ምሥክሮች
162,705
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
74,466
በ2012 በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ ሰዎች
265,407