የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 2/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምሥራቹ በእርግጥ ከአምላክ የመጣ ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ከአምላክ የመጣ ነውን?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ?
    ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 2/1 ገጽ 16
በጥንት ዘመን የተዘጋጀ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅልል
በጥንት ዘመን የተዘጋጀ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅልል

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል ነው?

የአምላክ ቃል ለየት ያለ መሆን አለበት ብለህ እንደምትጠብቅ የታወቀ ነው፤ ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ የተለየ መጽሐፍ ነው። በቢሊዮን የሚቆጠሩ የዚህ መጽሐፍ ቅጂዎች በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ታትመዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ፣ ሰዎች ተለውጠው የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ የማድረግ ኃይል አለው።—1 ተሰሎንቄ 2:13⁠ን እና 2 ጢሞቴዎስ 3:16⁠ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ በትክክል የሚናገሩ ትንቢቶችን መያዙ ይህን መጽሐፍ አምላክ እንዳጻፈው እንድንገነዘብ ያደርገናል። ሰዎች በራሳቸው ይህን ማድረግ አይችሉም። የኢሳይያስን መጽሐፍ እንደ ምሳሌ እንመልከት። ኢየሱስ ከመወለዱ ከመቶ ከሚበልጡ ዓመታት በፊት የተገለበጠ የዚህ መጽሐፍ ቅጂ በሙት ባሕር አቅራቢያ ባለ አንድ ዋሻ ውስጥ ተገኝቷል። ይህ ቅጂ የባቢሎን ከተማ ባድማ እንደምትሆን ይናገራል። ይህ ሁኔታ የተፈጸመው ኢየሱስ በምድር ላይ ካገለገለ ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው።—ኢሳይያስ 13:19, 20⁠ን እና 2 ጴጥሮስ 1:20, 21⁠ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው 1,600 በሚያህሉ ዓመታት ውስጥ ነው። አርባ የሚያህሉ ጸሐፊዎች በአንድ ጭብጥ ዙሪያ የሚያጠነጥንና እርስ በርሱ የማይጋጭ ሐሳብ ጽፈዋል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? እነዚህ ሰዎች የጻፉት አምላክ እየመራቸው ስለሆነ ነው።—2 ሳሙኤል 23:2⁠ን አንብብ።

አምላክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን በመላእክት፣ በራእይና በሕልም አማካኝነት ያነጋግራቸው ነበር። በአብዛኛው አምላክ የሚፈልገውን ሐሳብ በአእምሯቸው ውስጥ ያስቀምጥና ጸሐፊዎቹ የፈለጉትን ቃላትና ሐረግ በመጠቀም የእሱን ሐሳብ እንዲያስተላልፉ ያደርጋል።—ራእይ 1:1⁠ን እና 21:3-5⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 2 ተመልከት

www.jw.org/am ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማውረድ ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ