የርዕስ ማውጫ
ሐምሌ 15, 2015
© 2015 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከነሐሴ 31, 2015–መስከረም 6, 2015
ገጽ 7
ከመስከረም 7-13, 2015
ገጽ 14
ከመስከረም 14-20, 2015
ገጽ 22
ከመስከረም 21-27, 2015
ገጽ 27
የጥናት ርዕሶች
▪ መንፈሳዊውን ገነት ይበልጥ አስውቡት
የይሖዋ ሕዝቦች በአምላክ ድርጅት ምድራዊ ክፍል ውስጥ ልዩ የሆነ ሰላም በሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ። ይሖዋ ላደረገልን ለዚህ ዝግጅት ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? መንፈሳዊውን ገነት ይበልጥ ለማስዋብስ በግለሰብ ደረጃ ምን ማድረግ እንችላለን? ይህ ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
▪ ‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’!
ይህ ርዕስ ወደፊት የሚጠብቁንን አንዳንድ የሚያጓጉ ክስተቶች የሚያብራራ ነው። በተጨማሪም የአምላክ ሕዝቦች ታላቁን መከራ በልበ ሙሉነት መጠባበቅ የሚችሉት ለምን እንደሆነ ይገልጻል።
▪ ለአምላክ መንግሥት ምንጊዜም ታማኝ ሁኑ
ሰይጣን በሚመራው በዚህ ዓለም ውስጥ ሰዎች ለተለያየ ነገር ታማኝነት ያሳያሉ። ክርስቲያኖች ግን ለይሖዋ ታማኝ ለመሆን ቃል ገብተዋል። ይህ ርዕስ በዓለም ላይ በሚነሱ ውዝግቦች ውስጥ ከማንም ወገን የማንቆመው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ክርስቲያናዊ ገለልተኝነታችንን ለመጠበቅ አእምሯችንን እና ሕሊናችንን እንዴት ማሠልጠን እንደምንችል ያብራራል።
▪ ይህ የአምልኮ ቦታችን ነው
የይሖዋ ሕዝቦች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት አዳራሾችና ሌሎች ቦታዎች ይሰበሰባሉ። ለመንግሥት አዳራሾቻችን ሊኖረን ስለሚገባው አመለካከት እንዲሁም ለአዳራሹ የገንዘብ ድጋፍ ስለ ማድረግና አዳራሹን ስለ መንከባከብ የሚገልጹ ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በዚህ ርዕስ ላይ እንመለከታለን፤ እነዚህን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረጋችን ለይሖዋ ክብር ያመጣል።
ሽፋኑ፦ የተወሰኑ ክርስቲያኖች ሰፊ በሆነው የሳይቤሪያ ክልል ማዕከላዊ አካባቢ ሲያገለግሉ ቆይተው ምሳ ሲበሉ
ሩሲያ
የሕዝብ ብዛት
143,930,000
አስፋፊዎች