የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp16 ቁጥር 2 ገጽ 11-13
  • ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስማት ሕይወትህን ያተርፍልሃል!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስማት ሕይወትህን ያተርፍልሃል!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በባሕሩ ላይ የሚታየውን ለውጥ በንቃት ተከታተል
  • የአምላክ ፍቅር መግለጫ
  • ከጥፋቱ ለመትረፍ ሽሽ!
  • ቀሳፊ ማዕበል—የሚነገረው ነገርና እውነታው
    ንቁ!—2001
  • የዓለም ፍጻሜ የሚሆነው መቼ ነው? ኢየሱስ ምን ብሏል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • የመጨረሻውን ዘመን በተመለከተ የሚነሱ አራት ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • በ2011 በጃፓን የደረሰው ሱናሚ—ከአደጋው ከተረፉ ሰዎች አንደበት
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
wp16 ቁጥር 2 ገጽ 11-13
በኢንዶኔዥያ ውስጥ በሱማትራ የባሕር ዳርቻ በደረሰው ሱናሚ የወደመ አካባቢ

ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስማት ሕይወትህን ያተርፍልሃል!

ታኅሣሥ 26, 2004 ኢንዶኔዥያ ውስጥ በሱማትራ ሰሜን ምዕራብ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ የምትገኘው ሲመሉወ የምትባል ደሴት በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 9.1 በደረሰ የመሬት መናወጥ ተመታች። በባሕሩ ዳርቻ የነበሩት ሰዎች ባሕሩን እየተመለከቱ ነበር። ባሕሩ ከተለመደው በተለየ መልኩ ወደ መሃል እየሸሸ መሆኑን አስተዋሉ። ወዲያውኑ ሁሉም ሰው ‘ስሞንግ! ስሞንግ!’ (በአካባቢው ቋንቋ ሱናሚ ማለት ነው) እያለ ወደ ተራሮቹ መሮጥ ጀመረ። በ30 ደቂቃ ውስጥ ኃይለኛ ማዕበል ወደ ባሕሩ ዳርቻ የመጣ ሲሆን አብዛኞቹን ቤቶችና መንደሮች ጠራርጎ ወሰዳቸው።

በዚህ አውዳሚ ሱናሚ መጀመሪያ የተመታችው ሲመሉወ ደሴት ነበረች። ይሁንና ከደሴቷ 78,000 ነዋሪዎች መካከል የሞቱት 7 ብቻ ነበሩ። በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ የሟቾቹ ቁጥር ትንሽ የሆነው ለምንድን ነው?a የደሴቷ ነዋሪዎች ‘ኃይለኛ ነውጥ ከተከሰተና ባሕሩ ወደ ኋላ ካፈገፈገ ወደ ተራሮቹ ሽሹ፤ ምክንያቱም ባሕሩ ብዙም ሳይቆይ ወደ ዳርቻው ተመልሶ ይመጣል’ የሚል አባባል አላቸው። የሲመሉወ ነዋሪዎች በባሕሩ ላይ የሚፈጠረውን ለውጥ በማየት ሱናሚ ሊመጣ መሆኑን ማወቅ እንደሚችሉ ከተሞክሮ ተምረዋል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን አይተው እርምጃ መውሰዳቸው ሕይወታቸውን አትርፎላቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ በቅርቡ ጥፋት እንደሚመጣ ይኸውም “ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ ዳግመኛም የማይሆን ታላቅ መከራ” እንደሚከሰት ይናገራል። (ማቴዎስ 24:21) ይህ ሲባል ግን ኃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ድርጊት ወይም በተፈጥሮ አደጋ የተነሳ ምድራችን ትጠፋለች ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም የአምላክ ዓላማ ምድር ለዘላለም እንድትኖር ነው። (መክብብ 1:4) ከዚህ ይልቅ በቅርቡ ታላቅ መከራ የሚሆነው አምላክ ‘ምድርን እያጠፉ ያሉትን ለማጥፋት’ እርምጃ ስለሚወስድ ነው። በዚህ መንገድ ክፋትና መከራ ሁሉ ጨርሶ ይወገዳል። (ራእይ 11:18፤ ምሳሌ 2:22) ይህ እንዴት ያለ በረከት ይሆናል!

ከሱናሚ፣ ከምድር መናወጥ ወይም ከእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች በተለየ መልኩ፣ መጪው ጥፋት የንጹሐን ሰዎችን ሕይወት የሚቀጥፍ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ፍቅር ነው” በማለት ይናገራል፤ ከዚህም ሌላ ስሙ ይሖዋ የሆነው አምላክ “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ” በማለት ቃል ገብቷል። (1 ዮሐንስ 4:8፤ መዝሙር 37:29) ይሁንና ከታላቁ መከራ በሕይወት መትረፍና አምላክ ቃል የገባቸውን በረከቶች ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? ቁልፉ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ሰምቶ እርምጃ መውሰድ ነው!

በባሕሩ ላይ የሚታየውን ለውጥ በንቃት ተከታተል

ኢየሱስ “ስለዚያ ቀንና ሰዓት ከአብ ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ሆኑ ወልድ፣ ማንም አያውቅም” በማለት ስለተናገረ ክፋትና መከራ ሁሉ የሚወገድበትን ቀን ለይተን ማወቅ አንችልም። ያም ቢሆን ኢየሱስ “ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” የሚል ምክር ሰጥቶናል። (ማቴዎስ 24:36፤ 25:13) ነቅተን የምንጠብቀው ምኑን ነው? አምላክ ጥፋቱን ከማምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን ዓይነት ሁኔታዎች እንደሚኖሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጽልናል። በባሕሩ ላይ የታየው ድንገተኛ ለውጥ ሱናሚ እየመጣ መሆኑን የሲመሉወ ነዋሪዎች እንዲገነዘቡ እንደረዳቸው ሁሉ፣ በዓለም ላይ ያሉት ሁኔታዎች በከፍተኛ ደረጃ መለወጣቸውም ጥፋቱ መቅረቡን የሚያሳይ ምልክት ይሆነናል። በዚህ ርዕስ ውስጥ ያለው ሣጥን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ከፍተኛ ለውጦች መካከል አንዳንዶቹን ይጠቅሳል።

እርግጥ ነው፣ በዚህ ሣጥን ውስጥ ከተጠቀሱት ክስተቶች ወይም ሁኔታዎች መካከል አንዳንዶቹን በተናጠል ካየናቸው፣ ከዚህ በፊት በተወሰነ ደረጃ ተፈጽመዋል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ “እነዚህን ሁሉ ነገሮች” ስናይ ጥፋቱ በጣም መቅረቡን ማወቅ እንደምንችል ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:33) ራስህን እንደሚከተለው እያልክ ጠይቅ፦ ‘በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተገለጹት እነዚህ ሁሉ ነገሮች በታሪክ ዘመናት ውስጥ (1) በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈጸሙት፣ (2) በተመሳሳይ ጊዜ ላይ የተከሰቱት እንዲሁም (3) እያደር እየተባባሱ የሄዱት መቼ ነው?’ እነዚህ ነገሮች የተፈጸሙት በዘመናችን እንደሆነ በግልጽ ማየት ይቻላል።

የአምላክ ፍቅር መግለጫ

አንድ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዘዴዎች . . . የሰዎችን ሕይወት ያድናሉ” በማለት ተናግረዋል። በ2004 ከተከሰተው ሱናሚ በኋላ፣ በተመሳሳይ አደጋ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ለመከላከል ሲባል፣ ለአደጋ ተጋላጭ በሆነው ክልል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዘዴ ተቀይሷል። በተመሳሳይም አምላክ፣ ጥፋቱ ከመምጣቱ በፊት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ዝግጅት አድርጓል። መጽሐፍ ቅዱስ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል” የሚል ትንቢት ይዟል።—ማቴዎስ 24:14

ባለፈው ዓመት ብቻ የይሖዋ ምሥክሮች በ240 አገሮችና ከ700 በሚበልጡ ቋንቋዎች ምሥራቹን በመስበክ ከ1.9 ቢሊዮን በላይ ሰዓት አሳልፈዋል። በዘመናችን እየተፈጸመ ያለው ይህ ክንውን ጥፋቱ ለመቅረቡ ጠንካራ ማስረጃ ይሆናል። የይሖዋ ምሥክሮች ለሰዎች ፍቅር ስላላቸው፣ የአምላክ የፍርድ ቀን በፍጥነት እየቀረበ መሆኑን ለማስጠንቀቅ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። (ማቴዎስ 22:39) አንተም ይህ መረጃ የደረሰህ መሆኑ በራሱ፣ ይሖዋ ለአንተ ያለውን ፍቅር ያሳያል። አምላክ “ሁሉ ለንስሐ እንዲበቃ እንጂ ማንም እንዲጠፋ” እንደማይፈልግ አስታውስ። (2 ጴጥሮስ 3:9) ታዲያ ለአምላክ ፍቅር ምላሽ በመስጠት ቅድመ ማስጠንቀቂያውን ሰምተህ እርምጃ ትወስዳለህ?

ከጥፋቱ ለመትረፍ ሽሽ!

በሲመሉወ የባሕር ዳርቻ ባሉ መንደሮች ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች ባሕሩ ሲያፈገፍግ በተመለከቱ ጊዜ፣ ባሕሩ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ከመቆየት ይልቅ ራሳቸውን ከአደጋ ለማዳን ከፍ ወዳለ ስፍራ ወዲያውኑ እንደሸሹ አስታውስ። አፋጣኝ እርምጃ መውሰዳቸው ሕይወታቸውን አትርፎላቸዋል። አንተም ከመጪው መከራ በሕይወት ለመትረፍ ጊዜው ሳያልፍብህ በምሳሌያዊ መንገድ ወደ ከፍታ ቦታ መሸሽ ያስፈልግሃል። ይህን የምታደርገው እንዴት ነው? ነቢዩ ኢሳይያስ “በዘመኑ መጨረሻ” ማለትም እኛ በምንኖርበት ዘመን እየቀረበ ስላለ ለተግባር የሚያነሳሳ ግብዣ በመንፈስ መሪነት ጽፏል። ጥቅሱ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣ . . . እንውጣ። እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤ በጎዳናዎቹም እንሄዳለን” ይላል።—ኢሳይያስ 2:2, 3

ተራራ አናት ላይ መውጣት፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆነህ ሁኔታዎችን ለማየት እንዲሁም ከአደጋው ለመራቅ ያስችልሃል። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ በመላው ዓለም የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የአምላክን መንገዶች ማወቃቸው በሕይወታቸው ውስጥ ጠቃሚ ለውጥ እንዲያደርጉ ረድቷቸዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17) እንዲህ በማድረጋቸው ‘በአምላክ ጎዳናዎች መሄድ’ የጀመሩ ሲሆን የእሱን ሞገስና ጥበቃ እያገኙ ነው።

አንተስ ለዚህ ግብዣ ምላሽ በመስጠት በእነዚህ አስጨናቂ ቀናት የአምላክን ፍቅራዊ ጥበቃ ማግኘት ትችል ይሆን? በዚህ ርዕስ ውስጥ የሚገኘው ሣጥን፣ “በመጨረሻዎቹ ቀኖች” ውስጥ እንደምንኖር የሚያሳዩ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ይዟል፤ ማስረጃዎቹን በትኩረት እንድትመረምር እናበረታታሃለን። በአካባቢህ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች፣ የቀረቡትን ጥቅሶች በግልጽ መረዳትና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ እንድትችል ሊያግዙህ ፈቃደኞች ናቸው። አሊያም ደግሞ www.jw.org/am የተሰኘውን ድረ ገጻችንን በመጎብኘት ለጥያቄዎችህ መልስ ማግኘት ትችላለህ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች >የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚለው ሥር ይገኛል።

a በ2004 ላይ የተከሰተው ይህ ሱናሚ ከ220,000 የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ይህ በታሪክ ከተመዘገቡት እጅግ አውዳሚ ሱናሚዎች አንዱ ነው።

መጨረሻው መቅረቡን የሚጠቁሙ በዓለም ላይ የተፈጸሙ ጉልህ ክንውኖች

መድፍ

ዓለም አቀፍ ጦርነትና እየተባባሰ የሚሄድ ብጥብጥ

“ጦርነትና የጦርነት ወሬ ትሰማላችሁ። በዚህ ጊዜ እንዳትደናገጡ ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸው የግድ ነው፤ ሆኖም ፍጻሜው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤ . . . እነዚህ ነገሮች ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።”—ማቴዎስ 24:6-8

በረሃብ የተቆራመዱ ልጆች

በዓለም ዙሪያ በሽታና ረሃብ ይኖራል

“በተለያየ ስፍራም የምግብ እጥረትና ቸነፈር ይሆናል።”—ሉቃስ 21:11

በካቴና የታሰረ ቄስ

ሕገ ወጥነት ይስፋፋል፤ ብዙዎች በሃይማኖት ግራ ይጋባሉ

“ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤ ክፋት እየበዛ ስለሚሄድ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል።”—ማቴዎስ 24:11, 12

አንድ ቄስ ሁለት ሴቶችን ሲያጋባ

ሥነ ምግባራዊና ማኅበራዊ እሴቶች ታይቶ በማያውቅ ደረጃ ያሽቆለቁላሉ

“በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። ምክንያቱም ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ . . . ታማኝ ያልሆኑ፣ ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው፣ ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ ስም አጥፊዎች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ፣ . . . ይሆናሉ።”—2 ጢሞቴዎስ 3:1-4

የይሖዋ ምሥክሮች የጽሑፍ ጋሪ አጠገብ ሆነው ለአንድ ሰው ሲሰብኩ

የአምላክ መንግሥት ምሥራች በመላው ዓለም ይሰበካል

“ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”—ማቴዎስ 24:14

አንዲት ሴት መጨረሻው እንደቀረበ አለማመኗን ስትገልጽ

ተቺዎች መጨረሻው መቅረቡን ይክዳሉ

“በመጨረሻዎቹ ቀናት . . . የሚያፌዙ ፌዘኞች ይመጣሉ። እነዚህ ፌዘኞች ‘“እገኛለሁ” ያለው ታዲያ የት አለ? አባቶች በሞት ካንቀላፉበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ነገር ከፍጥረት መጀመሪያ አንስቶ እንዳለ ይቀጥላል’ ይላሉ።”—2 ጴጥሮስ 3:3, 4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ