የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp16 ቁጥር 4 ገጽ 14-15
  • ልታደርገው የሚገባ ጠቃሚ ንጽጽር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ልታደርገው የሚገባ ጠቃሚ ንጽጽር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የምናምንባቸውን ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ማነጻጸር የምንችለው እንዴት ነው?
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ወደ ሰማይ እነማን ይሄዳሉ? ለምንስ?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
wp16 ቁጥር 4 ገጽ 14-15

ልታደርገው የሚገባ ጠቃሚ ንጽጽር

የክርስትና እምነት ተከታይ ነህ? በዓለም ዙሪያ ከሁለት ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች የክርስቶስ ተከታይ እንደሆኑ ይናገራሉ። በዛሬው ጊዜ ክርስቲያን ተብለው የሚጠሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ያሉ ቢሆንም እርስ በርሱ በሚጋጭ መሠረተ ትምህርትና አመለካከት ተከፋፍለዋል። በመሆኑም የምታምንባቸው ነገሮች ክርስቲያን እንደሆኑ የሚናገሩ ሌሎች ሰዎች ከሚያምኑባቸው ነገሮች በጣም የተለዩ ሊሆኑ ይችላሉ። የምታምንበት ነገር ለውጥ ያመጣል? አዎ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን ክርስትና መከተል የምትፈልግ ከሆነ የምታምንበት ነገር ለውጥ ያመጣል።

የጥንቶቹ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች “ክርስቲያኖች” ተብለው ይጠሩ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 11:26) በወቅቱ አንድ የክርስትና እምነት ብቻ ስለነበር ተለይተው የሚታወቁባቸው ሌሎች ስሞች አላስፈለጓቸውም። ክርስቲያኖች፣ የክርስትና መሥራች የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶችና መመሪያዎች በአንድነት ይከተሉ ነበር። የአንተ ሃይማኖትስ በዚህ ረገድ እንዴት ነው? ቤተ ክርስቲያንህ ክርስቶስ ያስተማረውንና የጥንቶቹ የክርስቶስ ተከታዮች ያምኑበት የነበረውን ነገር እንደሚያስተምር ታምናለህ? ይህን በእርግጠኝነት ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? ይህን ማወቅ የምትችለው መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ሚዛን አድርገህ በመጠቀም ብቻ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ቅዱሳን መጻሕፍት የአምላክ ቃል እንደሆኑ ስለሚያምን ለእነሱ ጥልቅ አክብሮት ነበረው። ለወጎችና ለልማዶች ሲሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች የሚበርዙ ሰዎችን አይደግፍም ነበር። (ማርቆስ 7:9-13) ከዚህ አንጻር የኢየሱስ እውነተኛ ተከታዮች ለእምነታቸው መሠረት የሚያደርጉት መጽሐፍ ቅዱስን ነው ብለን መደምደም እንችላለን። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ‘የቤተ ክርስቲያኔ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል?’ ብሎ ራሱን መጠየቅ ይኖርበታል። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ቤተ ክርስቲያንህ የሚያስተምረውን ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ለምን አታነጻጽርም?

ኢየሱስ፣ ለአምላክ የምናቀርበው አምልኮ በእውነት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት ተናግሯል፤ እውነት የሚገኘው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። (ዮሐንስ 4:24፤ 17:17) በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ መዳናችን የተመካው “የእውነትን ትክክለኛ እውቀት” በማግኘታችን ላይ እንደሆነ ተናግሯል። (1 ጢሞቴዎስ 2:4) ስለዚህ እምነታችን በትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም መዳናችን ራሱ የተመካው በዚህ ላይ ነው!

የምናምንባቸውን ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ማነጻጸር የምንችለው እንዴት ነው?

በዚህ ርዕስ ውስጥ የቀረቡትን ስድስት ጥያቄዎች እንድትመለከትና መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ እንድታስተውል እንጋብዝሃለን። የቀረቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አንብባቸው፤ በመልሶቹም ላይ አሰላስል። ከዚያም ‘ቤተ ክርስቲያኔ የሚያስተምራቸው ትምህርቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሲነጻጸሩ እንዴት ናቸው?’ ብለህ ራስህን ጠይቅ።

በዚህ ርዕስ ውስጥ የሚገኘው አጭር ጥያቄና መልስ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ንጽጽር እንድታደርግ ሊረዳህ ይችላል። ቤተ ክርስቲያንህ የሚያስተምራቸውን ሌሎች ትምህርቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ማነጻጸር ትፈልጋለህ? የይሖዋ ምሥክሮች ግልጽ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንድትመረምር ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው። ታዲያ ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱን መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንዲያስተምርህ ለምን አትጠይቀውም? ወይም ደግሞ jw.org የተባለውን ድረ ገጻችንን መጎብኘት ትችላለህ።

1 ጥያቄ፦ አምላክ ማን ነው?

መልስ፦ የኢየሱስ አባት የሆነው ይሖዋ ዘላለማዊና ሁሉን ቻይ አምላክ እንዲሁም የሁሉም ነገሮች ፈጣሪ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ስለ እናንተ ስንጸልይ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት የሆነውን አምላክ ሁልጊዜ እናመሰግናለን።”—ቆላስይስ 1:3

“ይሖዋ አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ እንዲሁም ወደ ሕልውና የመጡትም ሆነ የተፈጠሩት በአንተ ፈቃድ ስለሆነ ግርማ፣ ክብርና ኃይል ልትቀበል ይገባሃል።”—ራእይ 4:11

ተጨማሪ ጥቅሶች፦ ሮም 10:13፤ 1 ጢሞቴዎስ 1:17

2 ጥያቄ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

መልስ፦ ኢየሱስ የአምላክ የበኩር ልጅ ነው። ኢየሱስ ፍጡር ነው፤ በመሆኑም መጀመሪያ አለው። ኢየሱስ ለአምላክ የሚገዛ ከመሆኑም ሌላ የአባቱን ፈቃድ በታዛዥነት ይፈጽማል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ከእኔ አብ ይበልጣል።”—ዮሐንስ 14:28

“[ኢየሱስ] የማይታየው አምላክ አምሳልና የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።”—ቆላስይስ 1:15

ተጨማሪ ጥቅሶች፦ ማቴዎስ 26:39፤ 1 ቆሮንቶስ 15:28

3 ጥያቄ፦ መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው?

መልስ፦ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ፈቃዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት ኃይል ነው። በመሆኑም አካል ያለው ነገር አይደለም። ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ኃይል ሊያገኙ ይችላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማህፀኗ ውስጥ ያለው ፅንስ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች።”—ሉቃስ 1:41

“መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኃይል ትቀበላላችሁ።”—የሐዋርያት ሥራ 1:8

ተጨማሪ ጥቅሶች፦ ዘፍጥረት 1:2፤ የሐዋርያት ሥራ 2:1-4፤ 10:38

4 ጥያቄ፦ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

መልስ፦ የአምላክ መንግሥት በሰማይ የሚገኝ መስተዳድር ነው። የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ኢየሱስ ነው። ይህ መንግሥት በቅርቡ የአምላክ ፈቃድ በመላው ምድር ላይ እንዲፈጸም ያደርጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። በሰማይም ታላላቅ ድምፆች እንዲህ ሲሉ ተሰሙ፦ ‘የዓለም መንግሥት የጌታችንና የእሱ መሲሕ መንግሥት ሆነ፤ እሱም ለዘላለም ይነግሣል።’”—ራእይ 11:15

ተጨማሪ ጥቅሶች፦ ዳንኤል 2:44፤ ማቴዎስ 6:9, 10

5 ጥያቄ፦ ጥሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?

መልስ፦ አይሄዱም። አምላክ ወደ ሰማይ እንዲሄዱ የመረጠው “ትንሽ መንጋ” ተብለው የተጠሩ ታማኝ ሰዎችን ያቀፈ አንድ አነስተኛ ቡድን ነው። እነሱም ከኢየሱስ ጋር ነገሥታት ሆነው በሰው ዘሮች ላይ ይገዛሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤ አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗል።”—ሉቃስ 12:32

“የአምላክና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእሱም ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሣሉ።”—ራእይ 20:6

ተጨማሪ ጥቅስ፦ ራእይ 14:1, 3

6 ጥያቄ፦ አምላክ ለምድርና ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

መልስ፦ በአምላክ መንግሥት ሥር ምድር ገነት ትሆናለች፤ ታማኝ ሰዎችም ፍጹም ጤንነት፣ ዘላቂ ሰላምና ዘላለማዊ ሕይወት አግኝተው በምድር ላይ ይኖራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።”—መዝሙር 37:10, 11

“እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።”—ራእይ 21:3, 4

ተጨማሪ ጥቅሶች፦ መዝሙር 37:29፤ 2 ጴጥሮስ 3:13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ