የርዕስ ማውጫ
ከነሐሴ 1-7, 2016 ባለው ሳምንት
6 ይሖዋ እንደሚቀርጸን መገንዘባችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?
ከነሐሴ 8-14, 2016 ባለው ሳምንት
ሸክላ ሠሪ፣ የሸክላ ጭቃን በእጁ በመቅረጽ ውብ ዕቃ የሚሠራ ባለሙያ ነው። ይሖዋ እንደ ሸክላ ሠሪ የሚቀርጸን እንዴት እንደሆነ እንዲሁም በቀላሉ እንደሚቀረጽ የሸክላ ጭቃ ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በእነዚህ ሁለት ርዕሶች ላይ እንመረምራለን።
ከነሐሴ 15-21, 2016 ባለው ሳምንት
አምላካችን ይሖዋ “አንድ ይሖዋ ነው” ሲባል ምን ማለት ነው? “አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ” መሆኑ ከእሱም ሆነ ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ባለን ግንኙነት ረገድ ምን እንድናደርግ ሊያነሳሳን ይገባል? ሁላችንም የተለያየ ባሕልና አስተዳደግ አለን፤ በመሆኑም ይሖዋ፣ “አምላካችን” እንዲሆን ከፈለግን እሱ ከእኛ ምን እንደሚጠብቅ ማወቅ ይኖርብናል።
ከነሐሴ 22-28, 2016 ባለው ሳምንት
23 ሌሎች የሚሠሩት ስህተት እንቅፋት አይሁንብህ
የሰው ልጆች ሁሉ ስህተት ስለሚሠሩ ሌሎችን ሊጎዱ ይችላሉ። ታዲያ ሌሎች በንግግራቸው ወይም በድርጊታቸው ስሜታችንን ቢጎዱት ምን ማድረግ አለብን? ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚረዱንን የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች በዚህ የጥናት ርዕስ ላይ እንመለከታለን።
32 ታስታውሳለህ?