የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/93 ገጽ 3
  • የአካባቢው ብርሃን አብሪዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአካባቢው ብርሃን አብሪዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 1/93 ገጽ 3

የአካባቢው ብርሃን አብሪዎች

1 በዚህ ዓመት የተደረገውን የወረዳ ስብሰባ ከተካፈልን በኋላ ለጎረቤቶቻችን ብርሃን አብሪዎች የመሆንን አስፈላጊነት በይበልጥ ተገንዝበናል። (ማቴ. 5:14) ወደኋላ ተመልሰን በፕሮግራሙ ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ሁሉ ስናስብባቸውና በዕለታዊ ኑሮአችን በሥራ ላይ ለማዋል ስንጥር በእውነተኛው አምልኮ የበለጠ ወደ ይሖዋ ለመቅረብ እንችላለን፤ እንዲሁም ይሖዋ ስለሰጠን ተስፋዎች እንዲማሩ ሌሎችን ለመርዳት የሚያግዝ ዕውቀት ልናገኝ እንችላለን።

2 የሐሙስ ጠዋቱ ፕሮግራም መዝጊያ ላይ ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆንን? የተባለ አዲስ ትራክት በወጣ ጊዜ ብርሃን የማብራት አጋጣሚዎቻችን ይበልጥ ጨምረዋል። ዓርብ ዕለት ጠዋት የነበሩት ትዕይንቶች ይህ ትራክት እንዴት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በማሳየት ረገድ በጣም ጠቃሚዎች ነበሩ። ከዚህ ጋር ደግሞ ሌሎች ሦስት ትራክቶች በቅርቡ እንደሚመጡ የሚገልጽ ማስታወቂያ ነበር። እነዚህም ለተጨነቁት የሚሆን መጽናኛ፣ በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት እና በእርግጥ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? የሚሉ ርዕሶች ያሏቸው ናቸው። አጋጣሚ በሚገኝበት ጊዜ ልንጠቀምባቸው እንችል ዘንድ እነዚህን ለመያዝ ምቹ የሆኑ መሣሪያዎች እንድንይዛቸው ማበረታቻ ተሰጥቷል።

3 “ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ከመከራ መዳን” በተባለው ዓርብ ዕለት ከሰዓት በኋላ በተሰጠው ንግግር መደምደሚያ ላይ አምላክ በእርግጥ ያስብልናልን? የተባለ ጥሩ የሆነ አዲስ ብሮሹር ወጣ። ይህ ባለሙሉ ቀለም የሆነና ጥሩ ጥሩ ስዕሎች ያሉበት ብሮሹር አምላክ መከራ እንዲኖር ለምን ፈቀደ? መከራ ያቆም ይሆንን? በመጨረሻዎቹ ቀኖች ላይ እንደምንኖር እንዴት እናውቃለን? ምድር ወደ ገነትነት የምትለወጠው እንዴት ይሆን? በአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት ልናገኝ የምንችለው እንዴት ነው? የመሳሰሉትን ብዙ ሰዎች የሚጠይቋቸውን ጥያቄዎችን ይመልሳል። ይህ ብሮሹር አዳዲስ ጥናቶችን ለማስጀመር እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ መሣሪያ ነው።

4 በ“ብርሃን አብሪዎች” የወረዳ ስብሰባ ላይ ላገኘነው የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ማዕድ ምንኛ አመስጋኞች ነን! የአምላክ መንፈሳዊ ብርሃን አብሪዎች እንደመሆናችን መጠን የተማርነውን ነገር በጥንቃቄ በሥራ ላይ በማዋልና በየትም ቦታ ያሉ ሰዎች ይሖዋን እንዲያውቁትና እንዲያገለግሉት ለመርዳት በነዚህ ጥሩ የሆኑ አዳዲስ ጽሑፎች በትጋት በመጠቀም ከልብ የመነጨ አድናቆታችንን ለማሳየት እንቁረጥ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ