ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች በጥር፦ በ1980 ወይም ከዚያ ቀደም ብሎ የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ከመደበኛው ዋጋ በግማሽ በመቀነስ ይበረከታል። አቅኚዎች ከመደበኛው የአቅኚ ዋጋ በግማሽ በመቀነስ የመጽሐፎቹን ቅጂዎች ሊወስዱ ይችላሉ። ጉባኤዎች ከ1980 ቀደም ብለው የታተሙትን እነዚህን የቆዩ መጻሕፍት S-20-AM ቅጽ በመሙላት የዋጋው ልዩነት እንዲቀነስላቸው ሊጠይቁ ይችላሉ።
◼ ከየካቲት በመጀመር አለዚያም ግፋ ቢል ከመጋቢት 7 ሳያልፍ የክልል የበላይ ተመልካቾች መስጠት የሚጀምሩት አዲስ የሕዝብ ንግግር ርዕስ “ወጣቶችን ከይሖዋ አመለካከት አንፃር መመልከት” የሚል ይሆናል።
◼ ለ1993 የመታሰቢያው በዓል የሚደረገው ልዩ የሕዝብ ንግግር በዓለም ዙሪያ እሁድ መጋቢት 28 ይሰጣል። የንግግሩ ርዕስ “‘የአምላክን ሥራዎች’ እንዴት ትመለከቷቸዋላችሁ?” የሚል ይሆናል። አስተዋጽዖው ይላክላችኋል። በዚያ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ የክልል የበላይ ተመልካች ጉብኝት፣ የክልል ስብሰባ ወይም የልዩ ስብሰባ ቀን የሚኖራቸው ጉባኤዎች ልዩ ንግግሩን ከዚያ በሚቀጥለው ሳምንት ያደርጋሉ። ማንኛውም ጉባኤ ልዩ ንግግሩን ከመጋቢት 28 በፊት ማድረግ አይኖርበትም።
◼ ከጥር 1, 1993 ጀምሮ በሊቱኒያ ቋንቋ ወርኀዊ የመጠበቂያ ግንብ እትም ይኖራል። ይህም መጽሔቱ የሚታተምባቸውን ቋንቋዎች ቁጥር 112 ያደርሰዋል። በተጨማሪም ከጥር ጀምሮ በቴሉጉ ቋንቋ የሚዘጋጀው የመጠበቂያ ግንብ እትም በወር ሁለት ጊዜ መውጣት ይጀምራል።
◼ በዚህ ዓመት የመታሰቢያው በዓል የሚውለው ማክሰኞ ሚያዝያ 6, 1993 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ነው። አዲስ የመታሰቢያው በዓል አስተዋጽዖ ይኖራል። ሽማግሌዎች ለዚህ ትልቅ በዓል ቅድመ ዝግጅት ማድረግ መጀመር ይኖርባቸዋል።
◼ የ1993 የዓመት ጥቅስ:- “አቤቱ ይሖዋ፣ አስተምረኝ፣ . . . ስምህን ለመፍራት ልቤን አንድ አድርግልኝ።” — መዝሙር 86:11 አዓት
◼ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የእንግሊዝኛ መጻሕፍት የደረሱን ስለሆነ ማዘዝ ይቻላል።
ታላቁ ሰው፣ ምክንያቱን ማስረዳት፣ የሙታን መናፍስት፣ የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ፣ የቤተሰብ ኑሮ፣ የመዝሙር መጽሐፍ፣ ለዘላለም መኖር፣ የ1992 የዓመት መጽሐፍ፣ የመጠበቂያ ግንብ ባውንድ ቮልዩም 65–79፣ 89፣ 91፤ የንቁ! ባውንድ ቮልዩም 89–91፤ የወጣቶች ጥያቄ፣ ፍጥረት፣ መጽሐፌ፣ ኢንዴክስ 30–85፣ መንግሥትህ ትምጣ፣ እውነተኛ ሰላምና ደህንነት፣ ከዕልቂት ተርፎ፣ የአምላክ ቃል ወይስ የሰው፣ ወጣትነትህ፣ የመዝሙር ካሴቶች፣ ቪዲዮ ካሴቶች።