ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
ቺሊ፦ በሚያዝያ ወር ሪፖርት ካደረጉት 42,778 አስፋፊዎች መካከል 8,680ዎቹ አቅኚዎች ነበሩ። እንዲሁም 2,820 የሚሆን አዲስ የዘወትር አቅኚዎች ከፍተኛ ቁጥር ላይ ደርሰዋል። በሚያዝያ ወር ሪፖርት ያደረጉት ጠቅላላ ሰዓት 1,009,001 ነበር።
ሌሴቶ፦ በሚያዝያ ሪፖርት ያደረጉት አስፋፊዎች ድምር 1,895 የነበረ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት አማካይ ቁጥር 19 በመቶ ጭማሪ ነበር።
ፖርቱጋል፦ በሚያዝያ 41,472 የሚሆን አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሰዋል። በሰዓት፣ በተመላልሶ መጠየቅና በቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ጠቅላላ ድምርም አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነበራቸው።
ቬንዙዌላ፦ 62,074 የሚሆኑት አስፋፊዎች ጠንክረው በመሥራታቸው በሚያዝያ ወር በሰዓት፣ በተመላልሶ መጠየቅና በቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ሊገኝ ችሏል።
የሚከተሉት ጉባኤዎች ሰሞኑን የመንግሥት አዳራሾቻቸውን አስመርቀዋል:- በኬንያ ውስጥ ጊታሩ፣ ሲያያ እና ሊሙሩ፤ በታንዛንያ ውስጥ እምበያ ሚጂኒ፣ እምበያ ኢሳንጋ፣ እምበያ ሲንሲቲላ እና ኪዬላ። ሌሎች ጉባኤዎችም በቅርቡ የመንግሥት አዳራሾቻቸውን ለማስመረቅ ዕቅድ አላቸው።