በከቤት ወደ ቤት በምናደርገው አገልግሎት በመጽሔቶቻችን መጠቀም
1 የንቁ! መጽሔት ዓላማ በእያንዳንዱ እትም ገጽ 4 ላይ በግልጽ ተቀምጧል። “ይህ መጽሔት በ1914 የተፈጸሙትን ነገሮች ያየው ትውልድ ከማለፉ በፊት ሰላማዊ የሆነና የሕይወት ዋስትና ያለው አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ፈጣሪ በሰጠን ተስፋ ላይ ያለንን ትምክህት ይገነባል” ይላል። እንዲህ ያለ መጽሔት ከቤት ወደ ቤት በምናደርገው አገልግሎታችን የተቻለንን ያህል በስፋት ልናሰራጨው የሚገባ መሆኑ የተረጋገጠ ነው!
2 ንቁ! መጽሔት መንፈሳዊ ዝንባሌ የሌላቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማነሳሳት የሚረዳ በጣም ጥሩ መጽሔት ነው። እያንዳንዱን እትም ስታነብ ለሌሎች ለመንገር የሚስማሙ ነጥቦችን ፈልግ። አንዳንድ አስፋፊዎች በራሳቸው ቅጂ ላይ ማስታወሻ ይጽፉና መጽሔቱን ይዘው ወደ መስክ አገልግሎት ከመሄዳቸው በፊት ከሰዎች ጋር የሚነጋገሩባቸውን ነጥቦች በአእምሮአቸው ለመያዝ በመጽሔቱ ላይ የያዟቸውን ማስታወሻዎች ይከልሷቸዋል።
3 በያዝነው የንቁ! መጽሔት ውስጥ የተብራራ አንድ ነጥብ በቀጥታ በማንሳት ውይይታችንን ለመጀመር እንፈልግ ይሆናል።
የቤቱ ባለቤት ፍላጎት ካሳየ እንዲህ በማለት መጽሔቱን ልናስተዋውቀው እንችል ይሆናል፦
◼ “በንቁ! መጽሔት ውስጥ ያለው ይህ ርዕስ ጉዳዩን የበለጠ በዝርዝር ያብራራዋል።” ከዚያ በኋላ አስቀድመህ የመረጥካቸውን አንድ ወይም ሁለት ዓረፍተ ነገሮች አንብብለትና እንዲህ በማለት ቀጥል:- “ይህ ጉዳይ የማረከዎት ይመስላሉ። ይህንን ርዕስና በዚህ የንቁ! መጽሔት ውስጥ ያሉትን ሌሎቹንም ወቅታዊ የሆኑ ርዕሶች ሊያነቧቸው ይፈልጋሉ? ማንበብ የሚፈልጉ ከሆነ ይህንንና የዚህ መጽሔት ተጓዳኝ የሆነውን የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ቢወስዱ ደስ ይለኛል። ለመጽሔቶቹ የምንጠይቀው መዋጮ — ብቻ ነው።”
4 ሰውየው ለመንፈሳዊ ነገሮች ፍላጎት እንዳለው በግልጽ ከተናገረ ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት የሚናገረውን በ2 ጢሞቴዎስ 3:1–5 ላይ ያለውን ወይም ሌላ ጥቅስ ልንጠቅስለት እንችላለን። ከዚያ በኋላ ለመጽሔቶቻችን ፍላጎት እንዲያድርበት ለማድረግ በቅርብ በወጣው የመጠበቂያ ግንብ እትም ገጽ 2 ላይ ያለውን “የመጠበቂያ ግንብ ዓላማ . . .” በማለት የሚጀምረውን ክፍል በቀጥታ ልናነብለት እንችላለን። ከዚያም በቅርብ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እትሞች በተለመደው ዋጋቸው እንዲወስድ ልንጠይቀው እንችላለን።
5 እውነተኛ ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኝ እንዲህ ልትለው ትፈልግ ይሆናል፦
◼ “እዚህ ሰፈር ከኛ በጣም የሚለዩ ብዙ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ ሰዎች አግኝተን አነጋግረናቸው ነበር። የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ ብዙ የተለያዩ አቅጣጫዎችን የተከተለ ሆኗል። [ሥራ 17:26, 27ን አንብብ።] አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ራሳቸው አምላክን ከመፈለግ ይልቅ የወላጆቻቸውን ሃይማኖት ይከተላሉ ቢባል አይስማሙም? [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ በተባለው በዚህ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ ያለው ነጥብ ይህ ነው። [በገጽ 8 አንቀጽ 12 ላይ ያለውን ሐሳብ ጎላ አድርገህ ግለጽ።] ስለ ሌሎች ሃይማኖቶች የበለጠ ማወቁ እውቀትን የሚያዳብርና ትምህርት ሰጪ ነው። ይህ መጽሐፍ በዓለም ላይ ያሉትን ዋና ዋናዎቹን ሃይማኖቶች አመጣጥ፣ የሃይማኖት ሥርዓትና ትምህርት ያብራራል።” ጊዜ ካለህ ምዕራፎቹ የተዘረዘሩበትን ገጽና በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን አንድ ሁለት ሥዕሎች አሳየው።
6 ከቤት ወደ ቤት ስንሄድ ሰዎች መንፈሳዊ ዕድገት እንዲያደርጉ ከሚረዷቸው በዓለም ላይ ካሉት መሣሪያዎች ሁሉ የተሻሉ የሆኑትን ሁለት መሣሪያዎች ማለትም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን መያዛችንን አንዘንጋ። በነዚህ መጽሔቶች አማካኝነት የሰዎችን ፍላጎት ለመቀስቀስና ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለማበርከት እንጣር።