ማስታወቂያዎች
◼ በአገልግሎት የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች:- በኅዳር፦ የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም እና መጽሐፍ ቅዱስ — የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ። በታኅሣሥ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ። በጥር፦ ቀለሙ እየደበዘዘ ወይም እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ ወይም ከ1980 በፊት የታተሙ ማናቸውንም ባለ 192 ገጽ መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። በየካቲት፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት ወርኀዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S–14–AM) ላይ መጠየቅ ይችላሉ።
◼ በኮምፒዩተር ዲስኬቶች ተቀርጾ የወጣ ሌላ አዲስ ጽሑፍ:- ባለ ማጣቀሻው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም/ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል። ይህ አዲስ የወጣ የኮምፒዩተር ዲስኬት የአዲሲቱ ዓለም ትርጉምን እና ማስተዋል የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ሁለት ጥራዞች አንድ ላይ የያዘ ነው። ዲስኬቶቹ የተዘጋጁት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ ሲሆን የሚገኙትም በ5 1/4–ኢንች 1.2–ሜጋባይት ወይም በ3 1/2–ኢንች 1.44–ሜጋባይት ዲስኬቶች ነው። በእነዚህ ዲስኬቶች ለመጠቀም ቢያንስ 18 ሜጋባይት የሚሆን ባዶ ቦታ ያለው ባለ ሃርድ ዲስክ ኮምፒዩተር ያስፈልጋል። ለጉባኤዎች ሁሉ የተላከው ደብዳቤ ስለነዚህ አዳዲስ ዲስኬቶችና ዲስኬቶቹን ለማግኘት ማዘዝ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የተቀረጸባቸውንም ዲስኬቶች ማግኘት ይቻላል።