የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/93 ገጽ 2
  • የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 11/93 ገጽ 2

የኅዳር የአገልግሎት ስብሰባዎች

ኅዳር 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 172

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች በመንግሥቱ የስብከት ሥራ ለሚያደርጉት ተሳትፎ አመስግናቸው።

10 ደቂቃ፦ “ሕልሞች።” ምክንያቱን ማስረዳት የተባለው መጽሐፍ ገጽ 104–106። ከመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ጋር በሚደረግ ውይይት መልክ የሚቀርብ። ተማሪው በሕልም መመራት ጥበብ ስለመሆኑ ጥያቄ ይጠይቃል። የዚህን ነገር አደገኛነት ይኸውም የዓለማዊ አስተሳሰቦችና የአጋንንት ተገዥዎች እንዴት ሊያደርገን እንደሚችል ንገረው። በአምላክ ቃል ውስጥ ባሉት መሠረታዊ ሥርዓቶች የመመራትን አስፈላጊነት ግለጽለት።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤ እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ወይም በነሐሴ 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 3–8 ላይ በወጣው “የሐሳብ ግንኙነት ሲባል መነጋገር ማለት ብቻ አይደለም” በሚለው ርዕስ ላይ የተመሠረተ ንግግር።

15 ደቂቃ፦ “መጽሐፍ ቅዱስ ለዛሬው ዓለም ያለው ጠቀሜታ።” ከቤት ወደ ቤት በመሄድ በሚያከናውነው አገልግሎት ችሎታውን ለማሻሻል በሚፈልግ አንድ አስፋፊና በአገልግሎት የበላይ ተመልካች መካከል የሚደረግ ውይይት። ከአንቀጽ 3 በኋላ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ እንደ ባለቤት ሆኖ የተነጋገሩባቸውን አቀራረቦች በመለማመድ እንዲሞክሯቸው የበላይ ተመልካቹ አስፋፊውን ይጠይቀዋል። አንቀጽ 4⁠ን ከተመለከቱ በኋላ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በጽሑፉ ላይ ያለውን አቀራረብ ለአስፋፊው ይነግረዋል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችና የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ን ጠቃሚነት እንዲገነዘቡት እንዲረዷቸው ጉባኤውን አበረታታ።

መዝሙር 85 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ልዩ የመስክ አገልግሎት ወር” በሚለው ርዕስ ላይ እንዲያተኩሩ አድርግና በታኅሣሥ ረዳት አቅኚዎች በመሆን ወይም ከአቅኚዎች ጋር በመሥራት የመስክ አገልግሎታቸውን ከፍ ለማድረግ የሚችሉበትን አጋጣሚ ሁሉም በቁም ነገር እንዲያስቡበት ጋብዛቸው።

15 ደቂቃ፦ “እውነተኛ መመሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ።” በጥያቄና በመልስ የሚሸፈን ትምህርት። በአንቀጽ 3 ላይ የተገለጸው ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። ከቤት ወደ ቤት በመሄድ እንዲሁም ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ ስላለው ተግባራዊ ጥቅም ሰዎችን በሚያነጋግሩበት ጊዜ ሞቅ ባለ ስሜት የሚናገሩ እንዲሆኑ ሁሉንም አበረታታ። ጽሑፎቹን በእጃችሁ ያዙ፤ ጽሑፉን በማስተዋወቅ ሰውየው እንዲወስደው በምትጠይቁበት ጊዜ ይሆናል የሚል ገንቢ አመለካከት ይኑራችሁ።

20 ደቂቃ፦ “ወጣቶች ሆይ፣ የይሖዋን ልብ አስደስቱ።” ከአንቀጽ 1–18 አንድ ሽማግሌ ያብራራል። ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነታቸው የሚያገኟቸውን ጥቅሞችና “የወጣቶች ጥያቄ . . .” በሚል ርዕስ የሚወጡትን ትምህርቶች ጠቃሚነት አጉላ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ጥቅሶችን አንብበህ ግለጽ።

መዝሙር 113 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ ካለ ጨምረህ አቅርብ። ለጉባኤውና ለማኅበሩ ዓለም አቀፍ ሥራ ማካሄጃ ስለሚያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ጉባኤውን አመስግን። በመጪው ቅዳሜና እሁድ የሚኖሩትን የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶች ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ “መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የሚያስፈልጓቸውን መንፈሳዊ ነገሮች ማቅረብ።” ጥያቄና መልስ። በጉባኤያችሁ ውስጥ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ከሌሉ በአገልግሎት ክልል ውስጥ የሚገኙትን የመስማት እክል ያለባቸው ሰዎች ችላ ባለማለቱ ላይ አተኩር። መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የተዘጋጀው አዲስ የወጣ ትራክት ይኑራችሁ። ቅርንጫፍ ቢሮውን በመጠየቅ ትችላላችሁ።

20 ደቂቃ፦ “ወጣቶች ሆይ፣ የይሖዋን ልብ አስደስቱ።” በአባሪው ላይ ያለው ርዕሰ ትምህርት ከአንቀጽ 19–33 በጥያቄና መልስ ይሸፈናል። ከአንድ ሁለት ወጣት አስፋፊዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ጉባኤው ለመንፈሳዊ ዕድገታቸው እንዴት እንደረዳቸው ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። ሁሉም በፊታችን ቅዳሜና እሁድ በምስክርነቱ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታቸው።

15 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ለጥናታቸው እንዲዘጋጁ እርዳቸው።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ የፈቀደልህን ያህል አንዳንድ አንቀጾችን አንብብ።

20 ደቂቃ፦ “ከቅዱሳን ጽሑፎች ምክንያቱን ታስረዳለህን?” ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎትና ተመላልሶ በመጠየቅ ውጤታማ በሆነ ወንድም በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። (2 ጢሞ. 4:2) አንቀጽ 5⁠ን ከተመለከታችሁ በኋላ ምክንያቱን ማስረዳት የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም ውጤታማ የሆነ አንድ አስፋፊ ጠርተህ መጽሐፉን ለምስክርነቱ ሥራ እንዴት እንደሚጠቀምበት እንዲናገር ጠይቀው።

መዝሙር 136 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ኅዳር 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 19

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሚችሉ በታኅሣሥ ረዳት አቅኚዎች እንዲሆኑ አበረታታ። በቅርብ የወጡ መጽሔቶችን እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል በፊታችን ቅዳሜና እሁድ በመስክ አገልግሎት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን መጽሔት ሲያበረክት የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናዊው ሰው የሚሆን ተግባራዊ መመሪያ።” በግንቦት 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ላይ የተመሠረተ የቤተሰብ ራስ በሆነ ወንድም የሚቀርብ ንግግር። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ ሰላማዊ የሆነና ፍቅር ያለበት ቤተሰብ እንዲኖር እንደሚያስችል ጎላ አድርገህ ግለጽ። ከአምላክ ቃል የሚገኙ ምክሮች አንድን ቤተሰብ ወይም ግለሰብ እንዴት እንደረዱ የሚያሳዩ በቅድሚያ ዝግጅት የተደረገባቸው አንድ ሁለት አስተያየቶች ከአድማጮች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ፦ በግ መሰል ሰዎችን ለመርዳት በታኅሣሥ ወር ታላቁ ሰው የተባለውን የእንግሊዝኛ መጽሐፍ መጠቀም። ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ስለ ኢየሱስ አገልግሎት ወይም ከሌሎች ጋር ስላደረጋቸው ግንኙነቶች ከሚገልጹት ታሪኮች ውስጥ ይበልጥ የነካችሁ የትኛው ነው? ይህ ታሪክ ሊነካችሁ የቻለው ለምንድን ነው? ይህ ጽሑፍ ምን ያህል ጠቅሟችኋል? መጽሐፉን በማጥናት ስለ ይሖዋ ምን አውቃችኋል? መጽሐፉን ለሌሎች በምታስተዋውቁበት ጊዜ የተጠቀማችሁት በየትኛው (በየትኞቹ) ነጥቦች ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ተጠቀም። ጥሩ ልምድ ያለው አስፋፊ ይህንን መጽሐፍ ለሌላ ሲያስተዋውቅ የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። እሁድ በመስክ አገልግሎት ሁሉም እንዲካፈሉ አበረታታቸው።

መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ