ማስታወቂያዎች
◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች መስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ቅጂዎች ይበረከታሉ። የመጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባትም ይቻላል። ኅዳር፦ ወጣትነትህን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀምበት። ታኅሣሥ፦ የራእይ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ። ጥር፦ ታላቁ አስተማሪ ወይም ዘላለማዊ ዓላማ (በእንግሊዝኛ) የተባሉትን መጽሐፎች።
ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስከ አሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S-14 AM) መጠየቅ አለባቸው። እባካችሁ የሚያስፈልጓችሁን ያህል በጥቅምት ወር የሚበረከቱ ተጨማሪ መጽሔቶችን እዘዙ።
◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም ሌላ እሱ የመደበው ወንድም የጉባኤውን ሒሳብ መስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ መመርመር አለበት። ምርመራው ከተደረገ በኋላም ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ በጥቅምት ወር ረዳት አቅኚ ለመሆን ያቀዱ አስፋፊዎች አስቀድመው ማመልከቻቸውን መሙላትና መስጠት አለባቸው። ይህም ሽማግሌዎች አስፈላጊውን የጽሑፍም ሆነ የአገልግሎት ክልል ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
◼ ወደ ጉባኤው ሊመለሱ የሚፈልጉትን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦች በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲከተሉ ሽማግሌዎችን እናሳስባለን።