የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/95 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 3/95 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በመጋቢት፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። በሚያዝያና በግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በተደጋጋሚ በተሸፈኑ ክልሎች (ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች ከተባለው ብሮሹር በስተቀር) ማንኛውንም ብሮሹር መጠቀም ይቻላል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ኮንትራት እንዲገቡ መጠየቅ ይቻላል። በሰኔ፦ ወጣትነትህ እና ቤተሰብ የተባሉት መጻሕፍት። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14 AM) መጠየቅ አለባቸው።

◼ በ1996 የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ማክሰኞ ሚያዝያ 2, ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። የ1996 የመታሰቢያው በዓል ስለሚከበርበት ቀን ይህ ማስታወቂያ ከረዥም ጊዜ በፊት መውጣቱ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች በአንድ የመንግሥት አዳራሽ በሚጠቀሙበትና ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ የግድ መፈለግ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ወንድሞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወይም አዳራሽ እንዲከራዩ ሲባል ነው።

◼ ከመስከረም 1, 1994 ጀምሮ በየአሥራ አምስት ቀኑ የሚታተመው መጠበቂያ ግንብ በጣልያንኛ ቋንቋ በካሴት መውጣት ጀምሯል። እርግጥ በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ የሚወጣው የመጠበቂያ ግንብ ካሴትም መውጣቱን ይቀጥላል።

◼ አደጋ በደረሰባቸውና ስደት ባለባቸው ቦታዎች የሚገኙ ወንድሞችን ለመርዳት ለማኅበሩ የእርዳታ ገንዘብ መላክ የሚፈልጉ ጉባኤዎች ለዚህ ዓላማ የሚያገለግል የመዋጮ ሣጥን ሊያዘጋጁና ከዚህ ሣጥን የሚገኘውን ገንዘብ “እርዳታ” በሚል ርዕስ በጽሑፍ ቅናሽ መጠየቂያ ቅጽ (S– 20–AM) በሌላ መስመር ላይ ሊያሰፍሩ ይችላሉ።

◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም እሱ የወከለው ሰው መጋቢት 1 ወይም በተቻለ መጠን ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ ከመድረክ ማስታወቂያዎችን የሚያቀርቡ ወንድሞች የሠርግ ዝግጅቶችን ወይም ሌሎች ማኅበራዊ ተግባሮችን በተመለከተ ከመድረክ ማስታወቂያ መናገር ወይም የማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ መለጠፍ እንደሌለባቸው እናሳስባቸዋለን። ለሠርግ ወይም ለሌላ ማኅበራዊ ተግባር ተብሎ የየትኛውም የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም መለወጥ የለበትም። በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ስለሚደረግ የጋብቻ ንግግር ብቻ አጠር ያለ ማስታወቂያ ይነገራል።

◼ በቅርቡ ይመጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ጽሑፎች:-

በአማርኛ፦ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? በጣልያንኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች። በትግርኛ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? (T-13) የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው ያምናሉ? (T-14) እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው? (T-16)

◼ አንዳንድ የዋጋ ማስተካከያዎች:- የቀን መቁጠሪያ:- ለሁሉም በአምስት ብር፤ ካሴቶች (አንዱ):- (ለአቅኚዎች) ብር 15.25፣ (ለአስፋፊዎች) ብር 16.50፣ የውዳሴ መዝሙሮች (8 ካሴቶች):- (ለአቅኚዎች) ብር 104.00፣ (ለአስፋፊዎች) ብር 121.50። የሌሎች ካሴቶችን ዋጋ ልትጠይቁ ትችላላችሁ።

◼ ሽማግሌዎች በመጋቢት 3 እና 4 በመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤት ስለሚካፈሉ ከየካቲት የመንግሥት አገልግሎታችን ጋር ተያይዞ በወጣው አባሪ ጽሑፍ ላይ ወይይት በሚደረግበት በዚያ ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ላይገኙ ይችላሉ። የአገልግሎት ስብሰባ ክፍሎችን በማቀያየር ይህን ክፍል በሌላ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ልትወስዱት ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ