የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/95 ገጽ 2
  • የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 6 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 13 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 20 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 27 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 3/95 ገጽ 2

የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች

መጋቢት 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34

13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ለአገልግሎት ስለምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች የሚገልጸውን የጥያቄ ሣጥን ተወያዩበት።

15 ደቂቃ፦ “ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል።” ጥያቄና መልስ። ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ብቃት ያላቸው ሁሉ በሚያዝያ ወር ለመመዝገብ እንዲያስቡበት አበረታታ።

17 ደቂቃ፦ “ቤታቸው ሄደን ካላነጋገርናቸው እንዴት ይሰማሉ?” እና “ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስተዋወቅ” የሚል ርዕስ ባላቸው የሐምሌ 1994 እና የየካቲት 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ላይ የተመሠረተ “ሰዎች በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር እንደሚችሉ ይወቁ” በሚል ርዕስ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚያቀርበው ንግግር። በተጨማሪም ከቤት ወደ ቤት አገልግሎት የሚያስገኛቸውን ጥሩ ውጤቶች የሚጠቁም የጉባኤውን ተሞክሮ አጠር አድርገህ አቅርብ። በሚቀጥለው ሳምንት የየካቲት 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን እትም እንደሚያስፈልግ ጥቀስ።

መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 177

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “ለጸሐፊውና ለአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የተሰጠ ማሳሰቢያ” የሚል ርዕስ ባለው ሣጥን ላይ ጥቂት ሐሳቦችን ስጥ። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ፦ “በመላው ዓለም የሚሰራጭ ወቅታዊ የመንግሥት ምሥራች።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በሚያዝያና በግንቦት ወራት የሚደረገውን የዚህን ልዩ የሥራ እንቅስቃሴ ጠቀሜታ አጉላ። አዲሶችን ጨምሮ ሁሉም ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ እቅድ እንዲያወጡ አበረታታቸው።

20 ደቂቃ፦ “ተስፋ የሌላቸው ሰዎች በሚያዝኑበት መንገድ አለማዘን” የሚለውን ርዕስ ከልስ። (2/95 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ አባሪ ሆኖ የወጣውን ትምህርት ተመልከት።) የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከአድማጮች ጋር ተወያይባቸው:- 1. ብዙ ዝርዝሮችን ከያዙ ደንቦች ይልቅ ይሖዋን የሚያስደስቱ ውሳኔዎችን ለማድረግ የሚረዳን ምንድን ነው? 2. (ሀ) በእኛ አስተሳሰብና በአብዛኞቹ ሰዎች አስተሳሰብ መካከል ምን ከፍተኛ ልዩነት አለ? (ለ) እድር የማንገባው ለምንድን ነው? 3. (ሀ) ዓለማውያን በሚያዝኑበት መንገድ የማናዝነው ለምንድን ነው? (ለ) በኢዩኤል 2:12, 13 ላይ ያለው ጥቅስ ሐዘንና ውጪያዊ ልብስን በተመለከተ ምን ይጠቁማል? 4. (ሀ) የኤፌሶን 5:15, 16⁠ን ምክር ከተከተልን ከየትኞቹ ልማዶች እንርቃለን? (ለ) በሐዘን ላይ ሆነንም እንኳ ቲኦክራሲያዊ ልማዶቻችንን ማከናወናችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል? 5. ከቀብር ሥነ ሥርዓቶች ጋር በተያያዘ መንገድ “ቀላል ዓይን” እንዳለን የምናሳይባቸውን ተግባራዊ መንገዶች ዘርዝር። 6. ለቀብር ሥነ ሥርዓቶች የሚደረጉትን ወጪዎች መቀነሳችን ምን ለማድረግ አጋጣሚዎችን ይፈጥርልናል? 7. ምንም ቃል ሳይተነፍሱ ከመቀመጥ ይልቅ ይበልጥ ለማጽናናትና ለማበረታታት የሚረዱት የትኞቹ ውጤታማ መንገዶች ናቸው? 8. ሌሎችን ለማጽናናት የምናደርጋቸውን ጥረቶች በዘልማድ ከተወሰኑት ጊዜያት ጋር ማያያዝ ወይም ሐዘኑ በተከሰተበት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ መወሰን የሌለብን ለምንድን ነው? 9. ቤቱ ተቀምጦ ለቅሶ ደራሾችን እንዲጠብቅ ማንንም የማናበረታታው ለምንድን ነው? 10. ምንም ተስፋ ከሌላቸው ሰዎች የተለየን መሆናችንን ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 11. ኢየሱስ ካሳየው ምሳሌ ጋር በሚስማማ መንገድ ውጪያዊ የሐዘን መግለጫዎችን በማሳየት ረገድ ከዓለም የምንለየው እንዴት ነው? 12. ፈጽሞ ልንርቃቸው የሚገቡን ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ልማዶች የትኞቹ ናቸው? 13. (ሀ) እውነተኛ ክርስቲያኖች ከዓለም የተለዩ መሆን የማያስፈራቸው ለምንድን ነው? (ለ) ተስፋ የሌላቸው ሰዎች በሚያዝኑበት መንገድ አለማዘናችን ምን ጥቅሞችን ያስገኝልናል? 14, 15. (ሀ) ለቀብር የሚደረጉ ወጪዎች የሚሸፈኑበት ሥርዓት ምንድን ነው? (ለ) ጉባኤው በጉዳዩ ውስጥ ጣልቃ የሚገባው በምን ሁኔታዎች ወቅት ነው? እንዴትስ? 16. በሐዘን ላይ ላሉ የይሖዋን በረከትና እውነተኛ መጽናናት የሚያስገኝላቸው ምን ዓይነት አቋም ነው?

መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 191

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችንና በየካቲት 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ስለ ሠርግ ግብዣዎች የወጣውን የጥያቄ ሣጥን አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “እንዴት ብለህ ትመልሳለህ?” ከአንድ ወይም ሁለት ትዕይንቶች ጋር በውይይት የሚቀርብ።

15 ደቂቃ፦ “ዲያቆናት ጠቃሚ አገልግሎት ያበረክታሉ።” መሪ የበላይ ተመልካቹ ከተጠመቁ አንድ ዓመት ያህል ቢሆናቸውም ገና ዲያቆን ካልሆኑ አንድ ወይም ሁለት እድገት የሚያሳዩ ወንድሞች ጋር አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 6 ይወያያል። በውይይቱ መደምደሚያ ላይ እያንዳንዱ አስፋፊ የመጽሐፉ ቅጂ እንዲኖረው አሳስብ።

መዝሙር 114 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

መጋቢት 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

8 ደቂቃ፦ “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” በተባለው ርዕስ ላይ የሚሰጥ ንግግር።

10 ደቂቃ፦ የመስክ አገልግሎታችሁን በትክክል ሪፖርት አድርጉ። ጸሐፊው በሪፖርት ረገድ ያጋጠሙትን ችግሮች ይገልጻል። ወርሃዊው ሪፖርት ሙሉ ሰዓት መሆን እንዳለበት ጥቀስ። መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሠከር፣ ጽሑፍ ሲበረከትና ተመላልሶ መጠየቆች ሲደረጉ እንዴት ሪፖርት መመዝገብ እንደሚቻል የሚጠቁሙ ጥቂት ምክሮችን ለግስ። ተመላልሶ መጠየቅ ተብሎ ሪፖርት የሚደረገው ምን እንደሆነ ግለጽ። (አገልግሎታችን ገጽ 102–103) ጊዜ ከተገኘ ጉባኤው በሚያስፈልጉት ሌሎች ነገሮች ላይ ውይይት ማድረግ ይቻላል።

12 ደቂቃ፦ “በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከተከሰቱት ነገሮች ሁሉ የላቀ ትርጉም ያለው ድርጊት።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ጉባኤው ለመታሰቢያው በዓል ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ጠቁም። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች መጋበዝና እንዲገኙ መርዳት ያለብን ለምን እንደሆነ ግለጽ።

10 ደቂቃ፦ በሚያዝያ ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ማበርከት። በተጨማሪም በተደጋጋሚ በተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎች (ትምህርት ቤት ከተባለው ብሮሹር በስተቀር) ማናቸውንም ብሮሹር ማበርከት እንችላለን። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ኮንትራት እንዲገቡ መጠየቅ ይቻላል። ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ወቅት መጽሔቶችን ለማበርከት የሚቻልባችውን የሚከተሉትን ሐሳቦች ግለጽ:- የወዳጅነት ስሜት የሚንጸባረቅበትን ፈገግታ አሳይ። ግለት ይኑርህ። ረጋ ብለህ ተናገር። በአንድ መጽሔት ውስጥ ካሉት ርዕሰ ትምህርቶች ውስጥ አንዱን ብቻ አብራራ። የሚቀጥሉት እትሞች ሲወጡ ተመልሰህ እንደምትመጣ አሳውቀው። ሰውዬው መጽሔቶቹን ካልወሰደ አዎንታዊ መደምደሚያ አቅርብ። ሰዎች ያሳዩትን ፍላጎትና ያበረከትካቸውን ጽሑፎች በማስታወሻህ ላይ መዝግብ። በመደምደሚያው ላይ በቅርቡ የወጡትን መጽሔቶች እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚጠቁሙ አንድ ወይም ሁለት አጫጭር አቀራረቦችን በትዕይንት አሳይ።

መዝሙር 79 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ