ማስታወቂያዎች
◼ በመስከረም ወር የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት መደረግ አለበት። ጥቅምት፦ ንቁ! እና መጠበቂያ ግንብ። የመጽሔቶቹን ቅጂዎች ለማበርከት ልዩ ጥረት አድርጉ። ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ የምናነጋግረው ሰው ልባዊ ፍላጎት ካሳየ ኮንትራት እንዲገባ ሐሳብ ልናቀርብለት እንችላለን። ኅዳር፦ የቤተሰብ ኑሮ እና/ወይም ወጣትነትህ የተባሉት መጽሐፎች እያንዳንዳቸው በ3 ብር ይበረከታሉ። ከላይ የተዘረዘሩትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14–AM) መጠየቅ አለባቸው።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው መስከረም 1 ወይም በተቻለ መጠን ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ለጉባኤው አስታውቅ።
◼ በጥቅምት ወር ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች ማመልከቻቸውን ቀደም ብለው መስጠት አለባቸው። ይህም ሽማግሌዎች ጽሑፍንና የአገልግሎት ክልልን በተመለከተ አስፈላጊ ዝግጅቶች ለማድረግ ያስችላቸዋል።
◼ ሽማግሌዎች መመለስ የሚፈልጉ የተወገዱና ራሳቸውን ያገለሉ ሰዎች በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21–3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲከተሉ ልናሳስባቸው እንወዳለን።
◼ ለ1996 የአገልግሎት ዓመት የሚያገለግሉ በቂ ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ ተልከዋል። እባካችሁ S-10-AM እና S-18-AM የተባሉትን ቅጾች ሞልታችሁ በወቅቱ መላካችሁን አትርሱ።
◼ ደስተኛ አወዳሾች የተባለው የአውራጃ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚካሄድባቸው ቀናት ተለውጠዋል። በአዲሱ የፕሮግራም ለውጥ መሠረት ስብሰባው የሚካሄደው መስከረም 22–24, 1995 ይሆናል። ይህ የፕሮግራም ለውጥ ሊያስከትል ለሚችለው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን።
◼ እባካችሁ በአማርኛው ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 91 ላይ ሥራ 15:28 የሚለውን ምሳሌ 15:28 ብላችሁ አስተካክሉት።