ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎቸ:- መጋቢት፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። ሚያዝያና ግንቦት፦ የመጠበቂያ ግንብና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት እንዲገቡ ልንጋብዛቸው እንችላለን።
◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ በየካቲት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ እንደተጠቀሰው በዚህ ዓመት በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር በብዙ ጉባኤዎች እሁድ ሚያዝያ 21 ይቀርባል። ንግግሩ “በጠማማ ትውልድ መካከል ያለነቀፋ መኖር” የሚል ርዕስ አለው። ሚያዝያ 2 ቀን በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙትን ሰዎች ይህ ንግግር ሲቀርብ እንዲገኙ ለመጋበዝ ልዩ ጥረት መደረግ ይኖርበታል።
◼ የመንግሥት አገልግሎታችን ለአስፋፊዎችና ዘወትር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚገኙ እድገት በማድረግ ላይ ላሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የበላይ ተቆጣጣሪነት በመጽሐፍ ጥናት መሪዎቻቸው በኩል መታደል አለበት። በመጽሔት ማከፋፈያ ዴስክ ላይ መውጣት አይኖርበትም።
◼ አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፋችን ገጽ 105 ላይ እንደተገለጸው የአስፋፊዎች መዝገብ (S-21-AM) ጉባኤ በሚቀይሩት አስፋፊዎች እጅ መላክ የለበትም። ከዚህ ይልቅ አስፋፊው በተዛወረበት አዲስ ጉባኤ ውስጥ የሚገኘው ጸሐፊ አስፈላጊዎችን መዝገብ ለማግኘት አስፋፊው በመጀመሪያ ወደ ነበረበት ጉባኤ ጸሐፊ ደብዳቤ መጻፍ ይኖርበታል።
◼ አንዳንድ ደብዳቤዎች እየጠፉ በመሆኑ ሁሉም ጉባኤዎችና ቡድኖች የነጋዴዎችን፣ የትምህርት ቤት ወይም የሚያውቋቸውን ሰዎች ፖስታ ሣጥን ከመጠቀም ይልቅ የራሳቸው የፖስታ ሣጥን ቢኖራቸው ጥሩ ይሆናል።
◼ ለቤቴል ቤተ መጻሕፍታችን የ1992ና ከዚያም በፊት ያሉትን የአማርኛ የመጠበቂያ ግንቦች ለማግኘት እንፈልጋለን። በዚህ በኩል የምታደርጉልንን ድጋፍ በጣም እናደንቃለን።
◼ የ1995ን ዋችታወር ላይብረሪ በአዲስ CD-ROM ለማዘጋጀት የሚደረገው ጥረት እየተጠናቀቀ ነው። ይህ እንደገና የተሻሻለውን ፕሮግራምና በ1995ና በ1994 የወጡትን አዳዲስ ጽሑፎች እንዲሁም ከ1979-70 ያሉትን ጽሑፎች ያካተተ ይሆናል። ማግኘት ስለሚቻልበት ዝርዝር ሁኔታ ቆየት ብሎ ይገለጻል።
◼ በእጃችን ያሉ አዲስ ጽሑፎች፦ እውቀት (በትግርኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በስፓኒሽና ፖርቹጋል ቋንቋዎች)፤ ትምህርት (በፈረንሳይኛና በጣልያንኛ)፤ አዋጅ ነጋሪዎች (በፈረንሳይኛ)፤ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም (በስፓኒሽና በፖርቹጋል)፤ የምታፈቅሩት ሰው ሲሞት (በፈረንሳይኛ)፤ እነሆ! (በእንግሊዝኛ)፤ ራእይ (እንግሊዝኛ) በአረብኛ፦ በደስታ ኑር!፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?፣ የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ፣ መጽሐፌ፣ ማመራመር፣ ራእይ፣ ታላቁ ሰው፣ የሙታን መናፍስት፣ የሕይወት ዓላማ