የመጋቢት ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
መጋቢት 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 47
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “‘ቀኑን ሙሉ’ ይሖዋን ባርኩ” በጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ከ2-5 ያሉትን አንቀጾች አንብብ። ረዳትና የዘወትር አቅኚ ሆኖ ስለማገልገል አዎንታዊ ማበረታቻ ስጥ።
20 ደቂቃ፦ “ከእውነተኛው አምላክ የሚገኘው እውቀት ወደ ሕይወት ይመራል።” የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስ። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።
መዝሙር 175 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መጋቢት 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 177
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት በጉባኤ ውስጥ ካሉ ወንድሞች የተገኘ አንድ የሚያንጽ ተሞክሮ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ከ1996 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጥቅም ማግኘት— ክፍል 3።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ሁኔታቸው የሚፈቅድላቸው ሁሉ እንዲመዘገቡና እምነት የሚጣልባቸው በመሆን ክፍላቸውን እንዲያቀርቡ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ በቤተሰብ መልክ አብራችሁ ሥሩ። አንድ አባት በመስከረም 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-19 ላይ ተመሥርቶ አንድ ላይ የመሥራትን አስፈላጊነት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከቤተሰቡ ጋር ይወያያል። በቤተሰብ ጥናትና በወንጌላዊነቱ ሥራ ላይ ያተኩራል። በዛሬው ጊዜ ያሉ ቤተሰቦች አብረው የሚያሳልፉት ጊዜ ባለመኖሩና ምንም ዓይነት የጋራ አመለካከት ስለሌላቸው እየፈራረሱ እንዳሉ ጠቁም። የአምላክን ቃል አብሮ ማጥናት በመስክ አገልግሎት አንድ ላይ መካፈል ለክርስቲያን ቤተሰብ በረከት ያመጣል። አባት እነዚህን ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ማደራጀቱና እናት መተባበሯ ያለውን ጠቀሜታ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር ተቀራርበው በመሥራት ለመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል። ቤተሰቡ አንድነት ያለው ይሆናል፤ እንዲሁም እየጨመረ የመጣውን ዓለማዊ ዝንባሌ የመያዝ ግፊት ለመቋቋም የሚያስችል ጠንካራ አቋም ይኖረዋል።
መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ መዝሙር
መጋቢት 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጥናት ያላቸው አስፋፊዎች ጥሩ እድገት እያደረጉ ያሉት ጥናቶቻቸው ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ለመሆን እንዲጣጣሩ ሊያበረታቷቸው ይገባል። ወላጆችም ልጆቻቸው አስፋፊዎች እንዲሆኑ ሊረዷቸው ይችላሉ። አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 97-100 ላይ የተዘረዘሩትን ሥርዓቶች ከልስ።
15 ደቂቃ፦ “ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት”፣ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ገጽ 133 ከሚጀምረው ንዑስ ርዕስ እስከ 137። ጥያቄና መልስ።
20 ደቂቃ፦ “ሌሎች ወደ ሕይወት የሚመራውን እውቀት እንዲያገኙ እርዷቸው።” ለተመላልሶ መጠየቅ የቀረቡትን ሐሳቦች ከልስ። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎችን ጨምረህ አቅርብ። ጥናት የማስጀመር ግብ እንዲኖራቸው ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
መዝሙር 204 እና የመደምደሚያ መዝሙር
መጋቢት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 105
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ክፍል ከልስ። በበዓሉ ላይ መገኘት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት አስረዳ። (የካቲት 15, 1985 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-20 ተመልከት።) አረጋውያን፣ የአካል ጉዳተኞችና አዲሶች በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ለመርዳት የተደረገውን ዝግጅት ጥቀስ። ከፊታችን ባለው ሳምንት ሰፊ የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ለማካሄድ ስለ ተደረጉት ዝግጅቶች ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በጥር 15, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-17 ላይ እንደተገለጸው ለጋሶች እንድንሆን የሚያንቀሳቅሱን ምክንያቶች ምን እንደሆኑ አብራራ።
15 ደቂቃ፦ “ለስኬታማነት ቁልፉ ዝግጅት ነው።” ጥያቄና መልስ። በሚያዝያና ግንቦት ወር መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እንደምናበረክት ጥቀስ። ከወዲሁ ተጨማሪ ቅጂዎችን በማዘዝ፣ የኮንትራት ማስገቢያ ቅጾችን በመያዝና ጉባኤው ካደረገው የመጽሔት ቀን ዝግጅት ጋር ለመተባበር ዕቅድ በማውጣት ዝግጅት አድርጉ።
መዝሙር 155 እና የመደምደሚያ ጸሎት