የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/96 ገጽ 1
  • በእምነት ተመላለሱ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በእምነት ተመላለሱ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “እምነት ጨምርልን”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • እምነት—በመንፈሳዊ የሚያጠነክር ባሕርይ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ይሖዋ በገባው ቃል ላይ እምነት እንዳላችሁ በተግባር አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • “በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 9/96 ገጽ 1

በእምነት ተመላለሱ

1 በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በሀብት የማታለያ ኃይል ላይ በሞኝነት ትምክህት በመጣል ሕይወታቸው በቁሳዊ ንብረቶች ላይ እንዲያተኩር አድርገዋል። (ማቴ. 13:22) ሀብታቸው ሲጠፋ ወይም ሲዘረፍ አለዚያም ሊያከናውነው የሚችለው ነገር ውስን መሆኑን ሲመለከቱ ከደረሰባቸው መራራ ተሞክሮ ይማራሉ። እኛ ግን መንፈሳዊ ሀብት ለመሰብሰብ በመጣጣር የጥበብን ጎዳና እንድንከታተል በጥብቅ ተመክረናል። (ማቴ. 6:19, 20) ይህም ‘በእምነት መመላለስን’ የሚጨምር ነው።— 2 ቆሮ. 5:7

2 “እምነት” የሚለው ቃል የተተረጎመው መመካት፣ መተማመንና ጽኑ እምነት የሚል ትርጉም ከሚያስተላልፈው የግሪክኛ ቃል ነው። በእምነት መመላለስ ማለት በአምላክ መመካት እንዲሁም አካሄዳችንን ለማቃናት ባለው ችሎታና የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን በመተማመን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ማለት ነው። ኢየሱስ ትኩረቱን በጣም አንገብጋቢ በሆኑ ነገሮች ላይ አድርጎ ወደፊት በመግፋት ፍጹም ምሳሌ ትቶልናል። (ዕብ. 12:2) እኛም በተመሳሳይ ልባችንን ዘወትር በማይታዩት መንፈሳዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ማድረግ ይኖርብናል። (2 ቆሮ. 4:18) የአሁኑ ሕይወታችን ዋስትና እንደሌለው ልብ ማለትና ከይሖዋ ተነጥለን ፈጽሞ መኖር እንደማንችል መገንዘብ አለብን።

3 በተጨማሪም ይሖዋ በ“ታማኝና ልባም ባሪያ” አመራር አማካኝነት በምድራዊ ድርጅቱ በኩል እየመራን እንዳለ ጽኑ እምነት ሊኖረን ይገባል። (ማቴ. 24:45-47) በጉባኤ ውስጥ ‘ቀዳሚ ሆነው ለሚያገለግሉት ስንታዘዝ’ እምነታችንን በተግባር እናሳያለን። (ዕብ. 13:17 አዓት) ከቲኦክራሲያዊ ዝግጅቶች ጋር በትሕትና ተባብረን መሥራታችን በይሖዋ እንደምንተማመን ያሳያል። (1 ጴጥ. 5:6) ድርጅቱ እንዲያከናውን ለተሰጠው ሥራ የሙሉ ልብ ድጋፍ ለመስጠት መነሣሣት ይኖርብናል። ይህም ከወንድሞቻችን ጋር በጠንካራ የፍቅርና የአንድነት ማሠሪያ ያስተሳስረናል።— 1 ቆሮ. 1:10

4 እምነትን ማጠንከር የሚቻለው እንዴት ነው?፦ እምነታችን ባለበት እንዲቆም ማድረግ አይገባንም። እምነታችንን ለማጠንከር ከባድ ተጋድሎ ማድረግ ያስፈልጋል። በጥናት፣ በጸሎትና በስብሰባዎች አዘውታሪ መሆን እምነታችንን ያጠናክርልናል፤ እምነታችን ጠንካራ መሆኑ ደግሞ በይሖዋ እርዳታ ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቋቋም ያስችለናል። (ኤፌ. 6:16) በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበትና ለስብሰባዎች የምትዘጋጅበት ጥሩ የጥናት ልማድ አለህን? ብዙ ጊዜ በተማርካቸው ነገሮች ላይ ታሰላስላለህን? እንዲሁም ወደ ይሖዋ ትጸልያለህ? በሁሉም ስብሰባዎች ላይ የመገኘትና አጋጣሚ ስታገኝ የመሳተፍ ልማድ አለህን?— ዕብ. 10:23-25

5 በጎ ሥራዎች የጠንካራ እምነት ማረጋገጫ ናቸው። (ያዕ. 2:26) እምነታችንን በተግባር ከምናሳይባቸው ጥሩ ጥሩ መንገዶች አንዱ ስለ ተስፋችን ለሌሎች መናገር ነው። ምሥራቹን ለማካፈል የምትችልባቸውን አጋጣሚዎች ለማግኘት ትጥራለህን? በአገልግሎት ይበልጥ ለመሳተፍ ሁኔታዎችህን ማስተካከል ትችላለህን? የአገልግሎታችን ጥራትና ውጤታማነት ለማሻሻል የሚሰጡንን ሐሳቦች ትጠቀምባቸዋለህን? በግልህ መንፈሳዊ ግቦችን አውጥተህ እነዚያ ግቦች ላይ ለመድረስ ትጣጣራለህን?

6 ኢየሱስ ስለ ዕለት ተዕለት ሕይወታችን ከልክ በላይ በመጨነቅ ቁሳዊ አስተሳሰብ ወይም የራስ ወዳድነት ፍላጎት መንፈሳዊ እይታችንን እንዲያደበዝዝብን መፍቀድ እንደሌለብን አስጠንቅቋል። (ሉቃስ 21:34-36) እምነታችን እንደ መርከብ የመስመጥ ወይም የመሰበር አደጋ ደርሶበት እንዳይጠፋ አካሄዳችንን ንቁ ሆነን መጠበቅ ይኖርብናል። (ኤፌ. 5:15፤ 1 ጢሞ. 1:19) መጨረሻ ላይ ‘መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫዬን ጨርሼአለሁ፣ እምነቴን ጠብቄአለሁ’ ብለን ለመናገር እንችላለን ብለን ሁላችንም ተስፋ እናደርጋለን።— 2 ጢሞ. 4:7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ