የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች
መስከረም 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 207
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ሁሉም ወንድሞችና እህቶች ቅዳሜና እሁድ በሚደረጉት የመስክ ስምሪት ስብሰባዎች ላይ ሲገናኙ ከቤት ወደ ቤት ባደረጉት አገልግሎት ያጋጠማቸውን ችግርና ተመሳሳይ ሁኔታ ሲኖር እንዴት መወጣት እንደሚቻል እንዲወያዩ አበረታታቸው።
15 ደቂቃ፦ “በእምነት ተመላለሱ።” ጥያቄና መልስ።
18 ደቂቃ፦ “አዎንታዊ አመለካከት በመያዝ ምሥራቹን ማቅረብ።” በአንቀጽ አንድ ላይ የተመረኮዘ የመግቢያ ሐሳብ አቅርብ። በእጃችን ላለው የቤተሰብ ኑሮ ለተባለው መጽሐፍ ቅድሚያ ልንሰጥ እንደሚገባ ግለጽ። ከዚያም አንቀጽ ከ2-6 ያለውን ሸፍን። ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ሠርቶ ማሣያዎችን አቅርብ። “የቤተሰብ ኑሮ” የተባለውን መጽሐፍ ካበረከቱ በኋላ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የሚዘጋጁ ካሉ በ1/96 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4 (ከታች) አንቀጽ 3 ላይ የቀረበውን ሐሳብ ጠቁማቸው። ምናልባትም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ስለ ማበርከት በ12/95 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10 ላይ የተሰጡትን ተግባራዊ ሐሳቦች ለመጥቀስ ትፈልግ ይሆናል።
መዝሙር 175 እና የመደመምደሚያ ጸሎት
መስከረም 9 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። “መንግሥቱን ስበኩ” የሚለውን ርዕስ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ የጉባኤውን የ1996 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ከልስ። በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በግለት የሚቀርብ የሚያንጽ ንግግር። (አገልግሎታችን የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 100-2 ተመልከት።) የጉባኤው ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገበትን ጎን በመጥቀስ አመስግን። የዘወትርና ረዳት አቅኚዎች ተሳትፎ የጉባኤውን እንቅስቃሴ በማሳደግ ረገድ ምን ሚና እንደተጫወተ ግለጽ። ምን ያህል የአገልግሎት ክልሎች እንደተሸፈኑ፣ የተሰብሳቢዎች ቁጥር ምን ያህል እንደነበርና አዘውትሮ በስብሰባዎች ላይ መገኘት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጥቀስ። በመጪው ዓመት ጉባኤው ሊደርስባቸው የሚገቡትን ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግቦች ጠቁም።
20 ደቂቃ፦ “‘የአምላካዊ ሰላም መልእክተኞች’ የ1996 የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ” የሚል ርዕስ ባለው ባለፈው ወር የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ጽሑፍ ላይ ከ10-17 ባሉት አንቀጾች ላይ የተመረኮዘ በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት።
መዝሙር 123 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መስከረም 16 የሚጀምር ሳምንት
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። እንዲሁም ከነሐሴ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ክፍል አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “በንግግራችሁና በጠባያችሁ ምሳሌ ሁኑ።” ጥያቄና መልስ።
15 ደቂቃ፦ በትምህርት ቤት ክርስቲያናዊ ጠባይ ማሳየት። አንድ አባት ከወንድ ወይም ከሴት ልጁ ጋር በትምህርት ቤት አካባቢ ስላሉት አንዳንድ አደገኛ ወጥመዶች እያነሳ ይወያያል፤ በውይይቱ ውስጥ በባልንጀራ ምርጫና አጠያያቂ በሆኑ እንቅስቃሴዎች መካፈልን በተመለከተ ጠንቃቃ የመሆንን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርጎ ይገልጻል። ትምህርት ቤት በተባለው ብሮሹር ከገጽ 9 ንዑስ ርዕስ እስከ ገጽ 11 ንዑስ ርዕስ ያሉትን ነጥቦች ይከልስና ምሥክር እንደመሆኑ [እንደመሆኗ] መጠን ጥሩ ምሳሌ መሆኑ [መሆኗ] ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይገልጻል። አባት ዕፅ መውሰድን፣ ከተቃራኒ ጾታ ጋር መቀጣጠርን፣ በግብዣዎቻቸው ላይ መገኘትን ወይም በስፖርት መካፈልን የመሳሰሉትን ሊነሡ የሚችሉ ፈታኝ ሁኔታዎች ከጠቃቀሰ በኋላ ችግሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ይወያያሉ። አባት ወጣት ልጁ ችግር ሲገጥመው ቶሎ እንዲነግረው በማበረታታት ችግር ካለ ችግሩን አውቆ ሊረዳው እንደሚፈልግ ይገልጽለታል።
መዝሙር 32 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መስከረም 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 172
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በተጨማሪም “የማኅበሩን ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ለመደገፍ የሚደረገው መዋጮ ለሥራው መስፋፋት እገዛ ያደርጋል” የሚለውን ርዕስ ሸፍን።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። (በየካቲት 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 27-9 ላይ በሚገኘው “ከምታያቸው ነገሮች ባሻገር ተመልከት!” በሚለው ርዕስ ላይ ወይም በ14-110 መጠበቂያ ግንብ “አኗኗርህ ሚዛናዊና ቀላል ይሁን” በሚለው ርዕስ ላይ የተመሠረተ መንፈሳዊ ሰዎች መሆንን ጠበቅ አድርጎ የሚገልጽ ንግግር ይቀርባል።)
20 ደቂቃ፦ “በማንኛውም ቦታ ምሥራቹን ስበኩ” ጥያቄና መልስ። ከአንቀጽ 1-15 ያሉትን ብቻ ሸፍን። ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎችን አክልበት።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት
መስከረም 30 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 29
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥኑን በውይይት አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “በማንኛውም ቦታ ምሥራቹን ስበኩ።” ጥያቄና መልስ። ከአንቀጽ 16-27 ያለውን ሸፍን። የቀረቡትን ሐሳቦች ጉባኤው እንዴት ሊሠራባቸው እንደሚችል ግለጽ። ከ18-20 ያሉትን አንቀጾች በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አንቀጽ 26, 27ን አንብብ።
13 ደቂቃ፦ በጥቅምት ወር የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እናበረክታለን። ኮንትራትም ልናስገባ እንችላለን። እንደሚከተሉት ያሉትን የተለያዩ ነጥቦች አብራራ:- (1) በመጀመሪያዎቹ ገጾች ላይ የተጠቀሰውን መጽሔቶቹ የሚታተሙበትን ዓላማ (2) በብዙ ቋንቋዎች የሚታተሙ በመሆናቸው የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት በዓለም ዙሪያ ለማሠራጨት እንደሚያገለግሉ (3) የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የሚዘጋጀው በግል፣ በቤተሰብና በቡድን ሆኖ ለማጥናት እንዲያመች ተደርጎ እንደሆነ (4) በተለያዩ ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ሰዎች እንደሚያነቧቸው (5) ማንበብ ለሚፈልጉ ሰዎች አዲስ የሚወጡትን ቅጂዎች በግላችን እንደምናሠራጭ (6) በተለይ ሥራ የሚበዛባቸውን ሰዎች ለመርዳት ታስበው የተዘጋጁ እንደሆኑ (7) መጠበቂያ ግንብ ከ1879 ጀምሮ፣ ንቁ! ደግሞ ከ1919 ጀምሮ ሲታተሙ እንደቆዩ ግለጽ። ለመጽሔቱ አድናቆት ያለው አንድ ሰው የሰነዘረውን አስተያየት በመጥቀስ ደምድም።— ሚያዝያ 15, 1986 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32ን ተመልከት።
መዝሙር 47 እና የመደምደሚያ ጸሎት።