ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ጥር፦ በጉባኤ ውስጥ ያለ ከ1984 በፊት የታተመ ማንኛውም 192 ገጽ ያለው መጽሐፍ። እነዚህ መጻሕፍት የሌሏቸው ጉባኤዎች በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት የተሰኘውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የካቲት፦ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም በጥር ወር ከሚበረከቱት መካከል ያላለቁት ጽሑፎች። መጋቢት፦ ደስተኛ ቤተሰብ የሚገኝበት ምስጢር የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ወይም እውቀት የተባለው መጽሐፍ። ሚያዝያ፦ የመጠበቂያ ግንብ ወይም ንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። በተደጋጋሚ በተሸፈኑ የአገልግሎት ክልሎች ውስጥ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተሰኘው አዲስ ብሮሹር መጠቀም ይቻላል።
◼ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሙያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ካርድ ጥር 6 በሚጀምረው ሳምንት በሚደረገው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለተገኙት ለተጠመቁ አስፋፊዎች በሙሉ ይታደላል። ለልጆቻቸው ደግሞ መታወቂያ ካርዱ ይሰጣል።
◼ ከየካቲት ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር ጭብጥ “ትምህርትን ይሖዋን ለማወደስ ተጠቀሙበት” የሚል ይሆናል።
◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት እሑድ መጋቢት 23 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የመታሰቢያ በዓል አመቺ የሆኑ ዝግጅቶችን ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳን ንግግሩን ቀደም ብሎ ማቅረብ ቢቻልም የመታሰቢያውን ቂጣና ወይን ጠጅ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ማዞር አይቻልም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቀው በስንት ሰዓት እንደሆነ አቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። በዚህ ቀን ለመስክ አገልግሎት ከሚደረገው ስብሰባ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ስብሰባ ስለማይደረግ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት በሌላ ጊዜ እንዲመራ አመቺ የሆነ ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል። የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በዚያ ሳምንት በሚያደርጉት የስብሰባ ፕሮግራም ላይ የአካባቢው ሁኔታ በሚፈቅደው መንገድ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳ እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ቢያከብር የሚመረጥ ቢሆንም ሁልጊዜ እንዲህ ማድረግ አይቻል ይሆናል። በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች የሚጠቀሙ ከሆነ ምናልባት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት የሚሆን ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በበዓሉ ላይ ለመገኘት እንዳይቸገሩ የመታሰቢያው በዓል የሚጀምረው በጣም ከመሸ በኋላ መሆን የለበትም። ከበዓሉ በፊት ወይም በኋላ ከአንዳንዶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ፣ ለአንዳንዶች ቀጣይ የሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ለማድረግ ወይም እዚያ የተገኙት ሁሉ እርስ በርስ ማበረታቻ ለመለዋወጥ እንዳይችሉ እስኪያደርግ ድረስ ፕሮግራሙ በጣም የተጣበበ መሆን የለበትም። ሽማግሌዎች ሁሉንም ነገር በደንብ ካጤኑ በኋላ በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙት ሁሉ በአጋጣሚው ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንዲችሉ ምን ዝግጅት ቢያደርጉ የተሻለ እንደሚሆን መወሰን አለባቸው።
◼ በ1997 በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር እሑድ ሚያዝያ 6 ይሰጣል። የንግግሩ አስተዋፅዖ ይላክላችኋል። በዚህ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት፣ የወረዳ ስብሰባ ወይም የልዩ ስብሰባ ቀን ያላቸው ጉባኤዎች በቀጣዩ ሳምንት ልዩ ንግግሩን ያቀርቡታል። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 6 በፊት ልዩ ንግግሩን ማቅረብ አይችልም።
◼ ጉባኤዎች የወረዳ ስብሰባና የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም በሚኖራቸው ጊዜ የሽማግሌዎች አካል የሚከተለውን ማስተካከያ ለማድረግ ንቁ መሆን ይኖርበታል:- የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም በሚደረግበት ጊዜ ጉባኤዎች በሳምንቱ ውስጥ የሚያደርጉትን የተለመዱትን ስብሰባዎች ያከናውናሉ። የሕዝባዊ ስብሰባና የመጠበቂያ ግንብ ጥናት ግን ይሰረዛሉ። የወረዳ ስብሰባ በሚደረግበት ጊዜ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ስብሰባና የአገልግሎት ስብሰባ የሚሰረዙ ሲሆን በዚያው ሳምንት የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ብቻ ይደረጋል።
◼ ከካናዳ ሰባት ሰዎች በቡድን በሚገቡት በአየር የሚላክ ኮንትራት ዋጋ ላይ የተደረገ ማስተካከያ:- ለአንድ ዓመት ኮንትራት አስፋፊ ብር 64.50፤ አቅኚ ብር 52
◼ በዚህ ዓመት ለሚደረገው “በአምላክ ቃል ላይ መታመን” ለተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ የወጣ ሊለወጥ የሚችል ፕሮግራም:- መስከረም 19-21:- ድሬዳዋ፤ መስከረም 26-28:- አዋሳ ወይም ሻሸመኔ፤ ጥቅምት 3-5:- ደሴ፤ ጥቅምት 10-12:- ጅማ፤ ጥቅምት 17-19 እና 24-26:- አዲስ አበባ።
◼ ቀደም ብሎ ዝግጅት ለማድረግ እንዲረዳ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ቀን እናሳውቃችኋለን:- እሁድ መጋቢት 23, 1997፤ ቅዳሜ ሚያዝያ 11, 1998 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ።
◼ በዚህ ዓመት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ለሚደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ጥሩ የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ ያላቸው አቅኚዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ማመልከቻቸውን አሁንኑ ወይም እስከ ጥር 20, 1997 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ለሚከተሉት መጠይቆች አጠር ያለ ማብራሪያ ያስፈልገናል:- 1. ስም፤ 2. ጉባኤ፤ 3. ዕድሜ፤ 4. ጥምቀት፤ 5. ነጠላ ወይም ያገባ፤ 6. የሚያውቋቸው ቋንቋዎች፤ 7. ከጥቅምት እስከ ታኅሣሥ 1996 ድረስ ያለው የአገልገሎት ሪፖርት ግልባጭ፤ 8. አመልካቹ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት ያለው ችሎታ፤ 9. የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ የፈረመበት አጭር አስተያየት።
◼ በቅርቡ የሚደርሱን ጽሑፎች:- አረብኛ፦ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፤ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? እንግሊዝኛ፦ የ1997 የቀን መቁጠሪያ።
◼ በቅርቡ የሚደርሱን ሌሎች ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ፦ ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?፤ ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ የተባለውን መጽሐፍ 8 ክሮች የያዘ አልበም።