የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ጥር 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 10
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በአገሪቱና በጉባኤው የጥቅምት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ላይ ሐሳብ ስጥ።
20 ደቂቃ:- በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ካርድ የሚታደስበት ጊዜ አሁን ነው። ካርዱን ሙሉ በሙሉ የመሙላትና ሁልጊዜ የመያዝን አስፈላጊነት ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ በውይይት ያቀርበዋል። በአደጋ ጊዜ ስለ አቋማችሁ ማብራራት ቢያቅታችሁ ይህ ሰነድ እንደ እናንተ ሆኖ ይናገራል። (ከምሳሌ 22:3 ጋር አወዳድር።) ከተሞላ አንድ ዓመት ያለፈው ሰነድ አንዳንድ ዶክተሮችንና ሌሎች ሰዎችን ግለሰቡ በአሁኑ ጊዜ ያለውን የጸና አቋም ላይገልጽ ይችላል ወደሚል መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ደም መውሰድ እንደማትፈልጉ የሚያረጋግጥ አዲስ ካርድ በየዓመቱ መሞላት ይኖርበታል። ከስብሰባው በኋላ በቅድሚያ የተሰጠ የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርገው ካርድ ለሁሉም የተጠመቁ አስፋፊዎች ይታደላል። እንዲሁም ላልተጠመቁ ትንንሽ ልጆች የመታወቂያ ካርድ ይሰጣል። እነዚህን ካርዶች ስብሰባው ላይ መሙላት እንደሌለባቸው ግለጽ። እቤት ከሄዱ በኋላ ፊርማቸውን ሳያሰፍሩ በጥንቃቄ ይሞላሉ። በሁሉም ካርዶች ላይ የሚፈረመው፣ የምሥክሮች ስምና ቀን የሚሞላው በመጽሐፍ ጥናቱ መሪ የበላይ ተቆጣጣሪነት በሚቀጥለው የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ ይሆናል። እርሱም በቡድኑ ውስጥ ያሉት ሁሉ ካርዱ እንደደረሳቸውና ተገቢው እርዳታ ማግኘታውን ያረጋግጣል። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙት የካርዱ ባለቤት በሰነዱ ላይ ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። በመጽሐፍ ጥናቱ ስብሰባ ላይ ሳይገኝ የቀረ ካለ በመጽሐፍ ጥናት መሪዎች/በሽማግሌዎች እርዳታ በሚቀጥለው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ ካርዱን እንዲሞላ ይደረጋል። በዚህ መንገድ ሁሉም የተጠመቁ አስፋፊዎች በሚገባ የተሞላና የተፈረመበት ካርድ እስኪኖራቸው ድረስ የመጽሐፍ ጥናት መሪዎች/ሽማግሌዎች እርዳታ መስጠታቸውን ይቀጥላሉ። (የጥቅምት 15, 1991 ደብዳቤ ከልስ።) ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከዚህ ካርድ ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የራሳቸውን መመሪያ ሊያዘጋጁ ይችላሉ።—ምሳሌ 16:20
15 ደቂቃ:- “ሌሎችን ለማስተማር ብቁና የታጠቁ መሆን።” በአንቀጽ 1-2 ላይ የተመሠረተ አጠር ያለ ሐሳብ ከሰጠህ በኋላ በይሖዋ እርዳታ ውጤታማ በሆነ መንገድ ሌሎችን ማስተማር እንደምንችል በራሳችን የመተማመን መንፈስ የመያዝን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ከአንቀጽ 3-6 ባለው አቀራረብ ተጠቅመው ሁለት አስፋፊዎች ከሁለት የቤት ባለቤቶች ጋር አንድን ሰው በመጀመሪያ ማነጋገርና ተመላልሶ መጠየቅ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲያቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 33 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19
15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በቅርብ ከወጡ መጽሔቶች መካከል ውይይት ለመክፈት የሚረዱ ነጥቦችን አቅርብ። መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመስከር ሰዎችን በምንቀርብበት ጊዜ ራሳችንን እንዴት አድርገን ማስተዋወቅ እንደምንችል የሚገልጹ ሐሳቦች አቅርብ። በሱቆች፣ በመንገድ ላይ፣ በመናፈሻዎች፣ በሕዝብ መጓጓዣዎችና በሌሎች ቦታዎች ሰዎችን ለማነጋገር ምን ዓይነት የመግቢያ ቃላት እንደሚጠቀሙ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
15 ደቂቃ:- ‘እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ እወቁ።’ (ቆላ. 4:6) “ማመራመር ” ከተባለው መጽሐፍ በተለይ ከገጽ 16-19 ላይ ከሰፈሩት መካከል በአገልግሎት ክልላችሁ ውስጥ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ ነጥቦችን ተወያዩ። እነዚህን ነጥቦች ጥሩ ችሎታ ያለው አስፋፊ ወይም አቅኚ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ወይም “ሸክማችሁን ምን ጊዜም በይሖዋ ላይ ጣሉ።” በሚያዝያ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 27-9 ላይ ባለው ሐሳብ የተመሠረተ አበረታች የሆነ ንግግር አቅርብ።
መዝሙር 6 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 8
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት በመጋቢት ወር በዛ ያሉ አስፋፊዎች ረዳት አቅኚ ሆነው ለማገልገል ጥረት አንዲያደርጉ አሳስብ። ዛሬውኑ ቅጽ ወስደው ሁኔታዎቻቸውን ማደራጀት እንዲጀምሩ ጋብዛቸው።
15 ደቂቃ:- “ሁሉም ዓይነት ሰዎች ይድናሉ።” ጥያቄና መልስ። የተለያየ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ሰዎች ጋር ውይይት አድርገው ጥሩ ምላሽ ያገኙት እንዴት እንደሆነ የሚገልጹ አንዳንድ ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- በጥሩ ጠባይ መመሥከር። አንድ ሽማግሌ ከሁለት ወይም ከሦስት ወጣቶች ጋር ውይይት ያደርጋል። በ16-108 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 3-15 ባለው ሐሳብ ላይ የተመሠረተ ይሆናል። ክርስቲያን ወጣቶች ባሳዩት ጥሩ ምግባር ተመልካቾች እንዴት እንደተነኩ የሚጠቁሙ ከጽሑፎችም ሆነ ከጉባኤው የተገኘ ተሞክሮዎችን አክለህ አቅርብ።
መዝሙር 26 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 175
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በጸሐፊው የሚከለስ።
15 ደቂቃ:- ‘ቃሉን እንሰብካለን።’ ጥያቄና መልስ። የአምላክ ቃል የሚሰጠውን ጥቅም ከፍ አድርገን የምንመለከተው ለምን እንደሆነ የሚገልጹ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።—መጋቢት 22, 1984 የእንግሊዝኛ ንቁ! ከገጽ 9-11 ተመልከት።
15 ደቂቃ:- በየካቲት የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። የመጽሐፉን አንዳንድ ማራኪ ገጽታዎች ጠቁም። (1) በሕይወት መትረፍ ከተሰኘው መጽሐፍ ምዕራፍ 3, 4, 7 ላይ ያሉት ፍላጎት የሚያነሳሱ ርዕሶች፣ (2) ልብ የሚነኩ ምሳሌዎች፣ (3) በሕይወት መትረፍ በተሰኘው መጽሐፍ በገጽ 5, 27, 95, 135 ወይም 172 ላይ እንደሚገኙት ያሉ የማስተማሪያ ሥዕሎች ወይም ሰንጠረዞች፣ (4) በሕይወት መትረፍ በተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 87 ላይ እንደሚገኘው 15ኛ ጥያቄ ላይ ያሉት አመራማሪ ጥያቄዎች። ቀደም ባለው ክፍል ላይ እንደተብራራው ታስቦባቸው የተመረጡ ጥቅሶችን በመግቢያ ላይ የመጠቀምን አስፈላጊነት አበረታታ። አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።