የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/97 ገጽ 1
  • ወደፊት በማይደገመው ሥራ ተካፈል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደፊት በማይደገመው ሥራ ተካፈል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ የፍርድ እርምጃ ሲወስድ ሁልጊዜ በቂ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ታላቁን መከራ በሕይወት ማለፍ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ከምንጊዜውም በበለጠ ነቅተን እንጠብቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 2/97 ገጽ 1

ወደፊት በማይደገመው ሥራ ተካፈል

1 በሰው ዘር ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች ይሖዋ በጠላቶቹ ላይ የጥፋት ፍርዱን ማስፈጸም አስፈልጎት ነበር። ይሁን እንጂ በምሕረቱ ቅን የሆኑ ሰዎች ደህንነት የሚያገኙበትን አጋጣሚ አዘጋጅቶላቸዋል። (መዝ. 103:​13) የሚሰጡት ምላሽ የመጨረሻ ዕጣቸውን ይወስን ነበር።

2 ለምሳሌ ያህል የጥፋት ውኃ ከመምጣቱ ቀደም ብሎ በ2370 ከአዘበ ኖኅ ‘ጽድቅን ይሰብክ’ ነበር። ጥፋት የደረሰባቸው መለኮታዊውን ማስጠንቀቂያ ለመከተል ቸል ያሉት ናቸው። (2 ጴ⁠ጥ. 2:​5፤ ዕብ. 11:​7) ኢየሩሳሌም በ70 እዘአ ከመጥፋቷ በፊት ኢየሱስ ከተማዋ ላይ ከሚደርሰው ጥፋት ለመዳን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ሊወስድ የሚገባውን እርምጃ በግልጽ ዘርዝሯል። እርሱ የሰጠውን የማስጠንቀቂያ መልእክት ለመከተል አሻፈረኝ ያሉ ሁሉ በመጨረሻው ጥፋት ደርሶባቸዋል። (ሉቃስ 21:​20-24) እንደነዚህ ያሉት መለኮታዊ ማስጠንቀቂያዎችና ፍርዶች በታሪክ ዘመናት ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜያት ተፈጽመዋል።

3 በዘመናችን እየተከናወነ ያለ የማስጠንቀቅ ሥራ:- ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ ባለው ክፉ ሥርዓት ላይ ቁጣውን እንደሚያወርድና ከዚህም ጥፋት በሕይወት የሚተርፉት ገሮች ብቻ እንደሆኑ ከረዥም ጊዜ በፊት አስታውቋል። (ሶፎ. 2:​2, 3፤ 3:​8) ይህ የማስጠንቀቂያ መልእክት የሚሰበክበት ጊዜ እየተሟጠጠ ነው! “ታላቁ መከራ” በጣም ቀርቧል፤ ገሮችም እየተሰበሰቡ ነው። በእርግጥም ‘አዝመራው ነጥቶ ለአጨዳ’ ደርሷል። ስለሆነም በአስፈላጊነቱና በአጣዳፊነቱ ከዚህ ሥራ ጋር ሊወዳደር የሚችል ምንም ዓይነት ሥራ የለም።​— ማቴ. 24:​14, 21, 22፤ ዮሐ. 4:​35

4 ሰዎች “ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ” በዘመናችን በሚሰጠው የማስጠንቀቅ ሥራ ተካፋይ መሆን አለብን። ይህ ችላ ልንለው የማይገባን አምላክ የሰጠን ሥራ ነው። (ሕዝ. 2:​4, 5፤ 3:​17, 18) በዚህ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተካፋይ መሆናችን ለአምላክ የጠለቀ ፍቅር እንዳለን፣ ለጎረቤቶቻችን ልባዊ አሳቢነት እንደምናሳይና አዳኛችን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጽኑ እምነት እንዳለን የምናሳይበት መንገድ ነው።

5 ለሥራ የምንቀሳቀስበት ጊዜ አሁን ነው:- ይሖዋ በቀድሞ ጊዜያት ፍርዶቹን ካስፈጸመ በኋላ ሰይጣንና አጋንንቱ ከክፉ ሥራቸው ባለመታቀባቸው ምክንያት ሁልጊዜ ክፋት እንደገና ብቅ ማለቱ አልቀረም። ይሁን እንጂ ይሖዋ ወደፊት ፍርዱን በሚያስፈጽምበት ጊዜ ሁኔታው ከዚህ የተለየ ይሆናል። የሰይጣን ተጽዕኖ ይወገዳል። በዓለም ዙሪያ እንደገና “ታላቁ መከራ” ይመጣል የሚል ማስጠንቀቂያ ማሰማት ጨርሶ አስፈላጊ አይሆንም። (ራእይ 7:​14፤ ሮሜ 16:​20) ወደፊት በማይደገመው ሥራ ተካፋይ የመሆን ልዩ መብት አለን። ይህን አጋጣሚ የተቻለንን ያህል የምንጠቀምበት ጊዜ አሁን ነው።

6 ሐዋርያው ጳውሎስ የአገልግሎቱን እንቅስቃሴ አስመልክቶ “ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ” ነኝ በማለት በእርግጠኝነት ሊናገር ችሏል። (ሥራ 20:​26) ማስጠንቀቂያውን ሳያሰማ በመቅረቱ የደም ዕዳ እንዳለበት አልተሰማውም። ለምን? ምክንያቱም አገልግሎቱን አስመልክቶ “እየተጋደልሁ፣ እደክማለሁ” ብሎ መናገር ስለቻለ ነው። (ቆላ. 1:​29) እኛም ወደፊት በማይደገመው ሥራ የቻልነውን ያህል ሙሉ በሙሉ ተካፋይ በመሆን ተመሳሳይ የሆነ እርካታ እናግኝ!​—2 ጢ⁠ሞ. 2:​15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ