የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/97 ገጽ 1
  • የእናንተስ ዘመዶች?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የእናንተስ ዘመዶች?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለዘመዶቻችን ምሥራቹን እንዴት መንገር እንችላለን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • የማያምኑ ዘመዶቻችንን ልብ መንካት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ሰላምን ሳይሆን ሰይፍን የሚያመጣው እውነት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • “የሚሰሙህ” ሰዎች ይድናሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 2/97 ገጽ 1

የእናንተስ ዘመዶች?

1 ብዙዎቻችን በእውነት ውስጥ የማይገኙ ብዙ ዘመዶች አሉን። እነኚህ የምንወዳቸው ሰዎች በሕይወት ጎዳና ላይ አብረውን እንዲጓዙ ምንኛ እንመኝ ይሆን! እነዚህ ሰዎች የቤተሰባችን አባላት ከሆኑ ደግሞ ስለ ዘላለማዊ ደህንነታቸው ያለን አሳቢነት ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል። ምንም እንኳ ለረዥም ዓመታት ወደ እውነት እንዲመጡ የጣርን ቢሆንም ሁኔታው ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ አድርገን መደምደም አይኖርብንም።

2 ኢየሱስ ስብከቱን ባከናወነበት ጊዜ “ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም” ነበር። (ዮሐ. 7:​5) እንዲያውም በአንድ ወቅት ዘመዶቹ ያበደ መስሏቸው ነበር። (ማር. 3:​21) ኢየሱስ ግን ተስፋ ቆርጦ አልተዋቸውም። ውሎ አድሮ ወንድሞቹ እውነትን ተቀብለዋል። (ሥራ 1:​14) ግማሽ ወንድሙ ያዕቆብ የክርስቲያን ጉባኤ አዕማድ ሆኗል። (ገላ. 1:​18, 19፤ 2:​9) አንተም ዘመዶችህ እውነትን ተቀብለው ማየት የምትፈልግ ከሆነ የመንግሥቱን ምሥራች ለእነርሱ ከመንገር ወደኋላ ማለት አይኖርብህም።

3 መንፈሳቸውን አነቃቁ እንጂ ሐሳብ በማብዛት አታስጨንቋቸው:- ኢየሱስ ለሌሎች በሚሰብክበት ጊዜ የአድማጮቹን መንፈስ ያነቃቃ ነበር። (ማቴ. 11:​28, 29) ሊጨብጡት ከሚችሉት በላይ ትምህርት በማዥጎድጎድ አላስጨነቃቸውም። ዘመዶችህን በእውነት ውኃ ለማርካት በአንድ ጊዜ አንድ ባልዲ ውኃ ሳይሆን አንድ ብርጭቆ ውኃ ብቻ ስጣቸው! አንድ ተጓዥ የበላይ ተመልካች “የተሻለ ውጤት የሚያገኙት ትንሽ እየመሰከሩ የዘመዶቻቸውን የማወቅ ፍላጎት የሚቀሰቅሱት ናቸው” በማለት ተናግሯል። በዚህ መንገድ ተቃዋሚዎችም እንኳን ሳይቀሩ ጥያቄ መጠየቅ ይጀምሩና ውሎ አድሮ ለእውነት ያላቸው ጥማት እያደገ ይሄዳል።​— 1 ጴ⁠ጥ. 2:​2፤ ከ1 ቆ⁠ሮንቶስ 3:​1, 2 ጋር አወዳድር።

4 ብዙ ያገቡ ክርስቲያኖች ፍላጎታቸውን ይቀሰቅስ ይሆናል ብለው ያሰቡትን ጽሑፍ ገልጠው በማስቀመጥ አጥጋቢ በሆነ መንገድ ለማያምነው የትዳር ጓደኛቸው መስክረዋል። እንዲህ ያደረገች አንዲት እህት ከዚህ በተጨማሪ ባሏ ሊሰማት በሚችል መንገድ እርሱን የሚነካውን ማብራሪያ ጮክ ብላ በመናገር ልጆቿን ታስጠና ነበር። አንዳንድ ጊዜም “ዛሬ ባደረግሁት ጥናት ይህንና ይህን የመሳሰሉ ጉዳዮችን ተምሬአለሁ። ስለዚህ ጉዳይ አንተስ ምን ይመስልሃል?” ብላ ትጠይቀው ነበር። በመጨረሻ ባሏ እውነትን ተቀበለ።

5 አክብሮትና ትዕግሥት ይኑራችሁ:- አንዲት አስፋፊ “ዘመዶቻችሁም የራሳቸው የሆነ አመለካከትና አስተያየት የመከተል መብት አላቸው” በማለት ገልጻለች። ስለዚህ ሐሳባቸውን በሚገልጹበት ጊዜ ወይም እውነትን አስመልክቶ ምንም ዓይነት ውይይት ከእነርሱ ጋር እንዳናደርግ በቀጥታ በሚጠይቁን ጊዜ አክብሮት ማሳየት ይገባናል። (መክ. 3:​7፤ 1 ጴ⁠ጥ. 3:​15) ታጋሽና አፍቃሪ እንዲሁም ጥሩ አድማጭ በመሆን ጥሩ ምስክርነት ለመስጠት የሚያስችል አመቺ የሆነ ጊዜ ልንጠብቅ እንችላለን። እንዲህ ያለው ታጋሽነት አማኝ ካልሆነች ሚስቱ ለ20 ዓመታት ይደርስበት የነበረውን ተቃውሞ በትዕግሥት ችሎ እንዳሳለፈው አንድ ክርስቲያን ባል ጥሩ ውጤት ሊያስገኝ ይችላል። ለውጥ ማድረግ በጀመረች ጊዜ እንዲህ አለ:- “ይሖዋ ቻይነትን እንዳዳብር ስለረዳኝ በጣም አመሰግነዋለሁ፤ ምክንያቱም አሁን ውጤቱን ማየት ችያለሁ:- ሚስቴ በሕይወት ጓዳና ላይ መጓዝ ጀምራለች!”

6 የእናንተስ ዘመዶች? በምታሳዩት ጥሩ ክርስቲያናዊ ጠባይና ስለ እነርሱ በምታቀርቡት ጸሎት አማካኝነት “ይሖዋን እንዲያመልኩ ልታደርጓቸው ትችላላችሁ።”​— 1 ጴ⁠ጥ. 3:​1, 2 የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ