የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች
የካቲት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 113
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “ወደፊት በማይደገመው ሥራ ተካፈል።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አዋጅ ነጋሪዎች ከተሰኘው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ገጽ 714-15 ላይ ያለውን “ነቅቶ መጠበቅ የሚቻለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “በጥድፊያ ስሜት ምሥራቹን ማቅረብ።” (ከአንቀጽ 1-5) ሊቀ መንበሩ በአንቀጽ 1 ላይ የተመሠረተ አጭር ሐሳብ ካቀረበ በኋላ ከአንቀጽ 2-5 ያለውን ከሁለት ወይም ከሦስት አስፋፊዎች ጋር በውይይት ያቀርበዋል። በቀረቡት መግቢያዎች ውስጥ የሚገኙትን ዋና ዋና ነጥቦች ይጠቅሱና እነዚህ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ መግቢያዎች በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውስጥ ውጤታማ የሚሆኑበትን ምክንያት አስመልክቶ ሐሳብ ይሰጣሉ። አስፋፊዎቹ ተራ በተራ ሠርቶ ማሳያዎች በማቅረብ ይለማመዳሉ። ሊቀ መንበሩ ካመሰገናቸው በኋላ የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ መግቢያዎቹን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ሐሳብ ይሰጣል። ከዚያም ጥናት የማስጀመር ግብ ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ መንገዶች ምን እንደሆኑ አድማጮችን ይጠይቃል። እውቀት በተሰኘው መጽሐፍ አማካኝነት ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል ግልጽ የሆነ ሐሳብ ይሰጣል።
መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 10 የሚጀምር ሳምንት
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
10 ደቂቃ:- “በጥድፊያ ስሜት ምሥራቹን ማቅረብ።” (ከአንቀጽ 6-8) በአንቀጽ 6 እና 7 ላይ የተመሠረቱ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ተመላልሶ መጠየቅ የማድረግን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
30 ደቂቃ:- “1, 000 ረዳት አቅኚዎች ይፈለጋሉ።” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በጥያቄና መልስ ይሸፍነዋል። ገጽ 3 ላይ ያለውን ሣጥን ጎላ አድርገህ ግለጽ። ገጽ 10 ላይ እንደ ናሙና ሆነው የቀረቡትን ፕሮግራሞች ከልስ። እያንዳንዱ የተጠመቀ አስፋፊ አንድ ወር ወይም ከዚያ በላይ ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል ይችል እንደሆነ በጸሎት ሊያስብበት ይገባል። ያልተጠመቁ አስፋፊዎችም በእያንዳንዱ ወር የራሳቸውን የሰዓት ግብ በማውጣት በአገልግሎት ያላቸውን ተሳትፎ ከፍ ሊያደርጉ ይችላሉ። በተጨማሪም ያልተሠራባቸውን የአገልግሎት ክልሎች ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ለመሸፈን ጉባኤው ያወጣውን እቅድ ጥቀስ።
መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 17 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በዚህ ሳምንት በሚደረገው አገልግሎት ላይ ሊጠቅሙ የሚችሉ በቅርቡ ከወጡ መጽሔቶች ላይ አንዳንድ ትኩረት የሚስቡ ነጥቦችን ተናገር።
13 ደቂቃ:- “ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው የመታሰቢያው በዓል!” ጥያቄና መልስ። በመጋቢት ወር በረዳት አቅኚነት አገልግሎት በመሳተፍ ወሩን በጠቅላላ በልዩ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ማበረታቻ ስጥ። የመታሰቢያውን በዓል የግብዣ ወረቀት የመጠቀምን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
22 ደቂቃ:- የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። በቅርብ ወራት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ መጻሕፍት ተበርክተዋል። ይህም ተጨማሪ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር መሠረት ጥሏል። መጻሕፍትንና ሌሎች ጽሑፎችን በማበርከት በኩል ጉባኤው ምን እንዳከናወነ በአጭሩ ጥቀስ። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ክትትል እንዲያደርጉላቸው አስፋፊዎችን አበረታታ። አዲስ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር በግል ምን ዓይነት ልዩ ጥረት መደረግ እንደሚኖርበት በርከት ያሉ አስፋፊዎች እንዲናገሩ አድርግ። ደቀ መዛሙርት ማድረግ የተልእኳችን ዓይነተኛ ክፍል መሆኑን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። (ማቴ. 28:19, 20) በሰኔ 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ አባሪ ሆኖ የወጣውን ሐሳብ በሥራ ላይ ለማዋል የምንጣጣር ከሆነ ይህ አጥጋቢ በሆነ መንገድ ሊከናወን ይችላል።
መዝሙር 47 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 24 የሚጀምር ሳምንት
18 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በመጋቢት ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉትን ስም ዝርዝር ተናገር። አሁንም ቢሆን ማመልከቻ ለማስገባት ጊዜው እንዳላለፈ ግለጽ። ቅዳሜ መጋቢት 1 ሁሉም በመስክ አገልግሎት የተሟላ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታ። በዚህ ወር በጉባኤው ውስጥ ተጨማሪ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች ለማድረግ የወጣውን ዝግጅት ግለጽ። የጥያቄ ሣጥኑን በጥንቃቄ ከልስ።
12 ደቂቃ:- “የእናንተስ ዘመዶች?” አንድ ባልና ሚስት ክፍሉን ይወያዩና ለማያምኑ ዘመዶቻቸው ምሥራቹን እንዴት እንደሚያቀርቡ መደምደሚያ ላይ ይደርሳሉ።— መጠበቂያ ግንብ 4-111 ገጽ 19-21 ተመልከት።
15 ደቂቃ:- በመጋቢት የሚበረከቱት ጽሑፎች የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር የተሰኘው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው የተሰኘው የአማርኛ መጽሐፍ መሆናቸውን ግለጽ። በዚህ ዘመናዊ በሆነው ኅብረተሰብ ለሚደርሰው የቤተሰብ መፈራረስ መንስኤ የሆኑት ነገሮች ምን እንደሆኑ በአጭሩ ግለጽ። (ጥቅምት 15, 1992 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 4-7 ተመልከት።) ገጽ 3 ላይ የሚገኘውን የመጽሐፉን ማውጫ አንብብ። ለመግቢያ የሚያገለግል አንድ ምዕራፍ እንዲመርጡ አድማጮችን ጋብዝ። መጽሐፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ብቃት ያለው አንድ ወንድም ሠርቶ ማሳያ ያቅርብ። ሁሉም አስፋፊዎች ቅዳሜና እሑድ በሚደረገው አገልግሎት እንዲጠቀሙበት የዚህን መጽሐፍ ቅጂ እንዲወስዱ አሳስብ።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።