ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- መጋቢት እና ሚያዝያ:- የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች ግንቦት፣ ሰኔ እና ሐምሌ:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ በዚህ ዓመት በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር በአብዛኞቹ ጉባኤዎች እሁድ ሚያዝያ 6 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ “ከዓለም ዕድፍ ራሳችሁን ጠብቁ” የሚል ነው። ሁላችንም በስብሰባው ላይ መገኘት ይኖርብናል፤ ከዚህም በላይ በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ለዚህ ንግግር እንዲመጡ ልንረዳቸው ይገባል። የምናገኘው ትምህርት አምላክን ለማስደሰት ያለንን የቁርጠኝነት ስሜት ይበልጥ የሚያጠናክርልን ነው።
◼ በየአገሩ በዓመት ውስጥ በተለያየ ወቅት ዓለማዊ በዓላት ሲከበሩ ተማሪዎች ከትምህርት ነፃ ይሆናሉ፤ ሠራተኞችም ዕረፍት ያገኛሉ። ይህም ጉባኤው በመስክ አገልግሎት የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ግሩም አጋጣሚ ነው። ሽማግሌዎች እነዚህን አጋጣሚዎች በመከታተል በበዓላቱ ቀናት ለሚከናወነው የቡድን ምሥክርነት የተደረጉትን ዝግጅቶች አስቀድመው ለጉባኤው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
◼ በ113 ካሴቶች ላይ የተቀዳው የመንግሥቱ መዝሙር ጥቂት ቅጂዎች ይቀሩናል። አሁን 100 መዝሙሮችን የያዘ የአማርኛ መዝሙር መጽሐፍ ስላገኘን ይህ ለጉባኤዎች ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል። እያንዳንዱ ካሴት በፊትና ጀርባ አንድ አንድ መዝሙር ብቻ ይዟል። ይህ በተለይ መዝሙር የሚያስተካክሉትን ወንድሞች ሥራ ያቀላጥፋል። የዚህ መዝሙር (Lsb-cs) ዋጋ ብር 483 ነው።
◼ በመጽሔት መያዣ ማኅደር ዋጋ ላይ ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን ብር 33 ሆኗል።
◼ ከጥር 20 ጀምሮ የሚደርሱን ጽሑፎች:-
እንግሊዝኛ፦ የ1986 መጠበቂያ ግንብ ጥራዞች፤ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፤ በኮምፓክት ዲስክ የተቀረጸ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የ1995 ቤተ መጻሕፍት፤ የ1997 የቀን መቁጠሪያ።
አማርኛ፦ የውዳሴ መዝሙሮች (100 መዝሙሮች)፤ ቅዱሳን ጽሑፎችን መመርመር 1997
አረብኛ፦ የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር፤ የይሖዋ ምሥክሮችና ትምህርት፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ፈረንሳይኛ፦ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ጣሊያንኛ:- የቤተሰብ ደስታ የሚገኝበት ምሥጢር፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ትግርኛ፦ ቅዱሳን ጽሑፎችን መመርመር 1997።
◼ በቅርቡ የሚደርሱ ሌሎች ጽሑፎች:- አማርኛ፦ እውቀት፤ አረብኛ፦ በደስታ ኑር! እንግሊዝኛ፦ የውዳሴ መዝሙሮች (ስምንት ክሮች ያሉት አልበም።)