የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/97 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 9/97 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም፦ ብሮሹሮች፤ የቤተሰብ ደስታ የተባለውን መጽሐፍ በውጭ አገር ቋንቋ ተናጋሪዎች ክልል መጠቀም ይችላል። ጥቅምት፦ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። በተመላልሶ መጠየቅ ጊዜ ሰውየው ፍላጎት ካሳየ ኮንትራት እንዲገባ ሐሳብ ማቅረብ ይቻላል። በቀሩት የወሩ ቀናት የመንግሥት ዜና ቁ. 35 እናሰራጫለን። ኀዳር፦ የመንግሥት ዜና ቁ. 35⁠ን ማሰራጨታችንን እንቀጥላለን። በእያንዳንዱ ቤት ወይም መኖሪያ የቤቱን ባለቤት በማግኘት የመንግሥት ዜና ቁ. 35⁠ን ቅጂ በማዳረስ ክልላቸውን የሸፈኑ ጉባኤዎች የእውቀት መጽሐፍን ማበርከት ይችላሉ። ታኅሣሥ፦ ታላቁ ሰው (የእንግሊዝኛ) እና/ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ።

◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እሱ የወከለው ሰው በመስከረም 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦች በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-3 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናሳስባቸው እንወዳለን።

◼ ጉባኤ የሚሰበሰቡ ሁሉ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት አዲስ ኮንትራት ለማስገባት ወይም ለማሳደስ እንዲሁም ለራሳቸው የግል ኮንትራት መግባት የሚኖርባቸው በጉባኤው በኩል ነው።

◼ አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ ማኅበሩ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርሃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ነገሮች ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት የትኞቹ ጽሑፎች እንደሆኑ እባካችሁ አስታውሱ።

◼ የጽሑፍ ትእዛዝ በሚዘጋጅበት ጊዜ የማኅበሩ ሲዲ-ሮም ያለአንዳች ልዩነት ለሁሉ ሰው የሚሰጥ አለመሆኑን ጉባኤዎች ማስታወስ አለባቸው። ሲዲ-ሮሙ በዋነኛነት የተዘጋጀው ለአስፋፊዎች ነው።

◼ የግንቦት 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን “የጥያቄ ሣጥን” ተቃራኒ ጾታ ካላቸው አስፋፊዎች ጋር በአገልግሎት ስለ መሠማራት ጠንቃቆች እንድንሆን አሳስቧል። በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ እንድንጠቀም የሚያደርጉ አጥጋቢ ምክንያቶች አሉ። እንዲህ ሲባል ግን ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች ወይም ሌሎች ወንድሞችም ቢሆኑ በመስክ አገልግሎት ከእህቶች ጋር ማገልገል አይችሉም ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ የጥያቄው ሣጥን መንፈስ አንድ ወንድም በሥጋ ከማይዛመዳት ከአንዲት እህት ጋር ብቻ አዘውትሮ በአገልግሎት ጊዜ ማሳለፉ ጥበብ እንደማይሆን የሚገልጽ ነው።

◼ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች ምሥራቹን ለማድረስና ፍላጎት ያሳዩትን ለማሰባሰብ ልዩ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ካሉ ለአዲስ አበባ የውቤ ጉባኤ ለማስታወቅ ትችላላችሁ።

◼ በቅርቡ ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው ጽሑፎች:- አማርኛ፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት፤ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የምትወዱት ሰው ሲሞት . . .፤ አረብኛ፦ ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈና ጠቃሚ ነው፤ እንግሊዝኛ፦ ትራክት ቁጥር 13, 14, 15, 16, 20፤ የመጠበቂያ ግንብ ጥራዞች የ1958, 1986, 1988፤ የመንግሥቱ ዜማዎች ቁ. 1 (ካሴት)፤ ፈረንሳይኛ፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት፤ ጣሊያንኛ፦ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ