የመስከረም የአገልግሎት ስብሰባዎች
መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 9 (26)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች ቅድሚያ ስጡ።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በየካቲት 22, 1987 የእንግሊዝኛ ንቁ! ገጽ 8-9 ላይ ከወጣው “ቅድሚያ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ሐሳብ ስጥ።
15 ደቂቃ፦ “ሌሎች ማጽናኛ እንዲያገኙ እርዷቸው።” አንቀጽ 1ን እና ከ6-8 ያሉትን አንቀጾች የሚሸፍን ንግግር። ከአንቀጽ 2-5 ያሉትን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ደቀ መዛሙርት ማፍራትን ዓላማ በማድረግ ጥናት የማስጀመር ግብ ላይ ለመድረስ ጥረት እንዲያደርጉ አጥብቀህ አሳስብ።
መዝሙር 46 (107) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 10 (27)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ በሚያስችል መንገድ ማስጠናት።” በንግግር የሚቀርብ።
15 ደቂቃ፦ “ተማሪዎች ራሳቸውን ለአምላክ ወደ መወሰንና ወደ ጥምቀት እንዲደርሱ አበረታቷቸው” በሚለው ንዑስ ርዕስ (የመንግሥት አገልግሎታችን 6/96 አባሪ ገጽ፣ አንቀጽ 20-22) አንድ ሽማግሌ ጥናት ከሚመሩ ተሞክሮ ካላቸው አስፋፊዎች ጋር ይወያያል።
መዝሙር 98 (220) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 43 (98)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ በኢትዮጵያ።” ጥያቄና መልስ።
20 ደቂቃ፦ ትምህርት ቤት የተባለውን ብሮሹር እየተጠቀማችሁበት ነው? አንድ ሽማግሌ በጥቅምት 1, 1985 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) ገጽ 30-31 ላይ ያለውን ከተወሰኑ ወላጆችና ልጆች ጋር ይወያያል። ትምህርት ቤት የተባለውን ብሮሹር በመጠቀም ያገኟቸውን ተሞክሮዎች ይናገሩ።
መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 12 (32)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ፦ ውይይት መክፈት የሚቻልበት መንገድ። በአገልግሎት የምናገኘው ስኬታማነት በአመዛኙ የተመካው ሌሎች ሰዎችን ትርጉም ባለው ውይይት ውስጥ ማስገባት በመቻላችን ላይ ነው። ሌሎች ሰዎች ማዳመጥ እንዲፈልጉ የሚያደርጋቸውን ነገር መናገር ከቻልን በምስክርነቱ ሥራ ከሚገጥሙን ትልልቅ ችግሮች አንዱን ተወጣን ማለት ነው። በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 16 አንቀጽ 11-14 ላይ ያሉትን ቁልፍ ነጥቦች ከአድማጮች ጋር ተወያይ። ውይይት በመክፈት ጥሩ ችሎታ ያላቸውና ውጤታማ የሆኑ አስፋፊዎች:- (1) በእግሩ ለሚጓዝ ሰው፣ (2) አውቶቡስ ውስጥ ላለ መንገደኛ፣ (3) ሱቅ ውስጥ ለሚሰራ ሻጭ፣ (4) በመኪና ማቆሚያ አካባቢ ለሚገኝ ገበያተኛ፣ (5) መናፈሻ ውስጥ ለተቀመጠ ሰው እና (6) በስልክ ሲመሰክሩ ያገኙትን ሰው ሲያነጋግሩ የሚጠቀሙባቸውን የመግቢያ ቃላት እንዲናገሩ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ የጉባኤውን የ1997 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ከልስ። ጉባኤው በተለይ በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ላደረገው መልካም ጥረት የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ምስጋና ያቀርባል። የመስክ አገልግሎትንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንቅስቃሴዎችን ከፍ ማድረግን በተመለከተ ከሽማግሌዎች አካልና ካለፈው የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ሪፖርት የተገኙ ሐሳቦችን ያቀርባል። አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመርና መምራትን እንዲሁም አምስት ቅዳሜና እሁድ ባላቸው በኅዳር፣ በግንቦትና በነሐሴ ረዳት አቅኚ መሆንን ጨምሮ በአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ ግቦችን ይጠቅሳል።
መዝሙር 48 (113) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 29 የሚጀምር ሳምንት
ዝሙር 16 (37)
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። በጥቅምት ወር ለሚደረገው የመጽሔት ዘመቻ ለመዘጋጀት በጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10 ላይ የተጠቀሰውን ‘የአገልግሎት ክልልህን የማጥናት፣’ ‘ከመጽሔቶቹ ይዘት ጋር የመተዋወቅ፣’ ‘በመግቢያ ላይ የምንናገራቸውን ቃላት የማዘጋጀት፣’ ‘ከባለቤቱ ሁኔታ ጋር የሚስማማ አቀራረብ የመጠቀም’ እና ‘እርስ በእርስ የመረዳዳትን’ አስፈላጊነት ተናገር።
15 ደቂቃ፦ የውገዳ ውሳኔዎችን በማክበር ለይሖዋ ታማኝነት ማሳየት። በሐምሌ 15, 1985 ገጽ 30, 31 እና በመስከረም 15, 1981 ገጽ 20-31 መጠበቂያ ግንብ (የእንግሊዝኛ) ላይ የተመሰረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ አገልግሎታችሁን ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ። ከአገልግሎታችን መጽሐፍ በገጽ 81-83 ባለው ላይ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ዋና ዋና ነጥቦቹን ለማጉላት እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቅ:- (1) የኢየሱስን ምሳሌ በመከተላችን ምን ጥቅም አግኝተናል? (2) የመስበክ ኃላፊነታችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው? (3) ሕይወታችንን ለይሖዋ እንድንወስን ያነሳሳን ዓላማ ምንድን ነው? (4) አንድ ሰው አምላክን ለማገልገል ምን ዓይነት ሥነ ምግባር እንዲኖረው ይፈለግበታል? (5) ከኢየሱስ የስብከት ዘዴ ምን ለመማር እንችላለን?
መዝመር 21 (46) እና የመደምደሚያ ጸሎት።