የጥር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ጥር 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 5 (10)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “የተጣራ ምሥክርነት በመስጠት ተደሰቱ።” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። ውጤታማ ለሆነ አቀራረብ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች አጉላ:- (1) ወዳጃዊ ሰላምታ ስጡ፣ (2) በቅርቡ የሰዎችን ትኩረት በሳበ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሐሳብ ስጡ ወይም ስለዚያ ጥያቄ ጠይቁ፣ (3) ተስማሚ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥቀሱ፣ እንዲሁም (4) በሚበረከተው ጽሑፍ ላይ እንዲተኮር አድርጉ። አንድ ጥሩ ችሎታ ያለው አስፋፊ በቀረቡት ሐሳቦች ተጠቅሞ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲያቀርብ አድርግ።
17 ደቂቃ፦ ደምን በተመለከተ አምላክ የሰጠውን ሕግ ለማክበር ከወዲሁ ተዘጋጁ። አንድ ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ በቅድሚያ የተሰጠውን የሕክምና መመሪያ/የሕክምና ባለሞያዎችን ከኃላፊነት ነፃ የሚያደርግ ካርድ የመሙላቱን አስፈላጊነት አስመልክቶ የሚያቀርበው ክፍል። በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈው መዝሙር 19:7 አምላክ ደምን በሚመለከት በሥራ 15:28, 29 ላይ ያሰፈረው ሕግ ፍጹም መሆኑን ያሳያል። ታማኝ አምላኪዎች ይህንን ሕግ ለማክበር ይጥራሉ። ይህ ሰነድ የአምላክን ሕግ ለማክበር ያደረግኸውን ቁርጥ ውሳኔ ሊያሳውቅልህና አቋምህን መግለጽ በማትችልበት ጊዜ ስለ አንተ ሆኖ ሊናገርልህ ይችላል። (ከምሳሌ 22:3 ጋር አወዳድር።) አዲስ የሕክምና ሰነድ መሙላትህ ደም ላለመውሰድ በአሁኑ ጊዜ ያደረግኸውን ውሳኔ ያሳያል። ከዚህ ስብሰባ በኋላ አዲስ ካርድ የሚፈልጉ የተጠመቁ ምሥክሮች አንድ አንድ ካርድ ይሰጣቸዋል። በተጨማሪም ያልተጠመቁ ትንንሽ ልጆች ያሏቸው ወላጆች ለእያንዳንዱ ልጅ የመታወቂያ ወረቀት ይሰጣቸዋል። እነዚህ ካርዶች በዚያው ምሽት መሞላት የለባቸውም። እቤት በጥንቃቄ ሊሞሉ ይገባል ሆኖም አይፈረምባቸውም። ሁሉም ካርዶች የሚፈረምባቸው፣ የምሥክሮቹ ስምና ቀን የሚጻፍባቸው ከፊታችን የሚደረገው የመጽሐፍ ጥናት ስብሰባ ካለቀ በኋላ በመጽሐፍ ጥናቱ መሪ ተቆጣጣሪነት ነው። እንደዚህ መደረጉ ይህንን የሕክምና ሰነድ በሚገባ አጠናቀው መሙላት የሚፈልጉ በእርሱ ቡድን ውስጥ ያሉት ሁሉ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያገኙ ያስችላል። ምሥክር ሆነው የሚፈርሙት ካርዱን የሚይዘው ሰው ሰነዱን ሲፈርም ማየት ይኖርባቸዋል። በዚህ ጊዜ ያልተገኘና ሆኖም ካርዱን ሞልቶ መፈረም የሚፈልግ ማንኛውም ወንድም በሚቀጥለው የአገልግሎት ስብሰባ ላይ የመጽሐፍ ጥናቱ መሪ ወይም ሌሎች ሽማግሌዎች ይረዱታል። ሁሉም አስፋፊዎች ካርዳቸውን በአግባቡ ሞልተው እስኪጨርሱ ድረስ በዚህ መልኩ ይቀጥላል። (የጥቅምት 15, 1991 ደብዳቤን ከልሱ።) ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ከሁኔታቸውና ከአቋማቸው ጋር በሚስማማ መንገድ ሐሳቡን ከዚህ ካርድ ላይ በመውሰድ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው የራሳቸውን መመሪያ ሊያዘጋጁ ይችላሉ።
መዝሙር 59 (139) እና የመደምደሚያ ጸሎት
ጥር 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 84 (190)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቶችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው።” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። በታኅሣሥ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 13 አንቀጽ 15 ላይ ያለውን ተሞክሮ ጨምረህ አቅርብ።
20 ደቂቃ፦ “ይሖዋ ከወትሮው የበለጠ ኃይል ይሰጣል።” ጥያቄና መልስ። (መጠበቂያ ግንብ 14-111 ገጽ 19 አንቀጽ 15-16ን ተመልከት።) ይሖዋ እንዴት እንዳበረታቸው የሚያሳዩ አበረታች ተሞክሮዎችን የሚናገሩ ወንድሞችና እህቶች አዘጋጅ።
መዝሙር 36 (81) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ፦ ደስታ የሚያስገኝ የቤተሰብ ጥናት። አንድ ባልና ሚስት ቤተሰባቸው ስለሚያስፈልገው መንፈሳዊ ነገሮች ይወያያሉ። ዓለማዊ ግፊቶች በልጆቻቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆኑ ስላሳሰባቸው የልጆቻቸውን መንፈሳዊነት የማጠናከሩ አስፈላጊነት ተሰምቷቸዋል፤ ሆኖም የቤተሰብ ጥናቱ የማይዘወተርና አብዛኛውን ጊዜም ውጤታማ እንዳልነበረ ያምናሉ። በነሐሴ 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 26-9 ላይ ትርጉም ያለው የቤተሰብ ጥናት እንዴት መምራት እንደሚቻል የሚገልጹትን ምክሮች አብረው ይከልሳሉ። የልጆቻቸውን መንፈሳዊ ደህንነት የመጠበቁን ጉዳይ በትኩረት ለመከታተል ሁለቱም ቁርጥ ውሳኔ ያደርጋሉ።
መዝሙር 62 (146) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 83 (187)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በየካቲት የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር። የቤተሰብ ኑሮ እና/ወይም ወጣትነትህ የተባሉትን መጻሕፍት ለማበርከት የሚረዱ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦችን ጥቀስ።
15 ደቂቃ፦ “ለይሖዋ የአምልኮ ቦታ አክብሮት አሳዩ።” ጥያቄና መልስ። በሽማግሌ የሚቀርብ፤ ጉባኤው ሊሠራባቸው የሚገባውን ነጥቦች በደግነት ማቅረብ ይኖርበታል።
18 ደቂቃ፦ በዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ ውስጥ ያበረከትነውን ድርሻ ሪፖርት ማድረግ። (አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 100-2, 106-10 ላይ የተመሰረተ።) የጉባኤው ጸሐፊ በንግግርና በውይይት ያቀርበዋል። በየጊዜው የስብከት እንቅስቃሴያችንን ሪፖርት ማድረግ ተገቢ የሆነበትን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምሳሌ ከገለጸ በኋላ ሁለት የጉባኤ አገልጋዮች “የመስክ አገልግሎታችንን ሪፖርት የምናደርግበት ምክንያት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ያሉትን ሐሳቦች እንዲናገሩ ይጋብዛቸዋል። ከዚያም ጸሐፊው ሳይዘገዩ ሪፖርቶችን በትክክል የመመለሱን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርጎ ከመግለጹም በላይ አብዛኛውን ጊዜ በተሳሳተ መንገድ የሚተረጎሙ ነጥቦችን ግልጽ ያደርጋል። የግል ግቦችን ማውጣት ጠቃሚ የሆነበትን ምክንያት ከጠቀሰ በኋላ በምሥክርነቱ ሥራ ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ ስለሚያስገኛቸው በረከቶች የሚያበረታታ ሐሳብ በመግለጽ ይደመድማል።
መዝሙር 73 (166) እና የመደምደሚያ ጸሎት።