ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
◼ ኢትዮጵያ፦ በአረካ፣ በጎንደር፣ በሆሳዕና እና በነገሌ አርሲ አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል።
◼ በዓለም ዙሪያ ባሉ ደሴቶች የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በጥር ወር አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ማግኘታቸውን ሪፖርት አድርገዋል። ከእነዚህ መካከል ዶሚኒካን ሪፑብሊክ፣ ሃይቲ፣ ማርቲንኪ፣ ሞሪሽየስ፣ ፊሊፒንስ፣ ታይዋን እና ትሪኒዳድ ይገኙበታል።
◼ ካለፈው ዓመት ከነበረው አማካኝ የአስፋፊዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በሲሼልስ የተመዘገበው ጭማሪ 18 በመቶ ሲሆን በሴይንት ማርቲን ደግሞ 16 በመቶ ነው።
◼ በሆንግ ኮንግ ያሉ አስፋፊዎች አማካይ የአገልግሎት ሰዓታቸው 12.7 ደርሷል።
◼ በታይዋን ለመጀመሪያ ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገነባው የመንግሥት አዳራሽ በየካቲት ወር ተጠናቋል።