የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/93 ገጽ 2
  • ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ቲኦክራቲካዊ ዜና
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ብሮሹሮችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 7/93 ገጽ 2

ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች

አርጀንቲና፦ በየካቲት ወር 98,601 ወደሆነ ከመቼው ጊዜ የበለጠ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሳለች። በዚያው ወር ውስጥ 507 አዲስ ደቀ መዛሙርት ተጠምቀዋል።

ቤኒን፦ በየካቲት ወር 2,967 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች። ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው እንቅስቃሴ ጋር ሲወዳደር አስፋፊዎች 13. 8 በመቶ፣ ሰዓት 6. 1 በመቶ፣ የተበረከቱ መጽሔቶች 40. 6 በመቶ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች 25. 1 በመቶ ጨምረዋል።

ኢኳዶር፦ በየካቲት ወር 23,176 አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎታቸውን ሪፖርት ሲያደርጉ 42,219 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መርተዋል። ይህም ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር ከነበረው ጋር ሲወዳደር አስፋፊዎች 2,180 እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች 3,183 ጨምረዋል።

አየርላድ፦ በየካቲት ወር 4,093 የደረሰ ተከታታይ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ለ59⁠ንኛ ጊዜ ሪፖርት አድርጋለች። 2,682 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች መመራታቸው ወደፊት እድገት እንደሚኖር ያሳያል።

ፔሩ፦ በፔሩ የሚገኙት 43,366 አስፋፊዎች 369,437 ተመላልሶ መጠየቆችንና 68,090 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በየካቲት ወር ሪፖርት አድርገዋል። በሊማ የተሰራው አዲስ የክልል ስብሰባ አዳራሽ 21,240 ሰዎች በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል።

ታሂቲ፦ በየካቲት ወር 1,604 አስፋፊዎች ሪፖርት በማድረጋቸው 13 በመቶ ጭማሪ ተገኝቷል። ይህም ታሂቲ ለ64ኛው ጊዜ በተከታታይ ያገኘችው ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ነበር።

ዛየር፦ በዚህ አገር ምንም እንኳን የኢኮኖሚና የፖለቲካ አለመረጋጋት ቢኖርም ወንድሞች በየካቲት ወር 71,098 የደረሰ አዲስ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርገዋል። ይህም ካለፈው ዓመት አማካይ በላይ 9 በመቶ ጨምሯል። የጉባኤ አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎት አማካይ ሰዓት 16. 8 ነው። ዛየር በአሁኑ ጊዜ ከ6,000 በላይ የዘወትር አቅኚዎች አሏት።

በካረቢያን አካባቢ ያሉት አሩባ፣ ጓዴሎፕ፣ ማርቲኒክ፣ ሴንት ኪትስና የዩ ኤስ ቨርጂን ደሴቶች በሙሉ በየካቲት ወር አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርገዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ