የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/99 ገጽ 7
  • ብሮሹሮችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብሮሹሮችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቲኦክራቲካዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
km 7/99 ገጽ 7

ብሮሹሮችን በሚገባ ተጠቀሙባቸው

1 በዚህ ዓመት ብሮሹሮችን ለማበርከት የምናደርገው ዘመቻ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ብዙ ዓይነት እንዲሁም የሚማርክ ርዕስ ያላቸውን ብሮሹሮች ያካተተ ነው። በቅርቡ የወጡትን ለሁሉም ሰው የሚሆን መጽሐፍ እና ስንሞት ምን እንሆናለን? የተባሉትን ብሮሹሮች ሳይቀር ይጨምራል። ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት የወጡትም ብሮሹሮች ቢሆኑ በክልላችን ውስጥ ላሉት አብዛኞቹ ሰዎች አዲስና በጣም ጠቃሚ ናቸው። የብሮሹሮቹ ዋጋ መቀነሱ በአብዛኛው ከእነዚህ ግሩም ጽሑፎች መካከል ሁለቱን ወይም ከዚያ የበለጡትን በአንድ ላይ ለማበርከት ያስችላል። አንዳንዶቹ ብሮሹሮችም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ያስችላሉ። እነዚህን ብሮሹሮች ለማበርከት በግለት መንቀሳቀስ ቀላል ነው ቢባል እንደምትስማሙ ምንም አያጠራጥርም!

2 ከዚህ በታች አንዳንድ ሐሳቦች ቀርበዋል። የመጀመሪያው አቀራረብ የአምላክ መንግሥት በተባለው ብሮሹር ላይ የሚያተኩር ይሆናል:- “ጎረቤቶቻችንን አንድ ጥያቄ እየጠየቅናቸው ነው እርስዎም በዚህ ጉዳይ ላይ ያለዎትን አስተያየት ብንሰማ ደስ ይለናል። ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት እንዲመጣና ፈቃዱም በሰማይ እንደሆነ በምድር እንዲሆን እንድንጸልይ አስተምሮናል። የአምላክ ፈቃድ በእርግጥ በምድር ላይ የሚሆን ይመስልዎታል?” መልስ እንዲሰጥ ፍቀዱለት። ከዚያም የአምላክ መንግሥት የተባለውን ብሮሹር ገጽ 31 ግለጡና እዚያ ላይ በሚገኘው የራእይ 21:3, 4 ተስፋ ላይ እንዲያተኩር አድርጉ። ከዚያም ገጽ 29 ላይ ያሉትን ነጥቦች ተጠቅማችሁ ውይይቱን መቀጠል ትችሉ ይሆናል። ንጉሣዊ መስተዳድር የሆነው የአምላክ መንግሥት ፈቃዱ በምድር እንዲፈጸም የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ አስረዱት።

3 ከጽሑፎቻችን ሁሉ የበለጠ ሰፊ ስርጭት ያለው በደስታ ኑር! የተባለው ብሮሹር ብዙ ቅጂዎች አሉን። ይህን ብሮሹር በዚህ መንገድ ልታበረክቱ ትችላላችሁ:- “ጎረቤቶቼን መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ ጥያቄ እንዳላቸው እየጠየቅኳቸው ነበር። ይህ ጽሑፍ መጽሐፍ ቅዱስን አስመልክተው የሚነሱትን የተለመዱ ጥያቄዎች ይዟል።” [ገጽ 2⁠ን በማሳየት አንዳንድ ጥያቄዎችን ምረጡ።] ከዚያም ከ15-17 ያሉትን ስለ ሞት የሚያስረዱትን ሥዕሎች ካሳያችሁት በኋላ ስለ ትንሣኤ ከሚናገረው ሥዕል 48 ጋር ማያያዝ ትችላላችሁ። ከ20-23 ያሉትን ሥዕሎች ከ2 ጢሞቴዎስ 3:1-5 ጋር በማያያዝ መጠቀም ደግሞ ሌላ አማራጭ ነው። ብሮሹሩን በመስጠትና በሌሎቹ ጥያቄዎች ላይ ለመነጋገር ቀጠሮ በመያዝ ደምድሙ።

4 የሕይወት ዓላማ የተባለውን ብሮሹር ለመጠቀም ሞክራችሁ ታውቃላችሁ? ይህ ምሳሌ ወጣቶችን የሚመለከት ቢሆንም ለወላጆችና ሌላው ቀርቶ በእድሜ ለገፉ ሰዎችም እንዲስማማ አድርጎ መጠቀም ይቻላል:- “ብዙ ወጣቶች እውነተኛ የሕይወት ዓላማ ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ጥቂቶች የተወሰነ ደስታ ቢያገኙም አብዛኞቹ ግን ሕይወታቸው በብስጭትና በመከራ የተሞላ ነው። የአምላክ ዓላማ እንደዚህ ባለ ሁኔታ እንድንኖር ነው ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀዱለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ይህን በመሰለ ዓለም ውስጥ እንድንኖር እንደሚፈልግ ያሳያል።” ገጽ 21 ላይ ያለውን ሥዕል አሳዩትና ወደ ገጽ 25 እና 26 አንቀጽ 4-6 ሄዳችሁ አምላክ የሰጠውን ተስፋ አብራሩ። በሚቀጥለው ጊዜ ስትመለሱ ልትወያዩበት ትችሉ ዘንድ ከመለያየታችሁ በፊት የሚከተለውን ጥያቄ አንሱ:- “አምላክ የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን?”

5 የሞት ጉዳይ ብዙ ሰዎችን ያሳስባቸዋል። ይህን ጉዳይ አስመልክተው የወጡ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት እና የሙታን መናፍስት . . . የተባሉ ሦስት ብሮሹሮች አሉን። ውይይቱን እንዲህ በማለት ልትጀምሩ ትችላላችሁ:- “ብዙውን ጊዜ ሰዎች በአሳዛኝ ገጠመኞች ምክንያት ሞተው ድንኳኖች ተጥለው ማየታችን እውነት አይደለም? (ቆም በሉ) ሁላችንም የምንወዳቸውን ሰዎች በሞት የማናጣበት ጊዜ ይመጣል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ ግሩም ብሮሹር እንዲህ ያለው ቀን በቅርቡ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገርለትን እርግጠኛ ተስፋ በመግለጽ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አጽናንቷል። [የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር ገጽ 5 ገልጣችሁ 1 ቆሮንቶስ 15:21, 22⁠ን ጨምሮ አምስተኛውን አንቀጽ አንብቡ። ከዚያም ገጽ 30 ላይ ያለውን ሥዕል አሳዩት።] እዚህ ላይ ሠዓሊው በሞት የተለዩንን የምንወዳቸው ሰዎች በትንሣኤ ጊዜ መልሰን ስንቀበል ልናገኘው የምንችለውን ደስታ አስቀምጦታል። ይሁን እንጂ ይህ አስደሳች ትዕይንት የሚከናወነው የት ነው? ይህ ብሮሹር መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ ይዟል።” ብሮሹሩን ከወሰደ እንዲህ በማለት ልትጨምር ትችል ይሆናል:- “ሌላ ጊዜ መጥቼ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ ብንወያይ ደስ ይለኛል።”

6 እርግጥ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉ። ሞትን በተመለከተ በዮሐንስ 11:11-14 ወይም በዮሐንስ 5:28, 29 ላይ ያሉትን ጥቅሶች የሙታን መናፍስት ከተባለው ብሮሹር ጋር አያይዞ መጠቀም ይቻላል። መለኮታዊው ስም የተባለውን ብሮሹር የጌታን ጸሎት ወይም ሌላ ተስማሚ ጥቅስ በመጥቀስ ማበርከት እንችላለን። ሙስሊሞችና ክርስቲያን ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች ሥላሴ ለተባለው ብሮሹራችን ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። በዚህም ብሮሹር መጠቀማችንን መቀጠል እንችላለን። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለው ብሮሹር ብዙ አስተዋይ ሰዎችን ለሚያስጨንቀው አምላክ መከራ እንዲኖር ለምን ፈቀደ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል። በአምላክ ሕዝቦች ላይ ብዙ የሐሰት ወሬዎች ስለሚሰነዘሩ ግራና ቀኙን ማየት የሚፈልጉ ግለሰቦች እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች የተባለውን ብሮሹር ማንበብ ሊያስደስታቸው ይችላል። እንግዲያውስ ከእነዚህ ግሩም መሣሪያዎች መካከል የተለያየ ዓይነት ያላቸውን ይዛችሁ በመሄድ ተስማሚ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አበርክቷቸው!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ