ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
◼ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች የሆኑት ቤኒን፣ ካሜሩን፣ ኮት ዲቩዋር፣ ጋና፣ ላይቤርያና ናይጄሪያ በየካቲት ወር አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ደርሰዋል።
◼ ብዙ ስደተኞች ወደ ላይቤርያ እየተመለሱ ሲሆን በዚህች አገር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለእውነት ከፍተኛ ጥማት አላቸው። በየካቲት ወር የነበሩት 2,286 አስፋፊዎች 6,277 የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት አድርገዋል።
◼ በደቡብ ፓስፊክ የሚገኙት ፊጂ፣ የሰሎሞን ደሴቶችና ታሂቲ በየካቲት ወር አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ሪፖርት አድርገዋል።
◼ የማዳጋስካር ደሴት 9,484 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ያገኘች ሲሆን ይህ ደግሞ ካለፈው ዓመት አማካይ ቁጥር 14 በመቶ ጭማሪ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በየካቲት ወር ውስጥ ከ20,000 በላይ የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት አድርገዋል።