የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/98 ገጽ 2
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 4/98 ገጽ 2

ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

ቤኒን፦ በኅዳር ወር ሪፖርት ያደረጉ 5,331 አስፋፊዎች ነበሩ፤ ይህ ደግሞ ለ59ኛ ጊዜ በተከታታይ የተገኘ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ነበር።

ቆጵሮስ፦ በኅዳር ወር የተመዘገበው የ2 በመቶ ጭማሪ፣ 1,758 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አስገኝቷል። ከዚህም በተጨማሪ ሪፖርት ያደረጉ 136 የዘወትር አቅኚዎች ስለነበሩ በዚህም ረገድ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ተመዝግቧል።

ሕንድ፦ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን የመለሱ 18,077 አስፋፊዎች ስለነበሩ በኅዳር ወር ውስጥ በስብከቱ ሥራ ጥሩ እድገት ታይቷል። ይህ ለ39ኛ ጊዜ በተከታታይ የተገኘ ከፍተኛ ጭማሪ ነበር።

ላይቤርያ፦ በኅዳር ወር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ 2,120 የደረሰ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አስፋፊዎች የመስክ አገልግሎታቸውን ሪፖርት አድርገዋል።

ሰሎሞን ደሴቶች፦ በኅዳር ወር 1,393 አስፋፊዎች ሪፖርት ያደረጉ በመሆኑ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ ተደርሷል።

ታይዋን፦ በያዝነው የአገልግሎት ዓመት እስካሁን ድረስ አማካኙ የአስፋፊዎች ቁጥር 3,516 ነው። ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት የ6 በመቶ ጭማሪ ያሳያል።

ኢትዮጵያ፦ በጥር ወር በሶዶና በነቀምቴ አዳዲስ የመንግሥት አዳራሾች አስደሳች በሆነ ሁኔታ ለአምላክ ተወስነዋል። በቅርቡ የተመሠረቱ አዳዲስ ጉባኤዎች:- በአዲስ አበባ:- አዲስ አምባ፣ መገናኛ እና አራት ኪሎ። ከአዲስ አበባ ውጪ:- ገብረ ጉራቻ፣ ነገሌ ቦረና፣ ሲባጫሮ (ጊምቢ አቅራቢያ)፣ ሚዛን፣ ቴፒ፣ ወልቂጤ፣ ሻኪሶ፣ ጊንጪ። በአሁኑ ጊዜ 90 ጉባኤዎችና ከ20 የሚበልጡ ቡድኖች አሉ። ባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ፣ እያደገ ላለው የትርጉም ክፍላችን ከቤቴል ብዙም በማይርቅና 160 ካሬ ሜትር የወለል ስፋት ባለው ቦታ ላይ የተቀመጡ የተሻሉ ቢሮዎች አግኝተናል። በትርጉም ሥራ የተሰማሩት ወንድሞቻችን እናንተንና ሌሎችን ለመጥቀም ሥራቸውን ለማሻሻል ያስቻላቸውን ይህን ፀጥታ የሰፈነበት አካባቢ በማግኘታቸው ተደስተዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ