ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
▪ ከደቡብ አፍሪካ የመጣው የዞን የበላይ ተመልካቻችን በአዲስ አበባ ስታዲየም በሰጠው ንግግር ላይ 6,356 ተሰብሳቢዎች ተገኝተው ነበር።
▪ በቅርቡ ባሳለፍናቸው ሳምንታት የሚከተሉት የመንግሥት አዳራሾች ተመርቀዋል:- እንጦጦ፣ አዲስ አበባ፤ ስድስት ኪሎ፣ አዲስ አበባ፤ ውቤ/ፒያሳ፣ አዲስ አበባ፤ ጅማ፤ ጌራ።
▪ በመጋቢት ወር አዲስ አበባ በሚገኝ በአንድ ጉባኤ ውስጥ ያሉ 66 አስፋፊዎች 329 መጽሔቶች ያበረከቱ ሲሆን በአማካይ እያንዳንዱ አስፋፊ 5 መጽሔቶች አበርክቷል ማለት ነው። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ ልዩ አቅኚዎች 90፣ 98 እና አልፎ ተርፎም 119 መጽሔቶች እንዳበረከቱ መረዳት ችለናል።
▪ አንዳንድ ጉባኤዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመምራት በኩል ተዋጥቶላቸዋል። በደብረ ታቦር 19 አስፋፊዎች 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት አድርገዋል፤ ፊንጫ 6 አስፋፊዎች 17 ጥናቶች ይመራሉ፣ እንዲሁም በጊምቢ 17 አስፋፊዎች 32 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ይረዳሉ።