ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ግንቦት:- የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ነጠላ ቅጂዎች። ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ማበርከት እንድትችሉ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለው ብሮሹር ይኑራችሁ። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትም ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ:- አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በማስጀመር ላይ ትኩረት አድርጉ። ሐምሌና ነሐሴ:- ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መካከል ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?