የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/00 ገጽ 7
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የትዳር ጓደኛ የሌላቸው ወላጆችና ዘርፈ ብዙ ችግሮቻቸው
    ንቁ!—2002
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
  • ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው
    ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 5/00 ገጽ 7

የጥያቄ ሣጥን

◼ ወላጆች ልጆቻቸው በስብሰባዎች ላይ ተገቢውን ሥርዓት እንዲይዙ በሚያደርጉት ጥረት አስተናጋጆች ሊያግዟቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ልጆች በተፈጥሮአቸው ወዲያ ወዲህ ማለት ስለሚወዱ በአንድ ቦታ ለረጅም ጊዜ የመቀመጥ ልማድ የላቸውም። ልጆች ከስብሰባዎች በኋላ የታመቀ ጉልበት ስለሚኖራቸው እየተሯሯጡ በመንግሥት አዳራሹም ሆነ በሌሎች መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ወይም በእግረኛ መንገድ ላይ የሚያገኟቸውን ሌሎች ልጆች ያሯሩጣሉ። ይሁንና ‘ያልተቀጣ ብላቴና ወላጁን ያሳፍራል’ የሚለው ምሳሌ እውነት ነው።​—⁠ምሳሌ 29:​15

አንዳንድ በዕድሜ የገፉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ትናንሽ ልጆች ሲሯሯጡ ገፍተው ስለጣሉአቸው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ያሳዝናል። እንዲህ ያለው ሁኔታ ያልታሰበ ስቃይ ከማምጣቱም በላይ በወላጆችና በጉባኤው ላይ አላስፈላጊ ወጪ አስከትሏል። ለራሳቸው ጥበቃና ለሌሎች ደህንነት ሲባል ልጆች በመንግሥት አዳራሹ ውስጥም ሆነ ውጪ እየተሯሯጡ መጫወት ሊፈቀድላቸው አይገባም።

ወላጆች ልጆቻቸው ለአምልኮ ቦታዎቻችን ተገቢውን አክብሮት እንዲያሳዩ የማሠልጠን ቅዱስ ጽሑፋዊ ኃላፊነት አለባቸው። (መክ. 5:​1ሀ) አስተናጋጆች በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች፣ በወረዳና በልዩ እንዲሁም በአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ‘ሁሉ ነገር በአግባብ መከናወኑን’ እንዲሁም ‘ሥርዓት’ መያዙን እንዲከታተሉ ይመደባሉ። (1 ቆ⁠ሮ. 14:​40፤ ቆላ. 2:​5) አስተናጋጆች ከስብሰባው በፊት፣ በስብሰባው ወቅትና ስብሰባው ካበቃ በኋላ በመንግሥት አዳራሹ ውስጥም ሆነ ውጭ ያለውን ሁኔታ ለመከታተል ንቁዎች መሆን አለባቸው። አንድ ልጅ የሚሯሯጥ ወይም የሚረብሽ ከሆነ አስተናጋጁ ልጁን ቀስ ብሎ ሊያስቆመውና እንዲህ ያሉት ድርጊቶች ተቀባይነት የሌላቸው ለምን እንደሆነ ሊያስረዳው ይችላል። በኋላም ምን ችግር እንደነበረና ልጁን መቆጣጠር አስፈላጊ እንደሆነ ለወላጁ በደግነት ሊነገረው ይገባል። ወላጁም ቢሆን ተገቢውን ምላሽ መስጠት አለበት።

አንዳንድ ጊዜ ሕጻናትና ትንንሽ ልጆች ስብሰባዎች በመካሄድ ላይ እያለ ሊያለቅሱ ወይም ሊበጠብጡ እንደሚችሉ የታወቀ ነው። አስተናጋጆች ስብሰባው ከመጀመሩ ቢያንስ 20 ደቂቃ ቀደም ብለው በመድረስ ሕጻናት ልጆቻቸውን ይዘው በአዳራሹ የኋለኛ ረድፍ መቀመጥ ለሚፈልጉ ወላጆች ቦታውን ክፍት ሊያደርጉላቸው ይችላሉ። የቀረነውም የኋለኞቹን መቀመጫዎች ለእነርሱ በመልቀቅ መተባበር ይኖርብናል።

አንድ ልጅ መበጥበጥ ከጀመረ ወላጁ አንድ ዓይነት እርምጃ መውሰድ አለበት። ሆኖም ወላጁ ምንም እርምጃ ካልወሰደና ረብሻው የሌሎችን ትኩረት የሚሰርቅ ከሆነ ልጁን ከጉባኤው አዳራሽ ይዞት እንዲወጣ አስተናጋጁ በደግነት ሊጠይቀው ይችላል። ትንንሽ ልጆች ያሏቸውን አዳዲስ ሰዎች ወደ ስብሰባዎች ስንጋብዝ አብረናቸው በመቀመጥ ልጆቹ ካለቀሱ ወይም በሌሎች መንገዶች ከረበሹ ልንረዳቸው ይገባል።

በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ልጆች ማየትና በአምላክ ቤት ውስጥ የሚያሳዩትን ጥሩ ጠባይ መመልከት ያስደስተናል። (1 ጢ⁠ሞ. 3:​15) ይሖዋ ለአምልኮ ያደረገውን ዝግጅት በማክበር ለእርሱ ክብር ከማምጣታቸውም በላይ ከሁሉም የጉባኤው አባላት አድናቆትን ያተርፋሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ