የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/00 ገጽ 2-5
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 24 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 31 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 7/00 ገጽ 2-5

የአገልግሎት ስብሰባዎች ኘሮግራም

ሐምሌ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 83 (187)

12 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በአገሪቱና በጉባኤው የሚያዝያ የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ላይ ሐሳብ ስጥ። እባክህ በጉባኤያችሁ ሪፖርት የመለሱትን የአስፋፊዎችና የአቅኚዎች ጠቅላላ ቁጥር ተናገር። ረዳት አቅኚዎች ሆነው ያገለገሉት ስንት እንደነበሩ ተናገር። እያንዳንዱ አስፋፊ በአማካይ ስንት ሰዓት እንዳገለገለ መናገርም ትችላለህ። በሐምሌና በነሐሴ ወር ሁሉም በአገልግሎቱ አዘውታሪዎች እንዲሆኑ አበረታታ። በሚያዝያ የነበረንን ያህል የአስፋፊዎች ቁጥር በዚህም ወር ማግኘት እንችል ይሆን? ትኩረታቸውን “የኋለኛውን ገጽ ተመልከቱ” ወደሚለው ሣጥን አዙርና በተጠቀሱት የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ውስጥ ካሉት አቀራረቦች መካከል በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውጤታማ ሊሆን የሚችል አንድ አቀራረብ መርጠህ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

15 ደቂቃ:- “ዝም ማለት አንችልም።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ክፍሉን በጥያቄና መልስ አቅርበው። የስብከት ሥራችንን አክብደን የምንመለከትባቸውን አንዳንድ ምክንያቶች ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ከጥር 15, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-4 ላይ ተስማሚ ነጥቦች ጨምረህ አቅርብ።

18 ደቂቃ:- የወደፊት ሕይወታችሁን በተመለከተ ጥበብ ያለበት ውሳኔ አድርጉ። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ወጣቶች ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር አስደሳች ሕይወት ለማሳለፍ መፈለጋቸው ተፈጥሯዊ ቢሆንም ስኬታማ መሆን ከፈለጉ አምላካዊ ምክርን ሥራ ላይ ማዋል ይኖርባቸዋል። (ምሳሌ 19:​20) ተቃራኒ ፆታ ባላቸው ወጣቶች መካከል ጠንካራ የሆነ የመሳሳብ ስሜት አለ። እንዲህ ያሉት ስሜቶች ቁጥጥር ካልተደረገባቸው አደገኛ ውጤት ሊያስከትሉ ይችላሉ። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ተቀጣጥሮ ወደ መጫወት የሚመሩ የፍቅር ግንኙነቶች በመመሥረት ከተቃራኒ ጾታ ጋር ስሜታዊ ቅርርብ መፍጠራቸው ጥበብ ነው ወይ በሚለው ጉዳይ ላይ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በሚለው መጽሐፍ ከገጽ 231-5 ላይ የተሰጠውን ምክር ከልስ። ወጣቶች በአምላክ ፊት ያለባቸውን ሁለንተናዊ ግዴታ የመፈጸማቸውን አስፈላጊነት የሚያጎሉ ዋና ዋና ነጥቦች ከኀዳር 15, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-23 ላይ አቅርብ። በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ወጣቶች ይህንን ምክር እንዲያስቡበትና ያልገቧቸው ነገሮች ካሉ ደግሞ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲወያዩ አበረታታቸው።

መዝሙር 2 (4) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 80 (180)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። መለኮታዊው ስም የተባለውን ብሮሹር በመጠቀም ፍላጎት ያሳየ አንድ ሰው የአምላክን የግል መጠሪያ ስም የማወቅና የመጠቀምን አስፈላጊነት እንዲገነዘብ መርዳት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ በአጭሩ ግለጽ።​—⁠ማመራመር መጽሐፍ ገጽ 197-8 ተመልከት። እባክህ በሚቀጥለው ሳምንት የጥቅምት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችንን እትም ይዘው እንዲመጡ አሳስባቸው።

10 ደቂቃ:- እንዴት ብላችሁ ትመልሳላችሁ? ጥሩ የማስተማር ችሎታ ያለው ወንድም አንድ ብቃት ያለው አስፋፊ ወይም አቅኚ ተጠቅሞ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በሠርቶ ማሳያ ያቀርባል። ገና የመግቢያ ሐሳብ እየተናገርን እንዳለን የቤቱ ባለቤት “ስለ ሃይማኖት ነው?” በማለት ያቋርጠናል። ሰዎችን የምናነጋግረው ስለ ሃይማኖት አይደለም ብለን መልስ መስጠታችን ሐቀኝነት የማይሆንበትን ምክንያት አብራራ። ከዚያም አስፋፊው በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 17 ላይ ‘የይሖዋ ምሥክሮችን አልፈልግም’ በሚለው ርዕስ ሥር ካሉት ሐሳቦች አንዱን ተጠቅሞ ከሁኔታው ጋር በሚስማማ መንገድ እውነቱን ሳይሸሽግ እንዴት በዘዴ መልስ እንደሚሰጥ አሳይ። መስጠት የምንችላቸውን ሁለት የተለያዩ መልሶች በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። ሁለተኛው መልስ በዚህ ርዕስ ሥር በተሰጠው ሁለተኛ ሐሳብ መሠረት ምክንያታዊ በመሆን ላይ ያተኮረ ሊሆን ይችላል። በቀጣዩ ሁኔታ ላይ ደግሞ አስፋፊው በመጽሔት ቀን ከ30-60 ሴኮንድ የሚፈጅ አቀራረብ ተጠቅሞ አንደኛውን መጽሔት ጎላ በማድረግና ለመዋጮ የተደረገውን ዝግጅት በመግለጽ ሁለት መጽሔቶች አንድ ላይ ያበረክታል። (በኅዳር 8, 1999 የአገልግሎት ስብሰባ ላይ በሠርቶ ማሳያ የቀረበውን ሐሳብ ልትጠቅስ ትችላለህ።) ከዚያም የቤቱ ባለቤት “መጽሔቱን ማንበብ እፈልጋለሁ ግን አሁን ገንዘብ የለኝም” በማለት ይመልሳል። አስፋፊው ለጽሑፎቻችን የምንጠይቀው ክፍያ እንደሌለና ሰውየው በእርግጥ ማንበብ የሚፈልግ ከሆነ መጽሔቶቹን ማግኘት እንደሚችል ይገልጽለታል። አክሎም አንዳንድ ጊዜ አስተዋጽኦ ማድረግ እየፈለጉ አቅማቸው የማይፈቅድላቸው ሰዎች እንደሚያጋጥሙንና እኛም ሁኔታቸውን እንደምንረዳላቸው ይገልጻል። ምናልባት ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ሌላ አመቺ ጊዜ ሊገጥመው እንደሚችልና መጽሔቱ እንደሚጠቅመው ተስፋ እንደሚያደርግ ይገልጽለታል። በመጨረሻም፣ አስፋፊው ስለ ሥላሴ ሲጠየቅ ምን ሐሳብ ተጠቅሞ መልስ እንደሚሰጥ ጠይቀው። እንደ ጥያቄዎቹ ሁኔታና ጥልቀት ከማመራመር፣ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ የውይይት አርዕስት፣ ከዘላለም መኖር ወይም ከሥላሴ ብሮሹር የተለያዩ ሐሳቦች ልንጠቀም እንደምንችል ግለጽ። ቆላስይስ 4:​6 ላይ በሚገኙት ቃላት ደምድም።

20 ደቂቃ:- ማንን ለመምሰል ብትጣጣር ይሻላል? አንድ አባት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ከሚገኙ አንድ ወይም ሁለት ልጆቹ ጋር ሆኖ የቤተሰብ ጥናት ይመራል። አባትየው ልጆቹ የሚያወሩት ነገር ብዙውን ጊዜ በታዋቂ ስፖርተኞች፣ በፊልም ተዋንያን፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎችና በሙዚቀኞች ላይ ያተኮረ መሆኑን በቅርቡ አስተውሏል። በእንዲህ ዓይነት ነገሮች መማረክ የዓለም መንፈስ የሚገለጥበት መንገድ በመሆኑ ሁኔታው እንዳሳሰበው ይገልጻል። በነሐሴ 1998 ንቁ! ገጽ 18-20 ላይ በወጣው ርዕሰ ትምህርት ላይ ይወያያሉ። ወጣቶቹ ዝነኛ ሰዎችን ማምለክ አደጋ እንዳለው ከመገንዘባቸውም በላይ ዓለማዊ ዝናና ክብር ለክርስቲያኖች ምንም የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ይስማማሉ። ወላጆችን፣ ሽማግሌዎችንና ሌሎች በጉባኤ ውስጥ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉትን፣ በተለይ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመምሰል መጣጣር የሚያስገኘውን ጥቅም ይወያያሉ።

መዝሙር 14 (34) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ራሳችንን የአምላክ አገልጋዮች አድርገን ማቅረብ። ሁለት የጉባኤ አገልጋዮች በታኅሣሥ 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 19-20 በቀረበው ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር ላይ ይወያያሉ። ከጉባኤ አገልጋዮች የሚፈለጉትን ብቃቶች በጥሩ ሁኔታ የማሟላትን አስፈላጊነት እንደሚገነዘቡና የተሰጣቸውን የሥራ ምድብ እየፈጸሙ እንደሆነ ለማሳየት በግላቸው ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይከልሳሉ። በመስክ አገልግሎት ጥሩ ምሳሌ ሆኖ የመገኘትን አስፈላጊነት ይወያያሉ። በተጨማሪም ለሌሎች የግል እርዳታ በመስጠት በኩል ሽማግሌዎችን ሊረዱ በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ውይይት ያደርጋሉ። ጉባኤው የጊዜውን አጣዳፊነት ተገንዝቦ በመንፈሳዊ እንዲያድግና እንዲበለጽግ ለመርዳት የቻሉትን ያህል መሥራት እንደሚኖርባቸው ይስማማሉ።

10 ደቂቃ:- ከጥቅምት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ “የመኖሪያ ቦታ ልትቀይር ነውን?” የሚለውን ርዕስ ከልስ። በግንቦት 1999 የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ላይ በወጣው የጥያቄ ሣጥን አንቀጽ 3 እና 4 ላይ የሚገኙትን ተስማሚ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። የመኖሪያ ቦታ ከቀየሩ በኋላ አስቀድመው ሳያስቡበት በመቅረታቸው አዘውታሪ አስፋፊ የማይሆኑት ይባስ ብሎም አገልግሎት የሚያቆሙት ሰዎች ሁኔታ በጣም እንደሚያሳስበን እባክህ ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። ለይሖዋና ለሕይወት ሰጪ እውነቱ ያለን ፍቅር በአዲሱ መኖሪያችን አካባቢ ከሚገኙት ወንድሞች ጋር ወዲያው እንድንገናኝ የሚያስችለንን ጥሩ ዝግጅት እንድናደርግ ሊገፋፋን ይገባል።

15 ደቂቃ:- ውጤታማ መግቢያዎች ተጠቀሙ። ከማመራመር መጽሐፍ ገጽ 9-15 ላይ ከሚገኙት መግቢያዎች ሁለት ወይም ሦስት ምረጥና እነዚህን መግቢያዎች በጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩባቸው። “አንድን ሰው በመንገድ ላይ፣ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወይም በሌላ የአገልግሎት ዘርፍ ቀርባችሁ ለማነጋገር የምትጠቀሙባቸው መግቢያዎች ምን ዓይነት ናቸው?” በማለት አድማጮችን ጠይቅ። ጊዜው በፈቀደልህ መጠን አንድ ወይም ሁለት መግቢያዎች በሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

መዝሙር 39 (86) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 17 (38)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ሁሉም የሐምሌ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አሳስብ። በዚህ ወር ብሮሹሮችን በማሰራጨቱ በኩል አድማጮች ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።

12 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

18 ደቂቃ:- “የይሖዋን ትዕግሥት ታደንቃላችሁን?” ጥያቄና መልስ። ስለ ይሖዋ ትዕግሥት የሚገልጹ ተስማሚ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።​—⁠ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ጥራዝ 2 ከገጽ 263-4 ያለውን ተመልከት።

መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 94 (212)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

17 ደቂቃ:- “ዓይናፋርነት ያጠቃሃልን?” ጥያቄና መልስ። በ1997 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 43-4 ላይ የሚገኘውን አበረታች ተሞክሮ ተናገር።

18 ደቂቃ:- “አምላክን የሚያስከብር መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።” ጥያቄና መልስ።

መዝሙር 66 (155) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ