የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/01 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 1/01 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባዎች ፕሮግራም

ጥር 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 11 (29)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

17 ደቂቃ:- “ብርሃናችሁ ይብራ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ሰኔ 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15 አንቀጽ 12-13 ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ሁሉም ማንኛውንም አጋጣሚ ለመመሥከር እንዲጠቀሙበት አበረታታ።

18 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 14 (34)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

15 ደቂቃ:- “ታዛዥ ልብ አለህን?” በሐምሌ 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-31 ላይ የተመሠረተ ንግግር።

20 ደቂቃ:- ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ ትመረምራለህን? በንግግርና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። በቤተሰብ ሆኖ በዕለቱ ጥቅስ ላይ መወያየት ያለውን ጥቅም የሚያጎላውን የታኅሣሥ 15, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 17-18 አንቀጽ 12-14 ተመልከት። በቅርቡ በዕለት ጥቅሱ ላይ ያደረጉት ውይይት በጣም እንደጠቀማቸው ለሚያስታውሱ የቤተሰብ አባላት ቃለ ምልልስ አድርግላቸው፤ እንዲሁም ለምን ጠቃሚ እንደነበረ ጠይቅ። በዕለት ጥቅሱ ላይ የሚደረገው ውይይት ቤተሰባችንን ለማጠንከርና በአገልግሎት በንቃት እንዲካፈል ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ የቤተሰብ ጥናት ፕሮግራም አንድ ክፍል እንደሆነ ተደርጎ መታየት እንዳለበት ጠበቅ አድርገህ ተናገር።

መዝሙር 31 (67) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

7 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

18 ደቂቃ:- መግቢያዎችን ማዘጋጀት የሚቻልበት መንገድ። በንግግርና በሠርቶ ማሳያዎች የሚቀርብ። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 9 ላይ የሚገኙትን ቁልፍ ነጥቦች ከልስ። ከራሳችን ተፈጥሮአዊ ባሕርይና ከአገልግሎት ክልሉ ጋር ይበልጥ የሚስማሙ መግቢያዎችን እንዴት መምረጥ እንደምንችል ተናገር። “ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ልና​ወያይዎ ነበር” ወይም “ምሥራች ልንነግርዎ እንፈልጋለን” እና የመሳሰሉ መግቢያዎችን እንዳይጠቀሙ አሳስብ። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ስናበረክት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ጥቂት መግቢያዎች እንደ ምሳሌ ጥቀስና አንዱን ወይም ሁለቱን በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። (የሚያዝያ 1997 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 10ን ተመልከት።) እያንዳንዳቸው በማመራመር መጽሐፍና በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች በመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴያቸው ላይ በጥሩ ሁኔታ እንዲጠቀሙባቸው አበረታታ።

20 ደቂቃ:- “ጥሩ አዳማጭ ሁኑ።” በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ገጽ 28 አንቀጽ 15-17 ላይ የሚገኙ ነጥቦችን በአጭሩ ተናገር። የማዳመጥ ችሎታችንን የምንፈትንበት ከሁሉ የተሻለው ዘዴ ምን ያህል ማስታወስ እንደምንችል ራሳችንን መጠየቅ ነው። አድማጮች በዚህ ዕለት በቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ ክፍል ያቀረቡ ግለሰቦች ከጠቀሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ጥቂቶቹን አስታውሰው እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 35 (79) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 59 (139)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ጉባኤው ያሉትን መጽሐፎች በመጥቀስ በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር።

15 ደቂቃ:- እውነተኛው አምላክ ያስገኘው የአምልኮ አንድነት ከተባለው መጽሐፍ ላይ “የአምላክን ቃል በድፍረት መናገርህን ቀጥል” የሚለውን 22ኛ ምዕራፍ በጥያቄና መልስ አቅርብ።

20 ደቂቃ:- “ወላጆች​—⁠ልጆቻችሁ ጠቃሚ ልማዶችን ማዳበር በሚችሉበት መንገድ ቅረጿቸው።” በንግግርና ልጆቻቸው በጥሩ መንፈሳዊ ሁኔታ ላይ ከሚገኙ ወላጆች ጋር ቃለ ምልልስ በማድረግ ይቀርባል። ወላጆች ልጆቻቸው በመስክ አገልግሎት እንዲካፈሉ ለማድረግ በወሰዷቸው አዎንታዊ እርምጃዎች ላይ ያተኩራሉ። ጊዜ በፈቀደ መጠን ለቤተሰብ ደስታ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 55-9 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 5 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 74 (168)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- “ደስተኛ አድራጊዎች ሁኑ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ማስተዋል በተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 2 ገጽ 120 አንቀጽ 6-8 ላይ በተገለጸው መሠረት ምን ምን ነገሮች በአምላክ አገልግሎት ተጨማሪ ደስታ እንደሚያስገኙልን ጥቀስ።

20 ደቂቃ:- ጤናማ የሆኑ መዝናኛዎችን መምረጥ ትችላለህ። አንድ ቤተሰብ በግንቦት 22, 1997 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ላይ የተሰጠውን ምክር ይወያይበታል። አባት የቤተሰቡ የመዝናኛ ምርጫ አሳስቦታል። ስም ሳይጠቅስ የሶፕ ኦፔራ ባሕርይ ያላቸውን የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልሞች የሚናገር ሲሆን ሙዚቃን ወይም ሌሎች የራዲዮ ፕሮግራሞችን ምንም ምርጫ ሳያደርጉ ዝም ብሎ ማዳመጥ የሚያስከትለውን ችግር ይጠቁማል። “በዛሬው ጊዜ ያለው መዝናኛ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?” (ከገጽ 4-7) የሚለውን በአጭሩ ይከልሱና ጤናማና ጠቃሚ በሆኑት የመዝናኛ ዓይነቶች ላይ ያተኩራሉ። አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 131-2 ላይ “መዝናኛ” የሚለውንና ገጽ 135-6 ላይ “ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” የሚለውን ተመልከት። ለመላው ቤተሰብ ጥቅም ሲባል ወላጆች አመራር በመስጠት ረገድ ስለሚጫወቱት ሚና እንዲሁም እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል መተባበሩ የሚያስገኘውን ጥቅም ጎላ አድርገህ ተናገር።

መዝሙር 84 (190) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ