ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- ጉባኤው ያለውን ከ1986 በፊት የታተመ ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። የሰው ልጅ አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍ ያላቸው ጉባኤዎች ይህንንም መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። በአማርኛ መንግሥትህ ትምጣ እና በሕይወት መትረፍ የሚባሉትን መጽሐፎች ለማበርከት ትኩረት ስጡ። የአምልኮ አንድነት መጽሐፍን ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ማበርከት ይቻላል። የወጣትነትህ መጽሐፍ ከተረፈ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮ መመለስ ትችላላችሁ። የካቲት:- ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? (እንግሊዝኛ)፣ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!፣ ወይም ጉባኤው ያለው ማንኛውም ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ። መጋቢት:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ልዩ ጥረት ይደረጋል። ሚያዝያ:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ሲደረግ ፍላጎት ለሚያሳዩ ሰዎች ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመርን ግብ በማድረግ እውቀት መጽሐፍን ወይም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ብሮሹር አበርክቱ።
◼ በዚህ ዓመት የምንጠቀምበት የሕክምና ሰነድ ወደፊት የሚላክላችሁ ሲሆን እስከዚያው ድረስ ግን አሁን በእጃችሁ ባለው ሰነድ መጠቀማችሁን ቀጥሉ።
◼ ከመጋቢት ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት አዲስ የሕዝብ ንግግር “የፍርድ ቀን—የሚያስፈራ ወይስ በተስፋ የሚጠበቅ?” የሚል ይሆናል።
◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት እሑድ ሚያዝያ 8 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የሚውለውን የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር ቢቻልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ሰዓት በአቅራቢያችሁ ከሚገኙ ምንጮች ጠይቃችሁ ተረዱ። በዚያ ዕለት ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በስተቀር ሌላ ስብሰባ ስለማይኖር የመጠበቂያ ግንብ ጥናቱ በሌላ ቀን እንዲመራ ተገቢው ዝግጅት መደረግ ይኖርበታል። የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሳምንቱን የስብሰባ ፕሮግራማቸውን እንደ አካባቢው ሁኔታ ማስተካከል ያስፈልጋቸዋል። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ቢያከብር ይመረጣል። ሁለት ጉባኤዎች አንድ ላይ ሆነው የመታሰቢያውን በዓል እንዲያከብሩ የሚያስገድድ ለየት ያለ ሁኔታ ሊኖር ቢችልም እንኳ በየዓመቱ ይህን ልማድ ማድረግ አይኖርባቸውም። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን ለማድረግ በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ ሁለት ሦስት ጉባኤዎች ካሉ አንዱ ወይም ሁለቱ ጉባኤዎች ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ መፈለግ ይችሉ ይሆናል። ከእንግዶች ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥና አዳዲሶችን ለማበረታታት የሚያስችል ጊዜ በመስጠት ሁሉም ከአጋጣሚው ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ ከተቻለ ሁለቱ ጉባኤዎች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ የ30 ደቂቃ ጊዜ እንድትመድቡ ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎች የሚወርዱበትንና የሚሳፈሩበትን ሁኔታ ጨምሮ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።
◼ በ2002 የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበት ዕለት የሚውለው የ 2001 የቀን መቁጠሪያ እንደሚያመለክተው አርብ መጋቢት 22 ሳይሆን ሐሙስ መጋቢት 28 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል።
◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው የ2001 ልዩ የሕዝብ ንግግር እሁድ ሚያዝያ 1 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ “የሚድኑት እነማን ናቸው?” የሚል ነው። የንግግሩ አስተዋፅዖ ይላክላችኋል። በዚህ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት፣ የወረዳ ወይም ልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ሚያዝያ 9 በሚጀምር ሳምንት ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ። ማንኛውም ጉባኤ ከሚያዝያ 1, 2001 በፊት ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ማቅረብ አይኖርበትም።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ:- የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን፣ እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፣ የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2001፣ T-22 (ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? )፤ አረብኛ:- የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ፤ እንግሊዝኛ:- የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን፣ የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ፣ የይሖዋ ምሥክሮች—እነማን ናቸው? (ብሮሹር)፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2001፤ የቴፕ ክሮች:- ለዘመናችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች (የ2000 የአውራጃ ስብሰባ ድራማ)፣ የመንግሥቱ ዜማዎች ቁ. 9፤ ፈረንሳይኛ:- የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን፣ የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2001፤ ኦሮምኛ:- የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ፤ ትግርኛ:- የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል፣ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው፣ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር—2001።
◼ እንደገና ይደርሱናል ብለን የምንጠብቃቸው፦ እንግሊዝኛ:- የቪዲዮ ክሮች:- እስከ ምድር ዳር ድረስ፣ በመለኮታዊ ትምህርት አንድ መሆን፣ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች. . . እውነተኛ ጓደኞች ማፍራት የምችለው እንዴት ነው?