የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/01 ገጽ 1
  • የአምላክን ቃል በትክክል ተጠቀምበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክን ቃል በትክክል ተጠቀምበት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክን ቃል በትክክል የምትጠቀም ነህን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • “የመንፈስን ሰይፍ” ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቀሙበት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ለአምላክ ቃል ጥብቅና ትቆማላችሁ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • በምታስተምሩበት ጊዜ አሳማኝ ማስረጃ አቅርቡ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 12/01 ገጽ 1

የአምላክን ቃል በትክክል ተጠቀምበት

1 ፊልጶስ ለአንድ ባለሥልጣን ሲመሰክር “አፉን ከፈተ፣ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት።” (ሥራ 8:35) ፊልጶስ ‘የእውነትን ቃል በትክክል ይጠቀም’ ነበር። (2 ጢ⁠ሞ. 2:​15 NW ) ይሁን እንጂ በዛሬው ጊዜ ብዙ አስፋፊዎች በሚመሰክሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስን እንደማይጠቀሙ ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች አስተውለዋል። በአገልግሎት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ትጠቀማለህ?

2 ለምናምንበትም ሆነ ለምናስተምረው ነገር ምንጩ የአምላክ ቃል ነው። (2 ጢ⁠ሞ. 3:16, 17) ሰዎች ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡ ከማድረጉም በላይ ለሕይወታቸው የሚጠቅም ትምህርት ይሰጣቸዋል። በአገልግሎታችን ላይ እንዲያው እኛን ደስ ስላለን ርዕሰ ጉዳይ ሰዎችን ከማወያየት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀሙ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። (ዕብ. 4:12) ብዙ ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው እውቀት ውሱን ስለሆነ በውስጡ የሚገኘውን ተግባራዊ መመሪያና ለሰው ልጅ የያዘውን የወደፊት ተስፋ ለማሳየት ከመጽሐፍ ቅዱስ ልናነብላቸው ያስፈልጋል።

3 በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብብ:- ቦርሳ ሳትይዝ አገልግሎት መውጣትን መሞከር ትችላለህ። የሚበረከተውን ጽሑፍ በባይንደር መጽሐፍ ቅዱስህን ደግሞ በእጅህ ወይም በኪስህ ልትይዝ ትችላለህ። ከዚያም ከአንድ ሰው ጋር ውይይት ስትጀምር ሰውዬው ሃይማኖታዊ ትምህርት ልትሰብከው እንደሆነ እንዲሰማው ሳታደርግ መጽሐፍ ቅዱስህን አውጣ። ከመጽሐፍ ቅዱስህ ጥቅስ አውጥተህ በምታነብበት ጊዜ አቋቋምህ የምታነጋግረው ሰው እያየ መከታተል በሚችልበት ሁኔታ ይሁን። ምናልባትም ራሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲያነብ ልትጋብዘው ትችላለህ። ሲነበብ ከመስማት ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ራሱ ሲመለከት በጥልቅ ሊነካ ይችላል። እርግጥ ነው፣ የጥቅሱን ሐሳብ እንዲገነዘብ ለመርዳት ሐሳቡን የሚያስተላልፉትን ቃላት ማጉላት ያስፈልጋል።

4 በአንድ ጥቅስ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ:- ራስህን ካስተዋወቅህ በኋላ እንዲህ ልትል ትችላለህ:- “ሰዎች ለሕይወታቸው መመሪያ ለማግኘት ወደ ተለያዩ ምንጮች ዞር ይላሉ። ከሁሉ የተሻለ ተግባራዊ መመሪያ የሚገኘው ከየት ነው ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህንን አባባል እንዴት ይመለከቱታል? [ምሳሌ 2:6, 7ን አንብብና መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ሰብዓዊ ጥበብ ብቃት ስለሚጎድለው ብዙ ሰዎችን ወደ ተስፋ መቁረጥ እየመራቸው ይገኛል። የአምላክ ጥበብ ግን ምንጊዜም እምነት የሚጣልበትና ጠቃሚ እንደሆነ ተረጋግጧል።” ከዚያም የምታበረክተውን ጽሑፍ አውጣና ከአምላክ የሚገኘውን ተግባራዊ ጥበብ የሚያጎላ አንድ ምሳሌ አሳየው።

5 ኢየሱስ ልበ ቅን ሰዎችን ለመርዳት ቅዱሳን ጽሑፎችን ተጠቅሟል። (ሉቃስ 24:32) ጳውሎስም ለሚያስተምራቸው ነገሮች ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃ ያቀርብ ነበር። (ሥራ 17:2, 3) የአምላክን ቃል በትክክል በመጠቀም ረገድ ችሎታችንን እያዳበርን ከሄድን በአገልግሎት በምንሠማራበት ጊዜ የሚኖረን ልበ ሙሉነትና ከአገልግሎቱ የምናገኘው ደስታ ይጨምራል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ