የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/01 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ታኅሣሥ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 31 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 12/01 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ታኅሣሥ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 44 (105)

13 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ታኅሣሥ 31 በሚጀምር ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ እስከ ምድር ዳር ድረስ በተባለው ቪዲዮ ላይ ውይይት ስለሚደረግ ሁሉም አስቀድመው ፊልሙን በማየት ተዘጋጅተው እንዲመጡ አበረታታ። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች በመጠቀም (1) የኅዳር 1 መጠበቂያ ግንብ እና (2) የኅዳር ንቁ! አስተዋጽኦ ማድረግ ስለሚቻልበት ዝግጅት በመጥቀስ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ።

12 ደቂቃ:- “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም።” ከኅዳር 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚቀርብ ንግግር።

ነ20 ደቂቃ:- “በመለኮታዊው ትምህርት አንድ መሆን​—⁠እውነተኛ የወንድማማችነት አንድነት ሲቃኝ።” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ክፍሉን ለማስተዋወቅና ለመደምደም በመጀመሪያውና በመጨረሻው አንቀጾች ተጠቀም። በቪዲዮው ላይ የሚደረገውን ውይይት ሕያው ለማድረግ የተዘጋጀውን እያንዳንዱን ጥያቄ ጠይቅ። በጉባኤው ውስጥ በሌላ አገር በተደረጉ ስብሰባዎች ላይ ተካፍለው የሚያውቁ ካሉ ድርጅታችን ዓለም አቀፋዊ ይዘትና አንድነት ያለው መሆኑን በራሳቸው ዓይን በመመልከታቸው የተሰማቸውን ስሜት እንዲናገሩ አድርግ። አሊያም በ1994 የዓመት መጽሐፍ ከገጽ 7-9 እና በ1995 የዓመት መጽሐፍ ከገጽ 8-11 ላይ ካሉት ልብ የሚነኩ ተሞክሮዎች የተወሰኑትን እንዲናገሩ አድርግ።

መዝሙር 100 (222) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 93 (211)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።

10 ደቂቃ:- “የ2002 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። ሁሉም የተሰጣቸውን ክፍል ለማቅረብ ትጉ እንዲሆኑ አበረታታ።

30 ደቂቃ:- “‘የአምላክ ቃል አስተማሪዎች’ በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ የተማርከውን በተግባር እያዋልክ ነውን?” በመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪው አማካኝነት በአውራጃ ስብሰባው ፕሮግራም ላይ ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ለአንድ ደቂቃ ያህል የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ ለእያንዳንዱ ቀን ፕሮግራም ከ9-​10 ደቂቃ መድብ። በእያንዳንዱ ንዑስ ርዕስ ስር የሚገኙትን ዋና ዋና ነጥቦች በአጭሩ ካቀረብክ በኋላ አድማጮች (1) ያገኙትን መመሪያ በሥራ ላይ ለማዋል ስላደረጉት ጥረት፣ (2) እንደዚህ በማድረጋቸው እንዴት እንደተጠቀሙና (3) ይበልጥ ማድረግ እንዳለባቸው የሚሰማቸው ምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ። ውይይቱን ሕያው ለማድረግ ለተሳትፎ የሚጋብዙ ጥያቄዎችን ተጠቀም። ሁሉም የተማሩትን በሥራ ላይ ማዋላቸው አስፈላጊ መሆኑን እንዲገነዘቡ እርዳቸው።

መዝሙር 97 (217) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 2 (4)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በጥር ወር የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ግለጽ። በገጽ 8 ላይ ያሉትን ሐሳቦች ተጠቅመህ አስተዋጽኦ ማድረግ ስለሚቻልበት ዝግጅት በመጥቀስ መጽሔት ሲበረከት የሚያሳዩ ሁለት አጫጭር ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። አንደኛውን ሠርቶ ማሳያ አንድ ወጣት እንዲያቀርበው አድርግ።

15 ደቂቃ:- “የአምላክን ቃል በትክክል ተጠቀምበት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በአንቀጽ 4 ላይ የሚገኘውን አቀራረብ የሚያሳይ ያልተጋነነ ሠርቶ ማሳያ ጨምረህ አቅርብ። በተጨማሪም ወቅታዊ በሆኑ የዓለም ሁኔታዎች የተጨነቁ ሰዎችን ለማበረታታት ወይም ለማጽናናት በአካባቢው የሚሠራበትን አንድ ውጤታማ አቀራረብ በሠርቶ ማሳያ አቅርብ። አጠር ያለ ተሞክሮ መናገር ይቻላል። አድማጮች መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም ምስክርነቱን ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል ብለው የሚያስቡት ለምን እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቅ።

20 ደቂቃ:- “ይሖዋ ላሳየን ፍቅር አመስጋኝ መሆን የሚያስገኛቸው በረከቶች​—⁠ክፍል 2።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከአንቀጽ 2-6 ያለውን ስትወያዩ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመመስከር፣ ደብዳቤ በመጻፍ ወይም በስልክ በመመስከር ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። ከተሞክሮዎቹ ውስጥ አንዱን ወይም ሁለቱን በሠርቶ ማሳያ ለማቅረብ አስቀድመህ ዝግጅት አድርግ። ሁሉም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምስክርነት የሰጡበትን ሰዓት የሚመዘግቡበት ማስታወሻ ደብተር ወይም የሪፖርት ቅጽ እንዲይዙ አሳስባቸው። በየጊዜው የሚመዘግቧቸው ጥቂት ደቂቃዎች ቢሆኑም በወሩ መጨረሻ አንድ ላይ ሊደመሩ ይችላሉ። በተጨማሪም በሕመም ወይም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ወርሃዊ ሪፖርትህ ዝቅተኛ ቢሆንም አዘውታሪ አስፋፊ ለመሆን ያደረግኸውን ጥረት የሚያሳይ ስለሆነ በዚያው ወር መመለስ አለበት እንጂ የሚቀጥለው ወር ሪፖርት ላይ መደመር የለበትም።

መዝሙር 69 (160) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ታኅሣሥ 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 58 (138)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲመልሱ አስታውሳቸው። ሁሉም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምስክርነት የሰጡበትን ሰዓት የሚመዘግቡበት ማስታወሻ ደብተር ወይም የሪፖርት ቅጽ እንዲይዙ አሳስባቸው። በየጊዜው የሚመዘግቧቸው ጥቂት ደቂቃዎች ቢሆኑም በወሩ መጨረሻ አንድ ላይ ሊደመሩ ይችላሉ። በተጨማሪም በሕመም ወይም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ወርሃዊ ሪፖርትህ ዝቅተኛ ቢሆንም አዘውታሪ አስፋፊ ለመሆን ያደረግኸውን ጥረት የሚያሳይ ስለሆነ በዚያው ወር መመለስ አለበት እንጂ የሚቀጥለው ወር ሪፖርት ላይ መደመር የለበትም። በአዲሱ ዓመት ጉባኤያችሁ የስብሰባ ሰዓት ለውጥ የሚያደርግ ከሆነ ሁሉም በአዲሱ የስብሰባ ሰዓት አዘውትረው እንዲገኙ በደግነት አሳስባቸው። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችና አዘውትረው በስብሰባ የማይገኙ አስፋፊዎች የተደረገውን ለውጥ እንዲያውቁ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ሽማግሌዎች የሚገባቸውን አክብሮት ስጧቸው። ሁለት ወይም ሦስት የጉባኤ አገልጋዮች በሰኔ 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 18-19 ላይ ይወያያሉ። ሰብዓዊ ሥራ፣ የቤተሰብ ኃላፊነቶችና ቲኦክራሲያዊ ሥራዎችን ጨምሮ ሽማግሌዎች ስለሚያከናውኗቸው የተለያዩ ሥራዎች ሐሳብ ይሰጣሉ። ሁሉም ሊያበረታቷቸው፣ ሸክማቸውን ሊያቀሉላቸውና የሚሰጡትንም መመሪያ ሊከተሉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ጥቀሱ። የጉባኤ አገልጋዮቹ ሽማግሌዎች ጠቃሚ የሆነ አገልግሎት እያከናወኑ እንደሆነና ‘ከመጠን ይልቅ አክብሮት’ እንደሚገባቸው ይስማማሉ።​—⁠1 ተ⁠ሰ. 5:12, 13

20 ደቂቃ:- “እስከ ምድር ዳር ድረስ​—⁠መመስከር” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሁሉም ባሉበት አካባቢም ሆነ የምሥራቹ ሰባኪ ይበልጥ በሚያስፈልግበት ቦታ ምሥራቹን ለሌሎች ለማዳረስ ከአሁኑ በበለጠ ምን ማድረግ እንደሚችሉ በቁም ነገር እንዲያስቡበት አበረታታቸው። የሐምሌ 2001 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 4ን ተመልከት። በየካቲት ኖኅ​—⁠አካሄዱን ከአምላክ ጋር አደረገ የተባለውን ቪዲዮ እንከልሳለን።

መዝሙር 13 (33) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ጥር 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 81 (181)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- ሕይወታችሁን ከሁሉ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት። የአንድ ቤተሰብ አባላት በነሐሴ 15, 1998 መጠበቂያ ግንብ በገጽ 8-9 ላይ ይወያያሉ። አባትየው ቤተሰቡ ሐዘን ሳይሆን ደስታ የሚያመጣውን መንገድ እንዲከተል ይፈልጋል። የማስተዋል ችሎታ መጠቀም፣ ቅድሚያ ሊሰ​ጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ቅድሚያ መስጠትና በይሖዋ መታመን ባላቸው አስፈላጊነት ላይ በማተኮር እንዴት ደስታ ማግኘት እንደሚችሉ የሚያሳዩትን በርዕሱ ውስጥ የሚገኙ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክሮች ይከልሳሉ። በቤተሰብ ደረጃ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸውን ተግባራዊ የሚሆኑ ማስተካከያዎች ያወጣሉ።

15 ደቂቃ:- ለመንግሥት አዳራሻችን ትኩረት መስጠት። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የመንግሥት አዳራሹ የሚገኝበትን ሁኔታ ተመልከት። ንጹሕ፣ በሥርዓት የተያዘና የሚስብ ነው? ትኩረት የሚያሻው ወይም መሻሻል ያለበት ነገር ካለ ጥቀስ። ከመታሰቢያው በዓል በፊት ልዩ የጽዳት ዘመቻ ለማድረግ ምን እቅድ ተይዟል? ከዘመቻው በፊት ጥገና የሚያስፈልጋቸው ምን ነገሮች አሉ? ጉባኤው እንዴት ድጋፍ ሊያበረክት እንደሚችል ግለጽ። የአምልኮ ቦታችን ለይሖዋ ቤት የሚገባውን ውበትና ክብር እንዲያንጸባርቅ ማድረግ ያለውን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።​—⁠መዝ. 84:1

መዝሙር 64 (151) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ